Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ነገር መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_news — አዲስ ነገር መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_news — አዲስ ነገር መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @addis_news
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 76.12K
የሰርጥ መግለጫ

አዲስ ነገር መረጃዎች
መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addisnegermereja_bot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2023-05-17 15:40:56
የኦሮሚያ ብልጽግና አመራር የሆኑት አቶ ታዬ ደንደኣ አዲስ ይገነባል የተባለውን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ቤተ መንግሥት ተቃወሙ

በአዲስ አበባ ከተማ ይገነባል የተባለውን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አዲስ ቤተ መንግሥት ግንባታ የተቃወሙት የኦሮሚያ ብልፅግና አመራሩ አቶ ታየ ደንደአ ናቸው፡፡ አቶ ታዬ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ ‹የሕዝቡ ጥያቄ ቤተ መንግሥት አይደለም› ብለዋል፡፡ 

የአቶ ታየ ደንደአ ተቃውሞ የመጣው የክልሉ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የሚያስገነቡትን ቤተ መንግሥት ሥራማስጀመራቸው ከተነገረ ከሰዓታት በኋላ ነው፡፡ ለኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የሚገነባው ይህ ቤተ መንግሥት ከ6 ሄክታር በላይ ስፋት ባለው ቦታ በቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገነባ መሆኑ ተነግሮለታል፡፡ የቤተ መንግስት ግንባታ ሥራ ማስጀመሪያውም የክልሉ ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት ይፋ ተደርጓል፡፡ 

ነገር ግን የኦሮሚያ ብልፅግና አመራሩ እና የወቅቱ የሠላም ሚኒስቴር ዲኤታው አቶ ታዬ የክልሉ ሕዝብ ጥያቄ ቤተ መንግሥት አለመሆኑን ጠቅሰው፤ ሌሎች ጉዳዮች ቅድሚያ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ አቶ ታዬ የሕዝቡ ጥያቄ የመልካም አስተዳደር፣ የሰላም እና ኢኮኖሚ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በአቶ ሽመልስ የተጀመረውን የቤተ መንግስት ግንባታም ለታማሚ ሰው የተሳሳተ መድሃኒት እንደመስጠት ነው ብለውታል፡፡

@Addis_News
@Addis_News
2.2K views12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 13:13:30
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአዲስ አበባ ለሚያስገነባው "ቤተ- መንግስት" ግንባታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሐ ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ የክልል እና የፌዴራል መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡ቤተ መንግስቱ የኦሮሞን ሕዝብ ወግ፣ ባህል እና ታሪክ በሚያንጸባርቅ መልኩ እንደሚገነባ ተገልጿል፡፡

@Addis_News
@Addis_News
6.1K views10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 13:10:37
እመኑኝ መረጃ ህይወት ነው
ሰበር ና እውን ፣ እጅግ ታማኝ እና ወቅታዊ ድብቅ
ሀገራዊና ክልል አቀፍ የመረጃ  ቻናል ልጠቁማችሁ
ገባ ገባ ብላችሁ መረጃ በየሰዓት አግኙ
ይኸው
https://t.me/+Rq8HblaNUhkySdXf
1.7K views10:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 12:01:18
ለዛሬ ታስቦ የነበረው የአማራ ክልል አመራሮች ስብሰባ ወደ ነገ ሐሙስ ተዘዋውሯል። በስብሰባው ከ1ሺህ 400 በላይ በክልሉ የሚገኙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የሚሳተፉ እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

@Addis_News
@Addis_News
7.3K views09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 11:00:16 በመጋቢት ወር ሀገራዊ አጠቃላይ የፍጆታ እቃዎች የዋጋ ግሽበት 33.7 በመቶ ደርሷል!

