Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ነገር መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_news — አዲስ ነገር መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_news — አዲስ ነገር መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @addis_news
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 76.16K
የሰርጥ መግለጫ

አዲስ ነገር መረጃዎች
መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addisnegermereja_bot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-05-20 15:57:43
የሟቾች ቁጥር 20 ደረሰ!

የመደ ወላቡ መምህራንን ይዞ ሲጓዝ በነበረው ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 20 ደረሰ

የመደ ወላቡ መምህራንን ይዞ ሲጓዝ በነበረው ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁን ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር 20 መድረሱ ተገለጸ። የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ዛሬ ማለዳ ለማስተማር ወደ ሻሸመኔ ካምፓስ በመጓዝ ላይ እያሉ በደረሰባቸው የትራፊክ አደጋ የ15 መምህራን ሕይወት ማለፉ ተገልጾ ነበር።

ተሸከርካሪው መንገድ ስቶ ወደ ገደል በመግባቱ በተፈጠረው በዚህ አደጋ ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር በአምስት ጨምሮ 20 መድረሱን ኦቢኤን ዘግቧል። ከአደጋው በሕይወት የተረፉት ሌሎች ሰዎች በአደባ፣ ዶዶላ እና ሮቤ ሆስፒታሎች ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ኢብራሂም ከሊል ተናግረዋል።

@Addis_News
@Addis_News
12.3K viewsedited  12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 13:15:14 Updated አጫጭር መረጃዎች

የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ 15 መምህራን ህይወታቸውን ያጡበት አደጋ በተመለከተ

የመዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከሚገኝበት ሮቤ ከተማ ወደ ዶዶላና አዳባ ካምፓሶች ለማስተማር ሲጓዙ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 15 ከፍተኛ ልምድ ያላቸው መምህራን ህይወታቸውን አጥተዋል።

50 ሰው ባሳፈረ አውቶቡስ ሲጓዙ የነበረ ሲሆን ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች በተጨማሪ 20 ሰዎች ክፉኛ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሮቤና ሻሸመኔ ሆስፒታል ተልከዋል።

መምህራኑ የርቀት ተማሪዎች የሆኑ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፣ የስፖርት ፣የጤናና የግብርና ትምህርት ክፍሎች ተማሪዎች ለማስተማር እያቀኑ እንደነበር በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎችና የመምህራን ጉዳዮች ዲን ዶ/ር ለት በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርከሪው በተለምዶ ሰብስቤ ዋሻ ውስጥ ተገልብጧል።ይህው አካባቢ በተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ የሚደርስበት ነው።

ተሽከርካሪው ያልተነሳ ሲሆን ክሬን በመፈለግ ቀሪ አስክሬን ለማውጣት እየተሞከረ መሆኑን በስፍራው የሚገኙት ዶ/ር ለታ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።


ዳጉ_ጆርናል

@Addis_News
@Addis_News
12.4K views10:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 13:13:51
እመኑኝ መረጃ ህይወት ነው
ሰበር ና እውን ፣ እጅግ ታማኝ እና ወቅታዊ ድብቅ
ሀገራዊና ክልል አቀፍ የመረጃ  ቻናል ልጠቁማችሁ
ገባ ገባ ብላችሁ መረጃ በየሰዓት አግኙ
ይኸው
https://t.me/+Rq8HblaNUhkySdXf
4.0K views10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 11:47:17
በትራፊክ አደጋ 15 የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ህይወታቸው አለፈ

15 የመደወላቡ ዩንቨርሲቲ መምህራን ዛሬ ማለዳ ለማስተማር ወደ ሻሸመኔ ካምፓስ በመጓዝ ላይ እያሉ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል፡፡

የሮቤ ከተማ ከንቲባ አቶ ንጋቱ ሞቱማ ተሸከርካሪው መንገድ በመሳት በተፈጠረው አደጋ እስካሁን 15 የዩንቨርሲቲው መምህራን ህይወት ማለፉን ገልፀዋል ሲል ኦቢኤን ዘግቧል።

@Addis_News
@Addis_News
11.3K views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 11:32:29
አስደሳች ዜና
ጠባሳዎ አስጨንቅዎታል


