Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ነገር መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_news — አዲስ ነገር መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_news — አዲስ ነገር መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @addis_news
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 76.16K
የሰርጥ መግለጫ

አዲስ ነገር መረጃዎች
መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addisnegermereja_bot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-06-13 11:18:11 "መንግስት ስልጣን የሰጣቸው የአብን አመራሮች ፓርቲው የተመሰረተበትን ዓላማ በመተው የመንግስት ጉዳይ አስፈፃሚ ሆነዋል" - የአብን ጽ/ቤት ሃላፊ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የጽህፈት ቤት ሃላፊ ቴዎድሮስ ሀይለማርያም (ዶ/ር) "መንግስት ስልጣን የሰጣቸው የአብን አመራሮች ፓርቲው የተመሰረተበትን ዓላማ በመተው የመንግስት ጉዳይ አስፈፃሚ ሆነዋል" ሲሉ ለአሻም ተናግረዋል።

በአማራ ክልል መንግስትና በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መካከል እየተደረጉ ያሉ ግንኙነቶችን አስመልክቶ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አመራሮች ለሁለት መከፈላቸውን ሃላፊው ይፋ አድርገዋል።

ሀላፊው እንደሚሉት የሁለቱ አካላት ግንኙነት ሰላም እስካመጣ ድረስ መልካም ነው የሚሉ አመራሮች አሉ በአንፃሩ  ደግሞ ተጠያቂነት ሳይኖር ጦርነቱን በበላይነት ሲመሩ የነበሩ አካላት የሚያደርጉት ውይይት አግባብ አይደለም የሚሉ መኖራቸውን ነግረውናል፡፡

እንደ እርሳቸው አገላለፅ "ይህ መከፋፈል የመጣውም በመንግስት ሹመት ተደልለው የመንግስት ስራ አስፈፃሚ የሆኑ የንቅናቄው አመራሮች በመኖራቸው ነው፡፡" ሲሉ ተችተዋል።

ግማሹ የፓርቲው ስራ አስፈፃሚ በመንግስት ካቢኔ ውስጥ ተቀምጠው የአማራ ህዝብን ሳይሆን የገዢውን ብልፅግና ፓርቲ ጉዳይ አስፈፃሚ ሆነዋል የሚሉት ቴዎድሮስ "በአማራ ህዝብ ላይ ይህ ሁሉ በደል ሲፈፀምበት ንቅናቄው ከተመሰረተበት ዓላማ ውጭ የመንግስትን ጉዳይ በማስፈፀም የአማራ ህዝብን የሚታገል ድርጅት ሆኗል" ሲሉም አክለዋል።

ሃላፊው  መፍትሔ ብለው በማስቀመጡት ሃሳብም "አብን ይህን ጉዳይ አስታርቆ  ሊቀጥል የሚችለው በመንግስት ስልጣን ውስጥ ያሉ ሰዎች ከስልጣናቸው ሲለቁ አልያም ፓርቲውን መልቀቅ ሲችሉ ብቻ ነው" ሲሉም ገልፀዋል፡፡

ሀላፊው አክለውም "ለአማራ ህዝብ እታገላለሁ እያሉ ለሕዝቡ ጠላት የሆነው መንግስትም አካል ነኝ ማለት ሊሆን አይችልም፤ ምን አልባትም ድርጅቱ ጉባኤውን ካካሄደ እነዚህን ሰዎች ምርጫቸውን ይሰጣቸዋል" ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

Via Asham

@Addis_News
@Addis_News
3.3K views08:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 10:57:50 በጉጂ ዞን በኦሮሞ እና በሲዳማ ብሔር ተወላጆች መካከል በተፈጠረ ግጭት በሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደረሰ

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን እና በሲዳማ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች በተፈጠረ ግጭት ከፍተኛ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገለጸ፡፡

በኹለቱ ብሔር ተወላጆች መካከል የቆየ የድንበር ይገባኛል ክርክር መኖሩን እና ይህንም ተከትሎ በተለያዩ ጊዜያት ግጭት እና አለመግባባት እንደሚፈጠር በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች ተናግረዋል ፡፡

ለአብነትም ሐሙስ ሰኔ 01/2015 ግጭት ተፈጥሮ በኹለቱም ብሔር ተወላጆች ላይ ከፍተኛ የአካል ጉዳት መደረሱን ነው ነዋሪዎቹ የገለጹት።

