Get Mystery Box with random crypto!

የኦሮሚያ ብልጽግና አመራር የሆኑት አቶ ታዬ ደንደኣ አዲስ ይገነባል የተባለውን የኦሮሚያ ክልል ፕሬ | አዲስ ነገር መረጃ

የኦሮሚያ ብልጽግና አመራር የሆኑት አቶ ታዬ ደንደኣ አዲስ ይገነባል የተባለውን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ቤተ መንግሥት ተቃወሙ

በአዲስ አበባ ከተማ ይገነባል የተባለውን የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አዲስ ቤተ መንግሥት ግንባታ የተቃወሙት የኦሮሚያ ብልፅግና አመራሩ አቶ ታየ ደንደአ ናቸው፡፡ አቶ ታዬ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ ‹የሕዝቡ ጥያቄ ቤተ መንግሥት አይደለም› ብለዋል፡፡ 

የአቶ ታየ ደንደአ ተቃውሞ የመጣው የክልሉ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የሚያስገነቡትን ቤተ መንግሥት ሥራማስጀመራቸው ከተነገረ ከሰዓታት በኋላ ነው፡፡ ለኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት የሚገነባው ይህ ቤተ መንግሥት ከ6 ሄክታር በላይ ስፋት ባለው ቦታ በቦሌ ክፍለ ከተማ የሚገነባ መሆኑ ተነግሮለታል፡፡ የቤተ መንግስት ግንባታ ሥራ ማስጀመሪያውም የክልሉ ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በተገኙበት ይፋ ተደርጓል፡፡ 

ነገር ግን የኦሮሚያ ብልፅግና አመራሩ እና የወቅቱ የሠላም ሚኒስቴር ዲኤታው አቶ ታዬ የክልሉ ሕዝብ ጥያቄ ቤተ መንግሥት አለመሆኑን ጠቅሰው፤ ሌሎች ጉዳዮች ቅድሚያ ሊሰጣቸው እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ አቶ ታዬ የሕዝቡ ጥያቄ የመልካም አስተዳደር፣ የሰላም እና ኢኮኖሚ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ በአቶ ሽመልስ የተጀመረውን የቤተ መንግስት ግንባታም ለታማሚ ሰው የተሳሳተ መድሃኒት እንደመስጠት ነው ብለውታል፡፡

@Addis_News
@Addis_News