በአደጋ፣በህክምና እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች በሰውነትዎ ላይ ያለውን ጠባሳ የሚያጠፉበት ክሬም

➤➲   የብጉር ጠባሳዎችን

➤➲   ማድያትን የሚያጠፋ

➤➲   የሸንተረር ምልክቶችን

➤➲   የቆዳ ቀዶ ጥገና ጠባሳዎችን

➤➲   የቆዳ ቁስሎችን

➤➲   የጭረት ምልክቶችን

➤➲   የንክሻ ምልክቶችን


ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት የማይፈጥር በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥ የሚያሳይ


                               ያሉበት እናደርሳለን


-------------------------------
ለበለጠ መረጃ +251964593642
                             +251906495051
                             +251907495051

Telegram:     t.me/AM_CS
                            t.me/AM_CS1
                            t.me/AM_CS2
-------------------------------

ተጨማሪ የዘመኑ ምርጥ ምርቶችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/+UTXVYbFomXPc4JFm
https://t.me/+UTXVYbFomXPc4JFm
10.2K views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 10:28:28 በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለቡና ምርት የሚውለው መሬት ከግማሽ በላይ እንደሚቀንስ ተገለጸ

የአየር ንብረት ለውጥ ለቡና ምርት የሚያገለግለውን የእርሻ መሬት መጠን በቀጣዮቹ 77 ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ54 በመቶ በላይ በሆነ መጠን እንደሚቀንሰው አዲስ ይፋ የተደረገ ጥናት አመላክቷል፡፡

ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን የበካይ ጋዝ መጠን በመቀነስና ሌሎች ሥራዎችን በመስራት የዓለም የሙቀት መጠን በ1 ነጥብ 5 እና 2 ድግሪ ሴንቲ ግሬድ መካከል የተገደበ እንዲሆን የተደረሰው ዓለም አቀፍ ስምምነት ቢከበር እንኳን፤ ቡና የሚያበቅለው የመሬት መጠን እንዲቀንስ እና በምርቱ ውጤት ላይ የሚደርሰው አሉታዊ ተፅዕኖ አይቀሬ ነው ተብሏል፡፡

በክርስትያናዊ የበጎ አድራጎት ተቋም በኩል ይፋ በተደረገው ጥናት መሰረት፤ በአየር ንብረት ለውጡ ሳቢያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በቡና ምርት በዓለም አቀፍ ገበያ ታዋቂ የሆኑ እንደ ብራዚል፣ ቬትናም እና ለሌሎች አገራት በዋናነት ተጎጂ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡

የሙቀት መጨመር፣ ያልተስተካከል ዝናብ፣ በሽታ፣ ድርቅ እና የመሬት መንሸራተት እንዲሁም ሌሎች ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች የዓለም የቡና ምርት እንዲመናመን እያደረጉ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

አፍሪካ የካርቦን ልቀት 4 በመቶ ብቻ ሆኖ ሳለ በአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ተጎጂ ነች የተባለ ሲሆን፤ ኃያላን አገራት የካርቦን ልቀት መጠናቸውን ሊቀንሱ እና ለታዳጊ አገራት ተገቢውን ካሳ ሊከፍሉ ይገባል ነው የተባለው፡፡

ከኢትዮጵያ የወጪ ንግድ የቡና ምርት ዋናው እና ቀዳሚው ቢሆንም፤ ዘርፉ የዚሁ ዓለም አቀፍ ስጋት ተጋላጭ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

@Addis_News
@Addis_News
10.3K views07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 10:27:37
9.8K views07:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 09:39:25
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ ከህብረተሰቡ የሚቀርቡ የምክክር አጀንዳዎችን ከዛሬ ጀምሮ መቀበል እንደጀመረ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚላኩለትን የምክክር አጀንዳዎች ከዛሬ ጀምሮ መቀበል እንደጀመረ አስታወቀ። ኮሚሽኑ በሀገራዊ ምክክሩ ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን የመለየት ስራን፤ በ4 ክልሎች እና በ1 የከተማ አስተዳደር ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ እንደሚያከናውንም ገልጿል።