አክለውም፤ በሲዳማ እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ቦታዎች በተለይም ጌዴኦ፣ ከማኒ፣ ገደብ እና ገርበማ በተሰኙ ሥፍራዎች በተደጋጋሚ ግጭት እንደሚከሰት እና በዚህ ሳቢያም ከኹለቱም ወገን ሰዎች ለአካል ጉዳት እንደሚዳረጉ አስረድተዋል፡፡

በተለይም ሐሙስ ሰኔ 01/2015 በጉጂ ዞን ቦሬ ሱኬ በተሰኘ ሥፍራ በሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች እና አገረ ሰላም በተሰኘ ስፍራ በሚኖሩ የሲዳማ ተወላጆች መካከል በድንበር አቅራቢያ በተቀሰቀሰ ግጭት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች መጎዳታቸው ተነግሯል።

መሰል ችግሮች በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ቢሆንም፤ በኹለቱም ክልሎች መንግሥታት በኩል የተወሰደ የመፍትሄ እርምጃ ባለመኖሩ በሰውና በንብረተ ላይ ጉዳት እየደረሰ ነው ተብሏል።

የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልሽ ቶማስ “የብሔር ግጭት ተፈጥሯል የሚባለው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው፡፡” ሲሉ ጠቅሰው፤ “ግለሠብ ከግለሠብ ከተጋጨም ሰዎች ለራሳቸው ፖለቲካዊ ትርፍ  ሲሉ አጋነው ያወራሉ፡፡” ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም፤ ከዚህ ቀደም በሲዳማ ክልል ሥር በሚገኘው ወንዶ ገነት ወረዳ ኤዶ የምትባል ቀበሌ በሕዝበ ወሳኔ ወደ ክልሉ ከተካለለች በኋላ፤ አገራዊ ምክክር በሚደረግበት ወቅት ቁጥራቸው ሦስት የሚሆኑ የሲዳማ ክልል ተወላጆች “እኛን የማይወክሉ የጉጂ ኦሮሞ ተወላጆች ተመርጠዋል እኛ በምርጫው ውስጥ አልተካተትንም፡፡” በማለት ረብሻ ፈጥረው እንደነበር አውስተዋል።

ኮሚሽነሩ በመጨረሻም “ከእኛ አቅም በላይ የሆነ ችግር በክልላችን አልተፈጠረም፡፡” ሲሉ ተደምጠዋል።  

@Addis_News
@Addis_News
3.8K views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 10:35:17
የትግራይ ቤተ ክህነት ኢትዮጵያ የሚለውን ስያሜ ከስሙ ውስጥ ሠረዘ!

"በትግራይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሚለው ስም ሙሉ በሙሉ ተቀይሮ የትግራይ መንበረ ሰላማ" መባሉን አባ ሠረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል ለዛራ ሚዲያ ገለጹ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጿል።

@Addis_News
@Addis_News
4.3K views07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 10:33:49
የትዳር እና የወንድ ልጅ ችግር የሆነውን የስንፈተ ወሲብ እንዲሁም የብልት ቁመት ማነስን በዘላቂነት ችግሩን የሚፈታ ORGINAL EUROPE STANDARD መዳኒቶች እኛ ጋር አሉ
   MAXMAN TITAN_GEL VIMAX
የብልት መጠንን በዘላቂ ሁኔታ ለመጨመር
በግንኙነት ወቅት ቶሎ ላለመርጨት
የተሻለ የወሲብ ፍላጎት አና ችሎታ የሚጨምር
ብልት ውጥር እና ቀጥ ብሎ እንዲቆይ
  % ኦሪጂናል (noside effect )
  % ተፈጥሮዊ (herbal)
                         +251907270050
                         +251907270050
እንዲሁም ኅርባል ክብደት መጨመሪያ አለ ይደውሉ
አ.አ ላላችሁትም በእራሳችን transport  ያሉበት ድረስ በ 30 ደቂቃ እናደርሳለን
ወደ ክልል ከተሞች በፖስታ ቤት እንልካለን
ለተጨማሪ መረጃ
https://t.me/TWAKELpharmacy
https://t.me/andehabsha
4.2K views07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 09:39:30 በባቱ (ዝዋይ) ከተማ በመንግሥት የጸጥታ አካላትና በ"ሸኔ" ታጣቂዎች መካከል በተደረገ የተኩስ  ልውውጥ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተሰማ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ባቱ (ዝዋይ) ከተማ እሁድ ሰኔ 4/2015 ዕለት ከሌሊቱ አምስት ሰዓት አካባቢ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች እና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራውና በመንግሥት ኦነግ ሸኔ ተብሎ በአሸባሪነት በተፈረጀው ታጣቂ ቡድን መካከል በተደረገ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ የአራት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

