Get Mystery Box with random crypto!

የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ግጭቶች በተከሰቱባቸውና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በ | አዲስ ነገር መረጃ

የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ግጭቶች በተከሰቱባቸውና አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀባቸው ክልሎች የመድኅን ከባንያዎች የመድኅን ሽፋን እንዳይሰጡ የጣለውን እገዳ በከፊል ማንሳቱን ሪፖርተር ዘግቧል።

የኢንሹራንስ ኮርፖሬሽኑ፣ በፖለቲካዊ ግጭት እስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በታወጀባቸው ክልሎች በካፒታል ንብረቶች ላይ ብቻ የኢንሹራንስ ሽፋን እገዳው ተፈጻሚ እንዳይኾን መወሰኑን ዘገባው አመልክቷል። በፖለቲካዊ ግጭት ሳቢያ በተንቀሳቃሽ ንብረቶች ላይ ለሚደርሱ ጉዳቶች ግን፣ የኢንሹራንስ ሽፋን እገዳው እንደጸና ይቀጥላል ተብሏል። የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኮርፖሬሽን እገዳውን የጣለው ባለፈው ነሃሴ ነበር። ኮርፖሬሽኑ እገዳውን በከፊል ያነሳው፣ ከኢትዮጵያ መድኅን ኩባንያዎች ማኅበር ጋር በተደረገ ድርድር እንደኾነ ዘገባው ገልጧል።

[Wazema]

@Addis_News
@Addis_News