Get Mystery Box with random crypto!

የሟቾች ቁጥር 20 ደረሰ! የመደ ወላቡ መምህራንን ይዞ ሲጓዝ በነበረው ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የ | አዲስ ነገር መረጃ

የሟቾች ቁጥር 20 ደረሰ!

የመደ ወላቡ መምህራንን ይዞ ሲጓዝ በነበረው ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 20 ደረሰ

የመደ ወላቡ መምህራንን ይዞ ሲጓዝ በነበረው ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ እስካሁን ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር 20 መድረሱ ተገለጸ። የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ዛሬ ማለዳ ለማስተማር ወደ ሻሸመኔ ካምፓስ በመጓዝ ላይ እያሉ በደረሰባቸው የትራፊክ አደጋ የ15 መምህራን ሕይወት ማለፉ ተገልጾ ነበር።

ተሸከርካሪው መንገድ ስቶ ወደ ገደል በመግባቱ በተፈጠረው በዚህ አደጋ ሕይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር በአምስት ጨምሮ 20 መድረሱን ኦቢኤን ዘግቧል። ከአደጋው በሕይወት የተረፉት ሌሎች ሰዎች በአደባ፣ ዶዶላ እና ሮቤ ሆስፒታሎች ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ኢብራሂም ከሊል ተናግረዋል።

@Addis_News
@Addis_News