Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ ከህብረተሰቡ የሚቀርቡ የምክክር አጀንዳዎችን ከዛሬ ጀምሮ መቀበ | አዲስ ነገር መረጃ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ ከህብረተሰቡ የሚቀርቡ የምክክር አጀንዳዎችን ከዛሬ ጀምሮ መቀበል እንደጀመረ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የሚላኩለትን የምክክር አጀንዳዎች ከዛሬ ጀምሮ መቀበል እንደጀመረ አስታወቀ። ኮሚሽኑ በሀገራዊ ምክክሩ ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን የመለየት ስራን፤ በ4 ክልሎች እና በ1 የከተማ አስተዳደር ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ እንደሚያከናውንም ገልጿል።

የምክክር ኮሚሽኑ ዛሬ አርብ ግንቦት 11፤ 2015 በጽህፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፤ ተሳታፊዎችን የመለየት ስራ የሚጀመረው በጋምቤላ፣ ሲዳማ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ሀረሪ ክልሎች እንዲሁም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እንደሆነ ይፋ አድርጓል። የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ፤ በአራቱ ክልሎች እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ባሉ ሁሉም ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ “የተለዩ የህብረተሰብ ክፍሎች” “ይወክሉኛል” የሚሏቸውን ተሳታፊዎች እንዲመርጡ እንደሚደረግ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ ከተሳታፊዎች የመለየት ስራ ጎን ለጎን በቀጣዩ ሳምንት በዋናነት የሚያከናውነው ስራ “አጀንዳዎች ማሰባሰብ” መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ ገልጸዋል። በሀገራዊ ምክክሩ ላይ ሊቀርቡ ይገባሉ የሚባሉ አጀንዳዎች “በቀጥታ ከህዝቡ” የሚሰበሰቡ መሆኑን ያስታወሱት ፕሮፌሰር መስፍን፤ ፍላጎቱ ያላቸው ሰዎች “በኢሜል፣ በአካል ወደ ኮሚሽኑ በመምጣት እና በፖስታ” አጀንዳዎችን ማቅረብ እንደሚችሉ አስታውቀዋል። ኮሚሽኑ በእንደዚህ አይነት መልኩ የሚመጡ አጀንዳዎችን ከዛሬ ጀምሮ መቀበል እንደሚጀምር ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ ሂሩት ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።

 @Addis_News
@Addis_News