ከሟቾቹ መካከል አንዲት ሴትን ጨምሮ ሦስቱ የመንግሥት የጸጥታ አካላት መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፤ አንዱ ደግሞ ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን አባል ነው ተብሏል።

የተገደለው የሸኔ ታጣቂ ቡድን አባል እግሩን ተመትቶ መሸሽ ባለመቻሉ፤ የታጣቂ ቡድኑ አባላት መረጃ እንዳያወጣ በማለት ገድለውት እንደሸሹ ተጠቁሟል።

ለተከታታይ ኹለት ሰዓታት በላይ ሲደረግ ነበር የተባለው የተኩስ ልውውጥ፤ ዓላማው እስረኛ ለማስፈታት እንደሆነ ተገልጿል።

እስር ቤቱ በተለምዶ ሀይቅ ዳር ወይም የቀድሞ ጤና ጣቢያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ እንደሚገኝ እና ታጣቂዎቹ ከዚህ ቀደምም በእስር ቤቱ የታሰረባቸውን አባል ለማስፈታት ጥረት ሲያደረጉ የሰዎች ሕይወት ማለፉን ነዋሪዎቹ አውስተዋል።

የሸኔ ታጣቂ ቡድን አባላት ቡልቡላ እና ቱሉ መካከል በተለምዶ ኦኢቱ በምትባል ስፍራ መሽገው እንደሚገኙ የገለጹት ነዋሪዎቹ፤ እስረኞቻቸውን ለማስፈታትም የዝዋይን ሀይቅ በጀልባ እየቀዘፉ መጥተው ጀልባቸውን ጦጣ ወንዝ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ እንዳቆሙ አብራርተዋል፡፡

አክለውም፤ እሁድ ሌሊት በተካሄድው የተኩስ ልውውጥ የታሰሩ የታጣቂ ቡድኑን አባላት ለማስፈታት የተደረገው መኩራ አለመሳካቱን በመጥቀስ፤ "የታጣቂ ቡድኑ አባላት አሉ ወደተባለበት ኦኢቱ አካባቢ የመንግሥት የጸጥታ አካላት በተደጋጋሚ ቢያቀኑም በሕይወት ተርፈው የሚመለሱት ጥቂቶች ናቸው።" ሲሉም ተደምጠዋል።

ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው እና በመንግሥት ኦነግ ሸኔ ተብሎ በአሸባሪነት የተፈረጀው ታጣቂ ቡድን በአካባው መንቀሳቀስ ከጀመረ ቆይቷል የተባለ ሲሆን፤ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ከባድ ቀውስ እያሳደረ እንደሚገኝም ተመላክቷል።

@Addis_News
@Addis_News
5.5K views06:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 09:19:44
የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ አባላት ክልል ተቀያይረው ውይይት እያካሄዱ ነው

ከሰሞኑ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የመከረው የገዥው ፓርቲ ብልጽግና ማዕከላዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ክልል ተቀያይረው ክልል አቀፍ የአመራር ውይይት ማካሄድ ጀምረዋል፡፡

ውይይቱን የሚመሩት የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባላት ሲሆኑ፤ የክልል አመራሮች ውይይቱ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ያስቀመጠውን አቅጣጫ በየደረጃው ለሚገኙ የክልል አመራሮች ለማስረጽ ያለመ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ወደ ሀዋሳ ተጉዘው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልልን የአመራሮች ወይይት እየመሩ ነው፡፡ በአንጻሩ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳደር ርስቱ ይርዳው ወደ ባህር ዳር ተጉዘው የአማራ ክልል አመራሮችን ውይይት እየመሩ ነው፡፡

የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ኡመር የሲዳማ ክልል የአመራሮች ውይይትን እየመሩ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት ውይይት ያልጀመሩ ክልሎች እንደሚጀመሩም ታውቋል።

@Addis_News
@Addis_News
5.5K views06:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 09:18:36 GERMANY WORK VISA 2023   
---—-----------------------      Congragulation For Ethiopian

