Get Mystery Box with random crypto!

የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ አባላት ክልል ተቀያይረው ውይይት እያካሄዱ ነው ከሰሞኑ በወቅታዊ ጉዳዮች | አዲስ ነገር መረጃ

የብልጽግና ሥራ አስፈጻሚ አባላት ክልል ተቀያይረው ውይይት እያካሄዱ ነው

ከሰሞኑ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የመከረው የገዥው ፓርቲ ብልጽግና ማዕከላዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ክልል ተቀያይረው ክልል አቀፍ የአመራር ውይይት ማካሄድ ጀምረዋል፡፡

ውይይቱን የሚመሩት የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባላት ሲሆኑ፤ የክልል አመራሮች ውይይቱ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ያስቀመጠውን አቅጣጫ በየደረጃው ለሚገኙ የክልል አመራሮች ለማስረጽ ያለመ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባል የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ወደ ሀዋሳ ተጉዘው የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልልን የአመራሮች ወይይት እየመሩ ነው፡፡ በአንጻሩ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳደር ርስቱ ይርዳው ወደ ባህር ዳር ተጉዘው የአማራ ክልል አመራሮችን ውይይት እየመሩ ነው፡፡

የሱማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ኡመር የሲዳማ ክልል የአመራሮች ውይይትን እየመሩ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት ውይይት ያልጀመሩ ክልሎች እንደሚጀመሩም ታውቋል።

@Addis_News
@Addis_News