Get Mystery Box with random crypto!

በሀዋሳ የቀጠለው አፈናና ጠለፋ!! ከጉጂ ጦርነትን ሸሽተን ብንመጣም በሀዋሳ ልጃችን ተወሰደችብን! | አዲስ ነገር መረጃ

በሀዋሳ የቀጠለው አፈናና ጠለፋ!!

ከጉጂ ጦርነትን ሸሽተን ብንመጣም በሀዋሳ ልጃችን ተወሰደችብን!

በትላንትናው እለት ከቀኑ6:40 ሰዓት አካባቢ የ14 ዓመቷ ታዳጊ የ8ተኛ ክፍል ተማሪ ሜላት መሐመድ ከምትማርበት ሀዋሳ ጉዱማሌ ት/ቤት ወጣች።

የትምህርት ቤት ጓደኞቿን ተሰናብታ፣ የአስፓልቱን መንገድ ታጥፋ ወደ ቤት አመራች። ቤቷ ልትገባ የተወሰኑ ሜትሮች ሲቀራት፥ ሞኖፖል ሠፈር ጋር በሁለት ዳማስ መኪና ሆነው አድፍጠዉ የሚጠብቋት ያልታወቁ ሰዎች አፈኗት። ከነለበሰችው ዩኒፎርምና ከያዘችው ደብተር ጋር ጠለፏት።

አካባቢው ላይ የነበሩ የዓይን እማኞች እርዳታ የምትሻ፤ የምትጮህ ልጅ በተመለከቱ ጊዜ መኪናዎቹ ላይ ድንጋይ በመወርወርና በመከተል ለማስጣል ቢሞክሩም አልቻሉም። መንገደኞች፥ ልጅቷን ተሽክመው ያስገቧት ዳማስ መኪና ለማስቆም ድንጋይ ወረወሩ። የግምባር መስታወቱን አገኙት።ግን ታዳጊዋን ይዘው ጠፉ።

ታዳጊዋ ሜላት በቅርቡ የስምንተኛ ክፍል ሚኒስትሪ ተፈታኝ ናት።እየጮኸችና እያለቀሰች አፍነው ይዘዋት ሄዱ።

* ታርጋ ቁጥር 01894ሲ.ዳ ና
* 05274ሲ.ዳ ነው

"#ሜላት የት ናት"
* 0911377698- እንዳልካቸው
* 0911377923- ምኞት

@Addis_News
@Addis_News