የምክክር ኮሚሽኑ ዛሬ አርብ ግንቦት 11፤ 2015 በጽህፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ተሳታፊዎችን የመለየት ስራ የሚጀመረው በጋምቤላ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ሀረሪ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እንደሆነ ይፋ አድርጓል። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ፤ በአራቱ ክልሎች እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባሉ ሁሉም ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ “የተለዩ የህብረተሰብ ክፍሎች” “ይወክሉኛል” የሚሏቸውን ተሳታፊዎች እንዲመርጡ እንደሚደረግ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ከተሳታፊዎች የመለየት ስራ ጎን ለጎን በቀጣዩ ሳምንት በዋናነት የሚያከናውነው ስራ “አጀንዳዎች ማሰባሰብ” መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ ገልጸዋል። በሀገራዊ ምክክሩ ላይ ሊቀርቡ ይገባሉ የሚባሉ አጀንዳዎች “በቀጥታ ከህዝቡ” የሚሰበሰቡ መሆኑን ያስታወሱት ፕሮፌሰር መስፍን፤ ፍላጎቱ ያላቸው ሰዎች “በኢሜል፣ በአካል ወደ ኮሚሽኑ በመምጣት እና በፖስታ” አጀንዳዎችን ማቅረብ እንደሚችሉ አስታውቀዋል። ኮሚሽኑ በእንደዚህ አይነት መልኩ የሚመጡ አጀንዳዎችን ከዛሬ ጀምሮ መቀበል እንደሚጀምር ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ ሂሩት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።

 @Addis_News
@Addis_News
10.1K views06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 09:38:28
የትዳር እና የወንድ ልጅ ችግር የሆነውን የስንፈተ ወሲብ እንዲሁም የብልት ቁመት ማነስን በዘላቂነት ችግሩን የሚፈታ ORGINAL EUROPE STANDARD መዳኒቶች እኛ ጋር አሉ
   MAXMAN TITAN_GEL VIMAX
የብልት መጠንን በዘላቂ ሁኔታ ለመጨመር
በግንኙነት ወቅት ቶሎ ላለመርጨት
የተሻለ የወሲብ ፍላጎት አና ችሎታ የሚጨምር
ብልት ውጥር እና ቀጥ ብሎ እንዲቆይ
  % ኦሪጂናል (noside effect )
  % ተፈጥሮዊ (herbal)
                         +251907270050
                         +251907270050
እንዲሁም ኅርባል ክብደት መጨመሪያ አለ ይደውሉ
አ.አ ላላችሁትም በእራሳችን transport  ያሉበት ድረስ በ 30 ደቂቃ እናደርሳለን
ወደ ክልል ከተሞች በፖስታ ቤት እንልካለን
ለተጨማሪ መረጃ
https://t.me/TWAKELpharmacy
https://t.me/andehabsha
10.0K views06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-20 08:02:38
የሱዳን ጦር መሪ አል ቡርሃን ተቀናቃኛቸዉንና ምክትላቸው ዳጋሎን ከስልጣን አነሱ

የሱዳን ጦር አዛዥ ሌተናል ጀነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ምክትላቸውን እና የፈጣን ደጋፊ ሃይሎች (RSF) አዛዥ መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ ወይም ሄሜቱ በመባል የሚታወቁትን ከስልጣናቸው አሰናብተዋል፡፡

ጄኔራል ቡርሃን እና ሄሜቲ ከጥቅምት 2021 ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት ጀምሮ የገዢው ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር እና ምክትል ሆነው አገልግለዋል።ጀነራል ቡርሃን በዛሬዉ እለት በተለቀቀው አዋጅ የቀድሞ የአማፂ ቡድን መሪ የነበሩትን ማሊክ አጋርን ምክትል አድርገው ሾመዋል።

ማሊክ አጋር የሱዳም ሉዓላዊው ምክር ቤት አባል ናቸው።የሉዓላዊው ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት እና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አዋጁ በአስቸኳይ እንዲተገበር መመሪያ ሰጥቷል።የጦር አዛዡ አል ቡርሃን ባለፈው ወር የአርኤስኤፍን ቡድን እንዲበተን በማድረግ ተዋጊዎቹን በአማጺነት ከፈረጀ በኃላ በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል የስልጣን ሽኩቻ ተፈጥሯል፡፡

@Addis_News
@Addis_News
10.7K views05:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