Get Mystery Box with random crypto!

የገጠር መሬት በማስያዝ ብድር ማግኘት የሚያስችል ድንጋጌ የተካተተበት ረቂቅ ሕግ ለፓርላማ ቀረበ! | አዲስ ነገር መረጃ

የገጠር መሬት በማስያዝ ብድር ማግኘት የሚያስችል ድንጋጌ የተካተተበት ረቂቅ ሕግ ለፓርላማ ቀረበ!

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተመራው የገጠር መሬት አስተዳደር አጠቃቀም ረቂቅ አዋጅ፣ የመሬት ይዞታን በማስያዝ ብድር ለማግኘት የሚያስችል ድንጋጌ ተካቶበት ቀርቧል፡፡

ረቂቁ አርሶና አርብቶ አደሮች ከመሬታቸው ያለ መፈናቀል መብታቸውን ማስከበር አስፈላጊ በመሆኑ ምክንያት፣ በመሬት የመጠቀም መብትን በማስያዝ ብድር ማግኘት እንዲችሉ ከአገሪቱ የመሬት ፖሊሲ ጋር በማጣጣም በጥንቃቄ ታስቦ የተዘጋጀ አዋጅ ነው፡፡

የገጠር መሬትን ዋስትና አድርጎ ማስያዝን የሚመለከት የሕግ ድንጋጌ እስካሁን አለመኖሩ በረቂቁ ተገልጿል፡፡ በዚህም በአሁኑ ጊዜ በአሠራር እየታዩ ያሉ የአነስተኛ የገንዘብ ተቋማት የገጠር መሬት ይዞታ መብትን በመያዝ ብድር የመስጠት ተግባር፣ ለሕጉ መሻሻል አስፈላጊ መሆኑ በረቂቁ ተመልክቷል፡፡

የገጠር መሬት ባለቤት የመጠቀም መብቱን በየክልሉ በሚወጡ ሕጎች በሚወሰን የጊዜ ገደብ አማካይነት፣ለፋይናንስ ተቋማት ለብድር ዋስታና ማስያዝ እንደሚቻል ተገልጿል፡፡ ባለይዞታዎች በመሬታቸው የመጠቀም መብታቸውን በማስያዝ፣የዘመናዊ የእርሻ መሣሪያዎችና ግብዓቶችን የሚያገኙበት አሠራር ማመቻቸትን ያለመ ስለመሆኑ በረቂቁ ተብራርቷል፡፡

አበዳሪዎች ሕጋዊ የፋይናነስ ተቋማት ብቻ ሲሆኑ፣ አራጣ አበዳሪነትን ለመከላከል ግለሰቦች በሕጉ መሠረት አበዳሪ ሆነው በመሬት የመጠቀም መብትን እንደ ማስያዣ ሊይዙ እንደማይችሉ በረቂቁ ተደንግጓል፡፡ ግብዓት ለመግዛት የገንዘብ እጥረት የሚያጋጥማቸው መሬታቸውን ያከራዩ ወይም ያስጠምዱ የነበሩ ባለይዞታዎች፣በመሬት የመጠቀም መብታቸውን በማስያዝ ብድር ወስደው አምርተው ብድራቸውን እንዲመልሱ የሚያስችል መብት ስለመሆኑም በረቂቁ ተጠቁሟል።(Reporter)

@Addis_News
@Addis_News