የመጋቢት ወር ሀገራዊ አጠቃላይ የፍጆታ እቃዎች ዋጋ ግሽበቱ 33.7 በመቶ መድረሱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታዉቋል። በወሩ የምግብ ነክ ፍጆታዉም 34.5 በመቶኛ መድረሱን ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

በተመሳሳይ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ዋጋ ግብበቱ 32.5 በመቶ ላይ ይገኛል ተብሏል። ግሽበቱ አሁንም በሁለት አኃዝ ቁጥር መገለጹ የዋጋ ንረቱ ጠንካ መሆኑን ያሳያል ብለዋል ሚኒስትር አህመድ ሽዴ። ይህም በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጫና እያሳደረ ይገኛል ብለዋል።

ሚኒስቴሩ ንረቱን ለመቆጣጠር እያከናወነ ያላቸዉን ተግባራት ሚኒስትሩ ዘርዝረዋል። በተያዘዉ አመት በዋነኛነት የአፈር ማዳበሪያ በመጨመሩ ሚኒስቴሩ 17 ቢሊዮን ብር ድጎማ ማድረጉን ገልጸዋል። በተመሳሳይ ሚኒስቴሩ ለክልሎች የአፈር ማዳበሪያ መግዣ 56.7 ቢሊዮን ብር ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋስትና መስጠቱን ገልጸዋል።

በሌላ በኩል የምግብ ነክ ሸቀጦች ዋጋ ንረትን ለማረጋጋት በ 97 ሚሊዮን ዶላር 43 ሚሊዮን ሊትር የፓልም የምግብ ዘይት ለመግዛት ዉል የተገባ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ በ 33.8 ሚሊዮን ዶላር 15 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ወደ ሀገር መግባቱን ሚኒስትሩ ተናግረዋል። በተጨማሪ ዘይት ፣ ሩዝ ፣ ስኳር እና ሌሎች ግብዓቶች በሀገር ዉስጥ ሲመረቱም ሆነ ወደ ሀገር ሲገቡ ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ መደረጉን አክለዋል።

የሀገር ዉስጥ አምራቾችን ለማበረታታትም የማኮሮኒ እና ፓስታ አምራች ተቋማት ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ እንዲሆኑ መደረጉን ገልጸዋል። በዚህም መንግስት ማግኘት የነበረበትን 11.3 ቢሊዮን ብር ገቢ አጥቷል ብለዋል።ሆኖም በአሁኑ ሰዓት በገበያዉ ፓስታ ከ 60 እስከ 70 ብር እንዲሁም ማኮሮኒ በኪሎ እስከ 90 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛል።

[ዳጉ ጆርናል]

@Addis_News
@Addis_News
8.1K views08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 08:57:53
የዴሞክራሲ ኃይሎች ወደ አንድ የመምጫ ጊዜ አሁን ነው!!

ፋሽዝም አቆጥቁጦ የአገር አንድነትና የሕዝብ አንድነት አደጋ እንዲሆን በተቃውሞ ጎራ የምንገኝ የዴሞክራሲ ኃይሎች ራሳችን ተወቃሾች ነን። ለአገዛዙ የጭቆና የድጋፍ ባላ ሆነን በመቆየታችን ዴሞክራሲን አኮስምነናል፤ ከእለት ወደ እለት የጭቆና ኃይሉ ወደለየለት ፋሽስታዊ ደረጃ እንዲያድግ በታሪክ ፊት ድንክ የሚያደርገንን ስህተት ሰርተናል። በዚህም አገርና ሕዝብ በድለናል።

ጥያቄው አሁንስ ከዚህ ስህተታችን ተምረናል ወይ ። የተቃውሞ ጎራው አሁንም ያሉ ውስን አቅሞችን በታትኖ በመንቀሳቀስ የጭቆና ተክል እንዲፋፋ በማዳበሪያነት ይቀጥላል ወይ? የዴሞክራሲ ኃይሎች አሁን ካልተሰባሰብን መቼ ልንሰባሰብ ነው?

