Get Mystery Box with random crypto!

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የታደሙበት የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል የገዳ ስርአቱን በጠበቀ መል | አዲስ ነገር መረጃ

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎች የታደሙበት የሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል የገዳ ስርአቱን በጠበቀ መልኩ በሰላም መከበሩን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታወቀ፡፡

አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ከተለያዩ የሀገሪቱና ከጎረቤት ሀገራት የመጡ እንግዶች እና ቱሪስቶች የታደሙበት የ2016 ሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በሰላም እና በልዩ ድምቀት መከበሩን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ-ኃይል አስታውቋል፡፡

የበዓሉ በሰላም መከበር የሀገሪቱን መልካም ገፅታ ለመገንባት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ግብረ-ኃይሉ አስታውሶ ለበዓሉ በሠላም መከበር የድርሻቸውን ለተወጡ ሁሉ ምስጋና አቅርቧል፡፡

@Addis_News