ከ 20,000- በላይ ክፍት ቦታዎች በ0 አመት እና በልምድ

Number of Positions: 20,000+ positions 0 EXP and with Exp

በተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች የወጣ የስራ ማስታወቂያ

Germany
0 Year Experiance And Experianced
2 Years Contrat
Quantity 20,000+
Salary:  Based On Profation
Full Sponsership By Campony


ፈጥነው ታች ባለው ሊንክ ይመዝገቡ

Apply Now
https://addiszemenvacancy.com/2023/06/04/germany-campony-jobs-2023/


----------Follow Our Website------
                           
         https://addiszemenvacancy.com

----------Join Our Telegram-------
                              
     https://t.me/Addis_Zemen_Vacancy
5.4K views06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 07:47:31 የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የምግብ እርዳታን ላልተፈለገ ዓላማ በማዋል ተሳትፏል መባሉን ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ አጣጥሏል።

በምግብ እርዳታ ዝርፊያና ለራስ ጥቅም በማዋል የተሳተፉ የሠራዊቱ ክፍሎች ወይም ተቋማት የሉም በማለት የገለጠው መግለጫው፣ ሠራዊቱ ከተረጅዎች እርዳታ ሊነጥቅ ይቅርና ለእርዳታ ፈላጊዎች እርዳታ ለመስጠት በቂ የሎጂስቲክስ አቅርቦት ያለው ተቋም ነው ብሏል። ሠራዊቱ፣ በድርጊቱ በግለሰብ ደረጃ ተሳትፈው የተገኙ አባላቱ ካሉ ግን ርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።

ሠራዊቱ ይህንኑ መግለጫ ያወጣው፣ የአሜሪካው ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት በውስጥ ምርመራው በኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ ወታደሮችንና የቀድሞ ተዋጊዎችን ለመመገብ እንደዋለ ደርሶበታል የሚል ሪፖርት መውጣቱን ተከትሎ ነው።

@Addis_News
@Addis_News
7.0K views04:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 07:46:46
መርጌታ መንግስቱ የባህል ህክምና የምንሰጣቸዉ የጥበብ  አገልግሎቶች
ለሀብት 0963401703
ለገበያ
ለወሲብ ስንፈት
ለመስተፋቅር
ለቁማር
ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
ለዓቃቤ ርዕስ
ለመክስት
ቡዳ ለበላው
ሰላቢ የማያስጠጋ
ለመፍትሔ ሀብት
ለመፍትሄ ስራይ
ለሁሉ ሠናይ
ለህማም
ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
ለመድፍነ ፀር
ሌባ የማያስነካ
ለበረከት
ለግርማ ሞገስ
ለዓይነ ጥላ
ለሁሉ መስተፋቅር
ጸሎተ ዕለታት
ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
ለድምፅ
ጋኒን ለያዘው

ለጥያቄዎ 0963401703
7.0K viewsedited  04:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 21:47:56 የችሎት ዜና!

ጋዜጠኞቹ መስከረም አበራና ጎበዜ ሲሳይን ጨምሮ በእነ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ መዝገብ የተከሰሱ ተጠርጣሪዎች ችሎት ለህዝብ ክፍት እንዲደረግ ታዘዘ

በአማራ ክልል ከልዩ ሀይል መፍረስና ፋኖን ትጥቅ ማስፈታት ጋር ተያይዞ በሽብር ወንጀል ተጠርጥረዋል ተብለው ለእስር የተዳረጉ በአማራ ጉዳይ ላይ የሚሰሩ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞችና ምሁራን ዛሬ ሰኔ 5/2015 ዓ/ም ከሰዓት በኋላ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበዋል።ችሎቱ ለዛሬ ተቀጥሮ የነበረው አቃቤ ህግ በእያንዳንዳቸው ተከሳሾች ላይ በሬጅስትራር በኩል የተረጋገጠ ክስ እንዲያቀርብ ነበር።

