Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ነገር መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_news — አዲስ ነገር መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_news — አዲስ ነገር መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @addis_news
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 76.16K
የሰርጥ መግለጫ

አዲስ ነገር መረጃዎች
መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addisnegermereja_bot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-10-07 14:45:12
ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ

የምንሰጣቸው የማስታወቂያ አገልግሎቶች

➠ የ ሙዚቃ ማስታወቂያ
➠ የ ኮንሰርት ማስታወቂያ
➠ የ ድርጅት ማስታወቂያ
➠ የ ዩቲዩብ ቻናል ማስታወቂያ
➠ ትሪትመንቶች እና ሌሎችም ሽያጮች ማስታወቂያ

የትምህርት ተቋማት…...
የህክምና ማዕከላት (ባህላዊ /ዘመናዊ)…...
የትራንስፖርት አገልግሎት…....
የስራ አገናኝ ኤጀንሲዎች……
ሆቴል፣ካፌና ሬስቶራንቶች......
➲ እንዲሁም የተለያዩ የ Business ስራወችን ከእኛ ጋ መስራት ለምትፈልጉ አናግሩን

ምርትና አገልግሎቶን በተመጣጣኝ ዋጋ ለ 71 ሺህ በላይ ኢትዮጲያዊያን ተደራሽ በማድረግ በእጥፍ ያትርፉ።


አሁኑኑ ያናግሩን

ለማናገር
• @nik_moon
13.3K views11:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-07 12:20:15 በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የታደሙበት የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል የገዳ ስርአቱን በጠበቀ መልኩ በሰላም መከበሩን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ፡፡

አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ከተለያዩ የሀገሪቱና ከጎረቤት ሀገራት የመጡ እንግዶች እና ቱሪስቶች የታደሙበት የ2016 ሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በሰላም እና በልዩ ድምቀት መከበሩን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል፡፡

የበዓሉ በሰላም መከበር የሀገሪቱን መልካም ገፅታ ለመገንባት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ግብረ-ኃይሉ አስታውሶ ለበዓሉ በሠላም መከበር የድርሻቸውን ለተወጡ ሁሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡

@Addis_News
12.7K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-26 19:54:50
ግለሰቦቹ ወደ ማረሚያ ቤት ወርደዋል

የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማቅረብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምቦ ዲስትሪክት የስራ ቅጥር ፈጽመዋል የተባሉ ግለሰቦች ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ አዘዘ።

የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ተከሳሾቹ የሙስና አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ድንጋጌን ተላልፈዋል በማለት ሀሰተኛ መንግስታዊ ወይም ህዝባዊ ሰነዶችን አዘጋጅቶ በመጠቀም የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።

ተከሳሾቹ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምቦ ዲስትሪክት በወጣ የስራ ማስታወቂያ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ በማቅረብ የስራ ቅጥር ውል ስምምነት መፈጸማቸው በክሱ ተጠቅሷል።

ተከሳሾቹ 12 ሲሆኑ 10 ሩ የቅጥር ውል ከፈጸሙ በኋላ ለ10 ወራት በየደረጃው በተለያየ መጠን ወርኃዊ ደመወዝ መውሰዳቸውን ነው  ዐቃቤ ሕግ በክሱ ያመላከተው።

ቀሪዎቹ ሁለት ተከሳሾች ደግሞ የስራ ቅጥር ውል ስምምነት ከፈጸሙ በኋላ  የማስረጃ ማጣራት ስራ ሲጀመር መሰወራቸውን ነው ዐቃቤ ሕግ በክሱ ያመላከተው።

በዚህም ዐቃቤ ሕግ ያቀረበባቸው ሀሰተኛ መንግስታዊ ወይም ህዝባዊ ሰነዶችን አዘጋጅቶ መጠቀም የሙስና ወንጀል ክስ ዝርዝር ለ 10 ግለሰቦች በችሎት እንዲደርሳቸው ተደርጓል።

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተረኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ በነበረው ቀጠሮ በችሎት የቀረቡት 10 ተከሳሾች ማረሚያ ቤት እንዲወርዱና ቀሪ ሁለት ተከሳሾችን ደግሞ የኦሮሚያ ፖሊስ አፈላልጎ በቀጣይ ቀጠሮ እንዲያቀርባቸው አዟል።

