Get Mystery Box with random crypto!

Updated አጫጭር መረጃዎች የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ 15 መምህራን ህይወታቸውን ያጡበት አደጋ | አዲስ ነገር መረጃ

Updated አጫጭር መረጃዎች

የመዳ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ 15 መምህራን ህይወታቸውን ያጡበት አደጋ በተመለከተ

የመዳወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከሚገኝበት ሮቤ ከተማ ወደ ዶዶላና አዳባ ካምፓሶች ለማስተማር ሲጓዙ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 15 ከፍተኛ ልምድ ያላቸው መምህራን ህይወታቸውን አጥተዋል።

50 ሰው ባሳፈረ አውቶቡስ ሲጓዙ የነበረ ሲሆን ህይወታቸውን ካጡ ሰዎች በተጨማሪ 20 ሰዎች ክፉኛ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሮቤና ሻሸመኔ ሆስፒታል ተልከዋል።

መምህራኑ የርቀት ተማሪዎች የሆኑ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፣ የስፖርት ፣የጤናና የግብርና ትምህርት ክፍሎች ተማሪዎች ለማስተማር እያቀኑ እንደነበር በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎችና የመምህራን ጉዳዮች ዲን ዶ/ር ለት በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርከሪው በተለምዶ ሰብስቤ ዋሻ ውስጥ ተገልብጧል።ይህው አካባቢ በተደጋጋሚ የትራፊክ አደጋ የሚደርስበት ነው።

ተሽከርካሪው ያልተነሳ ሲሆን ክሬን በመፈለግ ቀሪ አስክሬን ለማውጣት እየተሞከረ መሆኑን በስፍራው የሚገኙት ዶ/ር ለታ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።


ዳጉ_ጆርናል

@Addis_News
@Addis_News