Get Mystery Box with random crypto!

ላሊበላ ጉዳት ደረሰበት በሚል የሚናፈሰው ወሬ መሠረት ቢስ ነው ሲል የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም | አዲስ ነገር መረጃ

ላሊበላ ጉዳት ደረሰበት በሚል የሚናፈሰው ወሬ መሠረት ቢስ ነው ሲል የአማራ ክልል ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ አሳወቀ

ከትናንት በስቲያ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰሜን ወሎ ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርሚያስ ለቤተክርስቲያኗ የሚዲያ ተቋም በሰጡት ቃል ታሪካዊ ቅርሱ በጦርነት ምክኒያት አደጋ ላይ መሆኑን ተናግረዉ ነበር።

ይህንኑ ከተትሎ በፍልፍል አብያተ ክርስቲያናቱ ላይ ጉዳት መድረሱን የሚያሳዩ ምስዕሎች በማህበራዊ የትስስር ገጾች ላይ መሰራጨታቸዉን ዳጉ ጆርናል ታዝቧል። አንዳንዶቹም ከዚህ በፊት በነረዉ ጦርነት ቅርሱ ላይ ከደረሰዉ ጉዳት የተወሰዱ ናቸዉ።

በዛሬዉ እለት የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ባሰራጨው አጭር መግለጫ ፤ መረጃዉን አጣጥሎ ፤ በዚህ የዓለማችን ቀደምት ቅርስ ስም ሐሰተኛ ፕሮጋንዳ እየነዙ፤ ሕዝብን እያደናገሩ አሸናፊ ለመሆን መሞከር ሞራላዊና ኅሊናዊ ኪሳራን እንጅ ድልን አያጎናጽፍም ብሏል ቢሮው በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ ባጋራው መረጃ።

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በሚገኘው የላሊበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ላይ ጉዳት እንደደረሰ ተደርጎ ከትናንት ጀምሮ የሚናፈሰው ወሬ መሠረት ቢስ ነው ሲልም ጠቅሷል።

በላሊበላ ስም መቀደስ እንጅ የጥፋት ድግስ መደገስ አስፈላጊና ተገቢ አይደለም ያለዉ ቢሮዉ የላልይበላ ውቅር አብያተክርስቲያናት ቦታውም ቅዱስ ነው ህንጻውም ላይ የደረሰ ጉዳት የለም ሲል ተናግሯል።

@Addis_News
@Addis_News