የተከሳሾችን የዕምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ለጥቅምት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ መያዙም ተገልጿል፡፡
(ታሪክ አዱኛ)

@Addis_News
12.9K viewsedited  16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-26 12:21:09 በመቀሌ የሚገኙ ጋዜጠኞች በደረሰባቸው ከፍተኛ ድብደባ ክፉኛ መጎዳታቸውን ገለጹ


በትግራይ ክልል የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባለፈው ጳጉሜ ወር በመቀሌ ከተማ ጠርተውት ከነበረው ሰልፍ ጋር ተያይዞ፤ ለዘገባ በሥፍራው የተገኙ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች በደረሰባቸው ከፍተኛ ድብደባ ክፉኛ መጎዳታቸውን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

በሥፍራው ከተገኙት ጋዜጠኞች መካከል በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር እና ከያበላ ሚዲያ መስራቾች አንዱ መሆናቸውን የገለጹት ተሻገር ፅጋብ፤ “ሰልፉ ይደረግበታል ወደተባለው ሮማናት አደባባይ በማቅናት በእጅ ስልኬ የተወሰነ ተንቀሳቃሽ ምስል ለመያዝ ስሞክር “ቲዲኤፍ” ተብለው የሚጠሩ ኃይሎች ስልኬን ተቀብለው በያዙት ዱላ በመምታት ከጥቅም ውጪ አድርገውታል፡፡” ብለዋል።

አክለውም “በደረሰብኝ ከፍተኛ ድብደባ ራሴን ስቼ ወድቄ ነበር፡፡” ያሉት ተሻገር፤ “ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ሰሜን ክፍለ ከተማ ወደሚገኘው እስር ቤት ወሰዱኝ፡፡” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

“እስር ቤት ከገባሁ በኋላም ወደ ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል ሪፈር የተጻፈልኝ ቢሆንም፤ ‘የጥበቃ ኃይል የለንም’ በማለት ፈቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ከፍተኛ የሆነ ደም ፈሶኛል፡፡” ብለዋል።

እስር ቤት ውስጥ በተፈጸመባቸው ከፍተኛ ድብደባም ዓይናቸው፣ ጭንቅላታቸው እንዲሁም እጅና እግራቸው ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን ገልጸው፤ ሕክምና እየተከታተሉ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በአያም ሚዲያ ጋዜጠኛ የሆነው መሐሪ ሰሎሞን በበኩሉ፤ ተመሳሳይ ጥቃት እንደደረሰበት በመናገር “በሌሎች እስረኞች ላይም የሚፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከፍተኛ ነው፡፡” ብሏል።

በሰዓቱ በሌሎች ጋዜጠኞች ላይም ድብደባ እና ማዋከብ ሲፈጸም ማየቱን አውስቷል።

የደረሰባቸውን አካላዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳት አስመልክቶም በሕግ ለመጠየቅ በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ጋዜጠኞቹ ጠቁመዋል።

ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ጥብቃ ተሟጋች ኮሚቴ ሲፒጄ በትግራይ የተቃውሞ ሰልፍ ሊዘግቡ የወጡ ሶስት ጋዜጠኞችን ፖሊሶች ደብድበው አስረዋል ሲል ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ሲፒጄ በመግለጫው “መለዮ የለበሱ ፖሊሶች አስቁመው በዱላ እና በኮረንቲ ገመድ እንደመቷቸው ጋዜጠኞቹ ገልጸውልኛል” ያለ ሲሆን፤ “በጋዜጠኞቹ ላይ የደረሰው ድብደባ በትግራይ ያሉ ባለስልጣናት ሪፖርተሮች መንግሥትን የሚተቹ ጉዳዮችን እንዲዘግቡ እንደማይፈልጉ አሳዛኝ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው፡፡” ሲል ገልጿል፡፡

@Addis_News
13.4K views09:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-24 13:52:40
የሀድያ ብሄር የዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓል በደማቅ ስነ ስርዓት በመከበር ላይ ይገኛል።

ፎቶ: የሀድያ ዞን ኮሚኒኬሽን ቢሮ
#ዳጉ_ጆርናል
@Addis_News
12.9K views10:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-24 11:25:38 ጎንደር!