ሆኖም አቃቤ ህግ የተረጋገጠ ክስ ለሬጅስትራር ሰጥቻለሁ ቢልም ሬጅስትራር ግን ሊደርስልኝ የቻለው የ13 ተከሳሽ ክስ ብቻ ነው የሚል ምላሽ ሰጥቷል።በዚህም አቃቤ ህግ ባሉበትና በሌሉበት በሚል ክስ ከመሰረተባቸው 51 ተጠርጣሪዎች መካከል ለአስራ ሶስቱ የክስ ቻርጅ እንደተሰጣቸው ሮሃ ቲቪ በችሎት ተገኝታ ተከታትላለች።
በዚህ ላይ አስተያየት የሰጡት የተከሳሽ ጠበቆችም " የአስራ ሶስቱ ተከሳሾች ጉዳይ መታየት ይችላል ችግር የለብንም " ብለዋል።

ለችሎቱ የሰብዓዊ መብት አያያዛቸውን በተመለከተ ለችሎቱ አስተያየት የሰጡት ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይ አውግቸው በበኩላቸው " ዶክመንተሪ ተሰርቶብን ስማችን የጠፋ የፖለቲካ እስረኞች ስለሆንን  ችሎቱ ለቤተሰቦቻችን በተለይም ለአማራ ህዝብ ክፍት ተደርጎ በሰፊ አዳራሽ እንዲታይልን" ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል።ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በበኩሉ "ሌላ ቦታ የተሰደብነውና የተደበደብነው  ሳያንስ በችሎት አዳራሽ ፊት በፖሊሶች እንሰደባለን፣ ከጠበቆቻችን ጋር እንዳናወራ እንደረጋለን" ብሏል።

ዶ/ር መሰረት ቀለመወርቅ ደግሞ "የደረሰብንን የሰብዓዊ መብት ጥሰት አቅርበን ነበር አሁን ግን የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ወደ መደበኛ ችሎት ስለተቀየረ ምን ላይ እንዳለ አናውቅም ፣ ከምን እንደደረሰ ግልፅ ይደረግልን" ሲሉ ጠይቀዋል።47ኛ ተከሳሽ ማስረሻ እንየው " በህግ ማስከበር ዘመቻው ወቅት ሰውነቴ ውስጥ የቀረ ጥይት አለ ፣እንዳልታከም ተደርጌያለሁ ፣በቀጠሮዬ ቀንም ህክምና እንዳልቀርብ ተደረወጌያለሁ፣ በዚህም ለ75 ቀናት ገላዬን እንኳን መታጠብ አልቻልኩም " ብሏል ለችሎቱ።

ችሎቱም ረዳት ፕሮፌሰር ሲሳይና ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው ላቀረቡት "ጉዳያችን በክፍት አዳራሽ ይታይ" ጥያቄ በሰጠው ምላሽ በቀጣይ ጉዳያቸው በትልቅ አዳራሽ እንዲታይና ለህዝብ ክፍት እንዲሆን አዟል።በጊዜ ቀጠሮ መዝገብ በኢሰመኮ  እንዲጣሩ ውሳኔ የተሰጠባቸውን መዝገቦች እኛ እናጣራለን ብሏል የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት መደበኛ ችሎት።

ዶክመንተሪ ሰርተው ተጠርጣሪዎቹ በህግ ፊት ነፃ ሆኖ የመታየት መብታቸውን ያሳጡ የተባሉት የመንግስት ሚዲያዎች በስም የተጠሩ ሲሆን ፣ ይህንንም ጉዳይ እንደሚያጣራ ነው  ችሎቱ ያሳወቀው።አቃቤ ህግ ግን "ዶክመንተሪ የሰራው የጋራ ግብረሃይሉ ነው እኔን አይመለከተኝም" ብሏል።

"ለአስራ ሶስቱ ተከሳሾች የቀረበው ክስና የሰነድ ማስረጃን በተመለከተ  ሃላፊነቱን የወሰደው አቃቤ ህግ ስምና ፊርማ የለም ፣ሃላፊነት የሚወስድ አካል ያስፈልጋል " ሲሉም የተከሳሽ ጠበቆች ጠይቀዋል።
አቃቤ ህግም" ሃላፊነቱን የሚወስደው ፍትህ ሚኒስቴር ነው ፣ የፍትህ ሚኒስቴር ማህተም እስካለ ድረስ ሃላፊነቱን የሚወስደው ተቋሙ ነው "የሚል ምላሽ ሰጥቷል።የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዚህና በሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ዙሪያ በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ብይን ለመስጠት ለሰኔ 9/2015 ቀጠሮ ሰጥቷል።

      (ሮሃ ሚዲያ )
@Addis_News
@Addis_News
10.9K views18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