የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገራሚ ንግግር
<< ኢትዮጵያ ያመጣችውን የኢኮኖሚ ዕድገት ለመገንዘብ ኢትዮጵያውያን 15 ዓመት ያስፈልጋቸዋል >> - ጠ/ሚ ዐብይ አህመድጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት < ስለሰው ሰራሽ አስተውሎት ስልጠና ተከታትለው ለተመረቁ ወጣቶች > ህዳር 1 ቀን 2016 ዓ.ም ባስተላለፉት መልዕክት ነው።
ዐብይ እርሳቸው ወደስልጣን ከመጡ በኋላ ያሉት አምስት ዓመታት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት የተመዘገበበት መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል።
<< ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ዕድገት የዛሬ አምስት አመት ከምስራቅ አፍሪካ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ነበረች >> ሲሉ ያስታወሱት ዐብይ << አሁን ግን አንደኛ አይደለችም >> ሲሉ ተመዝግቧል ያሉትን ዕድገት ማስረዳት ይጀምራሉ።
<< የሁሉም ጎረቤት ሀገራት ዕድገት ተደምሮ፣ ከኢትዮጵያ አንሷል >> ሲሉ ተደምጠዋል። ለዚህ መጥቷል ላሉት ኢኮኖሚያዊ ዕድገት አሐዛዊ መረጃዎች ያልጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ዕድገት ግን ኢትዮጵያውያን ለመገንዘብ አስርት ዓመታት እንደሚያስፈልጋቸው አስረድተዋል።
ለዚህ ብያኒያቸው < ይሆናል > ያሉትን አመክንዮም አያይዘው አስገንዝበዋል። << እያንዳንዱ ጓዳ ገብቶ፣ የእያንዳንዱ ቤተሰብ ችግር እስኪፈታ ድረስ ሰው ያልደረሰለትን ውጤት በሩቅ አይቶ ሊገነዘብ አይችልም >> ብለዋል።
ዐብይ ከዚህ ቀደምም በብሪክስ ጉባዔ ወቅት ባደረጉት ንግግር ተመሳሳይ ይዘት ያለው መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል።
ዐብይ <<ከግራ ቀኝ የሚሰማው ዜና አንደኛ፣ በዚያ ልክ የሚያውቁ ሰዎች አይደሉም የሚናገሩት፤ኢትዮጵያንም የማያውቁ፣ በትምህርትም ይሄን የሚባል ታሪክ የሌላቸው ዝምብለው የሚተነትኑ ስለሆኑ እነርሱን በመስማት ጊዜ እንዳታባክኑ >>ሲሉ በአደራ ያጀቡትን ማሳሰቢያ ለተመራቂ ወጣቶቹ ነግረዋቸዋል።
Via - አሻም ቴቪ
@Addis_News
@Addis_News