በአሁኑ ሰአት በጎንደር ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ሲሆን ከተማዋም በአደገኛ መሳርያ እና በከፍተኛ ተኩስ እየተናጠች ነው።

@Addis_News
12.9K views08:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-09-24 08:42:15
ፎቶ፣ 70 የሚጠጉ ደሴቶች በህዳሴ ግድብ ላይ!

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ የቱሪዝም መዳረሻ ልማት አቅም ያላቸው ወደ 70 የሚጠጉ ደሴቶች መገኛ ሆኗል።

@Addis_News
12.7K viewsedited  05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 12:13:00
የሱዳን ግጭት ወደ እርስበእርስ ግጭት ሊያመራ እንደሚችል የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ገለጹ

የሱዳን ጦርነት የማይቆም ከሆነ የእርስበእርስ ግጭት እና ትርምስ እንደሚያስከትል የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ገልጸዋል።

ጦርነቱ በሱዳን ህልውና ላይ አደጋ መደቀኑን ሊቀመንበሩ ተናግረዋል።

የአፍሪካ ህብረት ግጭት እንዲቆም እና ተፋላሚ ወገኖች ወደ ንግግር እንዲገቡ ጥረት እያደረገ ነው ብለዋል ሊቀመንበሩ።

ጦርነቱ ከተጀመረ 9ኛ ሳምንቱን ይዟል።(አልአይን)

@Addis_News
@Addis_News
1.4K views09:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 12:11:39
ማስታወቂያ
መኪና በተመጣጣኝ ዋጋ
መኪና ለመግዛት ካሰቡ ብዙ አማራጭ እኛ ጋር ያገኛሉ እንዲሁም ለዘመናዊ መኪና ፈላጊዎች ስለሚገዙት መኪና እናማክራለን!!!
  በባንክ ብድር አዲስ መኪና መግዛት ምትፈልጉ ደንበኞቻችን 50% ብድር በ15.5 ወለድ ለ5 አመት የሚከፈል እናመቻቻለን
ከስር ባለው ሊንክ የቴሌግራም ቻናላችንን Join በማለት ስለመኪና ወቅታዊ ዋጋ እና መረጃ ያግኙ
https://t.me/AbrahamDealer
https://t.me/AbrahamDealer
ስልክ
+251939842424
+251992229292
1.4K views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 11:22:57
በሀዋሳ የቀጠለው አፈናና ጠለፋ!!

ከጉጂ ጦርነትን ሸሽተን ብንመጣም በሀዋሳ ልጃችን ተወሰደችብን!

በትላንትናው እለት ከቀኑ6:40 ሰዓት አካባቢ የ14 ዓመቷ ታዳጊ የ8ተኛ ክፍል ተማሪ ሜላት መሐመድ ከምትማርበት ሀዋሳ ጉዱማሌ ት/ቤት ወጣች።

የትምህርት ቤት ጓደኞቿን ተሰናብታ፣ የአስፓልቱን መንገድ ታጥፋ ወደ ቤት አመራች። ቤቷ ልትገባ የተወሰኑ ሜትሮች ሲቀራት፥ ሞኖፖል ሠፈር ጋር በሁለት ዳማስ መኪና ሆነው አድፍጠዉ የሚጠብቋት ያልታወቁ ሰዎች አፈኗት። ከነለበሰችው ዩኒፎርምና ከያዘችው ደብተር ጋር ጠለፏት።

አካባቢው ላይ የነበሩ የዓይን እማኞች እርዳታ የምትሻ፤ የምትጮህ ልጅ በተመለከቱ ጊዜ መኪናዎቹ ላይ ድንጋይ በመወርወርና በመከተል ለማስጣል ቢሞክሩም አልቻሉም። መንገደኞች፥ ልጅቷን ተሽክመው ያስገቧት ዳማስ መኪና ለማስቆም ድንጋይ ወረወሩ። የግምባር መስታወቱን አገኙት።ግን ታዳጊዋን ይዘው ጠፉ።

ታዳጊዋ ሜላት በቅርቡ የስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ተፈታኝ ናት።እየጮኸችና እያለቀሰች አፍነው ይዘዋት ሄዱ።

* ታርጋ ቁጥር 01894ሲ.ዳ ና
* 05274ሲ.ዳ ነው

"#ሜላት የት ናት"
* 0911377698- እንዳልካቸው
* 0911377923- ምኞት

@Addis_News
@Addis_News
3.3K views08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