Get Mystery Box with random crypto!

መረጃ የአማራ ብልፅግና አመራሮች የክልሉ መንግስታዊ መዋቅር በፈረሰባቸው አካባቢዎች አመራሮቹ | አዲስ ነገር መረጃ

መረጃ

የአማራ ብልፅግና አመራሮች የክልሉ መንግስታዊ መዋቅር በፈረሰባቸው አካባቢዎች አመራሮቹ እስከ ህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በየአመራር ቦታቸው በመገኘት መደበኛ ስራቸውን እንዲቀጥሉ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጠ መሆኑ ታወቀ፡፡

በክልሉ ከወራት በፊት የተቀሰቀሰውን ውጊያ ተከትሎ በበርካታ አካባቢዎች በንግስታዊ መዋቅሮች የፈረሱ ሲሆን በርካታ አመራሮችም  ያልታወቁ ሰዎች በሚል በደፈጣ ጥቃቶች ተገድለዋል። አመራሮቹን ኢላማ ባደረገ መልኩ እየደረሱ ያሉትን ጥቃቶች እና ግድያዎች ተከትሎ በርካታ በየወረዳው እና በየዞኑ ያሉ አመራሮች የመንግስት የተሻለ ጥበቃ አለ ብለው ወዳመኑባቸው አካባቢዎች የተሰባሰቡ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘም የአማራ ክልላዊ መንግስት ሁሉም የዞን እና የወረዳ አመራሮች እስከ ህዳር 30 ድረስ በተመደቡባቸው ቦታዎች በስራ ገበታቸው ላይ እንዲገኙ በጥብቅ መመሪያ  የወረደላቸው መሆኑ ነው የታወቀው፡፡