Get Mystery Box with random crypto!

በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለቡና ምርት የሚውለው መሬት ከግማሽ በላይ እንደሚቀንስ ተገለጸ የ | አዲስ ነገር መረጃ

በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለቡና ምርት የሚውለው መሬት ከግማሽ በላይ እንደሚቀንስ ተገለጸ

የአየር ንብረት ለውጥ ለቡና ምርት የሚያገለግለውን የእርሻ መሬት መጠን በቀጣዮቹ 77 ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ54 በመቶ በላይ በሆነ መጠን እንደሚቀንሰው አዲስ ይፋ የተደረገ ጥናት አመላክቷል፡፡

ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን የበካይ ጋዝ መጠን በመቀነስና ሌሎች ሥራዎችን በመስራት የዓለም የሙቀት መጠን በ1 ነጥብ 5 እና 2 ድግሪ ሴንቲ ግሬድ መካከል የተገደበ እንዲሆን የተደረሰው ዓለም አቀፍ ስምምነት ቢከበር እንኳን፤ ቡና የሚያበቅለው የመሬት መጠን እንዲቀንስ እና በምርቱ ውጤት ላይ የሚደርሰው አሉታዊ ተፅዕኖ አይቀሬ ነው ተብሏል፡፡

በክርስትያናዊ የበጎ አድራጎት ተቋም በኩል ይፋ በተደረገው ጥናት መሰረት፤ በአየር ንብረት ለውጡ ሳቢያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በቡና ምርት በዓለም አቀፍ ገበያ ታዋቂ የሆኑ እንደ ብራዚል፣ ቬትናም እና ለሌሎች አገራት በዋናነት ተጎጂ እንደሚሆኑ ተገልጿል፡፡

የሙቀት መጨመር፣ ያልተስተካከል ዝናብ፣ በሽታ፣ ድርቅ እና የመሬት መንሸራተት እንዲሁም ሌሎች ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ አደጋዎች የዓለም የቡና ምርት እንዲመናመን እያደረጉ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

አፍሪካ የካርቦን ልቀት 4 በመቶ ብቻ ሆኖ ሳለ በአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ተጎጂ ነች የተባለ ሲሆን፤ ኃያላን አገራት የካርቦን ልቀት መጠናቸውን ሊቀንሱ እና ለታዳጊ አገራት ተገቢውን ካሳ ሊከፍሉ ይገባል ነው የተባለው፡፡

ከኢትዮጵያ የወጪ ንግድ የቡና ምርት ዋናው እና ቀዳሚው ቢሆንም፤ ዘርፉ የዚሁ ዓለም አቀፍ ስጋት ተጋላጭ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

@Addis_News
@Addis_News