Get Mystery Box with random crypto!

በተሽከርካሪ ታግዘው የሞባይል ስልክ ስርቆት ወንጀል በመፈፀም የተጠረጠሩ 25 ግለሰቦችን በቁጥጥር | አዲስ ነገር መረጃ

በተሽከርካሪ ታግዘው የሞባይል ስልክ ስርቆት ወንጀል በመፈፀም የተጠረጠሩ 25 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ከተጠርጣሪዎቹ 6ቱ ሴቶች ሲሆኑ ግለሰቦቹ “ሿሿ” ብለው በሚጠሩት ወንጀል ከሚያገኙት ገንዘብ በቀን እስከ 35 ሺህ ብር እንደሚቆጥቡ በምርምራ ደርሼበታለሁ ብሏል የአዲስ አበባ ፖሊስ።

ከተጠርጣሪዎቹ እጅ ሁለት ሚኒባስ ታክሲዎች እንዲሁም ለወንጀል ሥራቸው የሚጠቀሙባቸውን 4 ተጨማሪ ተሽከርካሪዎችን መያዙን ፖሊስ ገልጿል።

በተጨማሪም 14 ዘመናዊ ሞባይል ስልኮች እና ገንዘብ ስለመገኘቱም የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያስረዳል።

@Addis_News
@Addis_News