ህዝቡ በተለይ የተቃዋሚ ሀይሎች ወደ አንድ መጥተው የአገርን አንድነትና የሕዝብን ደኅንነት እንዲያስጠብቁ በጎ ግፊት ማድረግ ይኖርበታል። በተለያዩ አሰላለፎች ያሉ መዋቅሮች፣ አመራሮችና አባላት በየድርጅቶቻቸው በኩል የዴሞክራሲ ኃይሎች ወደ አንድ መጥተው ለአገርና ሕዝብ በእንደዚህ ያለ ሁነኛ ጊዜ በጠንካራ ቁመና የሚገኝ አማራጭ መሆን እንደሚገባቸው ትግል ሊያደርጉ ይገባል።

ፋሽዝም ሲከስም የኢትዮጵያ ትንሳዔ ይጀምራል!

አቶ ክርሰቲያን ታደለ

@Addis_News
@Addis_News
8.8K views05:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 08:14:33
የኢትዮጵያ ህገ መንግስት "መደበኛ ባልሆነ መንገድ" መሻሻል መጀመሩን ሰላም ሚንስቴር ተናገረ!

የኢትዮጵያ ህገ መንግስት "መደበኛ ባልሆነ መንገድ" መሻሻል መጀመሩን የሰላም ሚንስትር ዴኤታ ስዩም መስፍን (ዶ/ር) ተናግረዋል።

የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ለውጥ ያስፈልገው ይሆን? ከሆነስ የትኞቹ ድንጋጌዎች በሚል የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት ጥናት አካሂዷል።የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት ባደረገው ጥናት ማብሰሪያ ላይ የሰላም ሚንስትር ዴኤታ ስዩም መስፍን (ዶ/ር) ምንም እንኳን ህገ መንግስቱ አልተሻሻለም ይባል እንጂ የተለያዩ አንቀጾች በአዋጅና በትርጉም እንዲሁም በሌላ መንገድ ተሻሽለዋል ብለዋል።

ህገ መንግስቱ በመደበኛም ይሁን በኢ-መደበኛ መንገድ እንደሚሻሻል የጠቀሱት ሚንስትር ዴኤታው፤ ህገ መንግስቱ ሙሉ ሊሆን እንደማይችል ተናግረዋል። የፌዴራሉ አባል ክልሎችን የሚደነግገው አንቀጽ 47 ስለመሻሻሉ ጠቅሰዋል።

የፌዴራልና የክልል የጋራ ገቢዎች የሚወስነው አንቀጽ 58 እንዲሁም መሬት አስተዳደርን የሚደነግገው አንቀጽ 89 እና ሌሎች አንቀጾች መሻሻላቸውን ስዩም መስፍን (ዶ/ር) አንስተዋል።ህገ መንግስቱን በሚመለከት ሦስት አይነት ምልከታዎች አሉ ያሉት ሚንስትር ዴኤታው፤ "ህገ መንግስቱ ረብ የለውም፣ በፍጹም መነካት የለበትም እንዲሁም ሁሉንም ባካተተ መልኩ ይሻሻል" የሚሉ ለየቅል ሀሳቦች መኖሯቸውን ተናግረዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

ሚንስትር ዴኤታው "ጠቃሚው ሀሳብ ሁሉንም ባካተተ መልኩ ይሻሻል" የሚለው እንደሆነ አንስተዋል።ህገ መንግስቱን ማሻሻል እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ያነሱት ስዩም መስፍን (ዶ/ር)፤ የማይሻሻል ከሆነ ጥያቄ የሚያነሱ አካላት ሙሉ በሙሉ በኃይል የመቀየር እንቅስቃሴ እና ፍላጎት ሊያሳዩ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

 @Addis_News
@Addis_News
8.5K views05:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 07:54:46
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህ.ወ.ሓ..ት ህጋዊ ሰውነት የመመለስ ጥያቄ አስመልክቶ በሰጠው ውሳኔ ላይ ከህ.ወ.ሓ.ት የተሰጠ መግለጫ

@Addis_News
@Addis_News
8.1K views04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 07:54:38
7.7K views04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 07:54:38
7.5K views04:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