Get Mystery Box with random crypto!

ግለሰቦቹ ወደ ማረሚያ ቤት ወርደዋል የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ሀሰተኛ የ | አዲስ ነገር መረጃ

ግለሰቦቹ ወደ ማረሚያ ቤት ወርደዋል

የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወንጀል ችሎት ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ በማቅረብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምቦ ዲስትሪክት የስራ ቅጥር ፈጽመዋል የተባሉ ግለሰቦች ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ አዘዘ።

የኦሮሚያ ክልል ፍትህ ቢሮ የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ተከሳሾቹ የሙስና አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23 ድንጋጌን ተላልፈዋል በማለት ሀሰተኛ መንግስታዊ ወይም ህዝባዊ ሰነዶችን አዘጋጅቶ በመጠቀም የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።

ተከሳሾቹ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አምቦ ዲስትሪክት በወጣ የስራ ማስታወቂያ የመጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃ በማቅረብ የስራ ቅጥር ውል ስምምነት መፈጸማቸው በክሱ ተጠቅሷል።

ተከሳሾቹ 12 ሲሆኑ 10 ሩ የቅጥር ውል ከፈጸሙ በኋላ ለ10 ወራት በየደረጃው በተለያየ መጠን ወርኃዊ ደመወዝ መውሰዳቸውን ነው  ዐቃቤ ሕግ በክሱ ያመላከተው።

ቀሪዎቹ ሁለት ተከሳሾች ደግሞ የስራ ቅጥር ውል ስምምነት ከፈጸሙ በኋላ  የማስረጃ ማጣራት ስራ ሲጀመር መሰወራቸውን ነው ዐቃቤ ሕግ በክሱ ያመላከተው።

በዚህም ዐቃቤ ሕግ ያቀረበባቸው ሀሰተኛ መንግስታዊ ወይም ህዝባዊ ሰነዶችን አዘጋጅቶ መጠቀም የሙስና ወንጀል ክስ ዝርዝር ለ 10 ግለሰቦች በችሎት እንዲደርሳቸው ተደርጓል።

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተረኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ በነበረው ቀጠሮ በችሎት የቀረቡት 10 ተከሳሾች ማረሚያ ቤት እንዲወርዱና ቀሪ ሁለት ተከሳሾችን ደግሞ የኦሮሚያ ፖሊስ አፈላልጎ በቀጣይ ቀጠሮ እንዲያቀርባቸው አዟል።

የተከሳሾችን የዕምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ለጥቅምት 6 ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ መያዙም ተገልጿል፡፡
(ታሪክ አዱኛ)

@Addis_News