Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ነገር መረጃ

የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_news — አዲስ ነገር መረጃ
የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_news — አዲስ ነገር መረጃ
የሰርጥ አድራሻ: @addis_news
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 76.16K
የሰርጥ መግለጫ

አዲስ ነገር መረጃዎች
መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇
@Addisnegermereja_bot

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-10-10 09:12:28
የዓለም የምግብ ድርጅት በኢትዮጵያ ለፍልሰተኞች የሚያደርገውን ርዳታ ቀጠለ!

የርዳታ ምግብ ላልታሰበለት ዓላማ እየዋለ እና ተሰርቆ ለገበያ እየቀረበ ነው በሚል ባለፈው ሰኔ በኢትዮጵያ የሚያደርገውን የምግብ ስርጭት አቋርጦ የነበረው የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ 900 ሺሕ ለሚሆኑ ፍልሰተኞች ምግብ በማደል ፕሮግራሙን መልሶ ጀምሯል።

ዕደላውን መልሶ የጀመረው፣ የቁጥጥር ሥርዐቱን በማሻሻል እንደሆነም ታውቋል። በፍልሰተኞች መጠለያ የሚገኙት 24 ማከማቻዎች አሁን ድርጅቱ እንደሚቆጣጠራቸውና፣ የተረጂዎች ምዝገባም በዘመናዊ መንገድ እንደሚደረግ ድርጅቱ ገልጿል።

በአምስት ክልሎች ባሉ የስደተኞች መጠለያ የሚገኙ ሰዎች እንዲሁም አዲስ ከሱዳን የገቡ ፍልሰተኞች የምግብ ዕደላ እየተደረገላቸው እንደሆነ ድርጅቱ ሮም ከሚገኘው ጽ/ቤቱ ዛሬ አስታውቋል። ባለፉት ስድስት ወራቶች ውስጥ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የገቡ 35ሺሕ የሚሆኑ ፍልሰተኞች በአስቸኳይ ምግብ እንደሚያስፈልጋቸው፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ፤ ከሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ የመጡ 850 ሺሕ የሚሆኑ ፍልሰተኞችን በማስተናገድ ላይ መሆኗል ድርጅቱ ገልጿል።

በኢትዮጵያ የምግብ ርዳታ ለሚያሻቸው ዕደላው እንዲቀጥልም፣ የቁጥጥር ሥርዐቱን ለማሻሻል እያደረገ ያለው ሙከራ መልካም ውጤት እያሳየ እንደሆነ የምግብ ድርጅቱ ጨምሮ ገልጿል።

Via VoA
@Addis_News
16.5K views06:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-10 09:11:25
የ 12ኛ ክፍል ውጤት ተለቀቀ
---—----------------------------      
   
  አስደሳች ዜና ለ 2015 Entrance ለተፈተናችሁ ተማሪዎች

ትምህርት ሚኒስተር ዛሬ የ 12ተኛ ክፍል ውጤት ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ማንኛውም ተፈታኝ ታች ባለው ሊንክ በመጠቀም ውጤቱን መመልከት ይችላል ብሏል


ፈጥነው ታች ባለው ሊንክ ውጤትዎን ይመልከቱ

ማሳሰቢያ:- VPN ወይም Psiphon መጠቀም ይኖርባችሗል

Apply Now

 https://addiszemenvacancy.com/2023/09/18/grade-12-entrance-exam-result-2016-2023/

-------Follow Our Website-------
                   
        https://addiszemenvacancy.com

--------Join Our Telegram----------
                                                                        
 https://t.me/Addis_Zemen_Vacancy  
---------------------------------
15.5K views06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-10 08:20:23 ውጤት

ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ውጤት ከ1 ሰዓት ጀምሮ መመልከት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ያሳወቀ ቢሆን እስካሁን ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት እንዳልቻሉ ገልጸዋል።

ተማሪዎች ውጤቱን ለምን እስካሁን  መመልከት እንዳልቻሉ የሚመለከታቸውን አካላት አነጋግሮ ለማሳወቅ ጥረት እንደሚያደርግ #ቲክቫህ አስታውቋል።

Share @Addis_News
14.4K viewsedited  05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-10 06:54:06 መልካም እድል

ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ውጤት ማየት ይጀምራል በድጋሚ ለሁላችሁም መልካም እድል።

share @Addis_News
15.8K views03:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-10 06:25:23 የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ማክሰኞ በ29/01/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ ብሏል።

ተፈታኞች የሚከተሉትን 3 አማራጭ አድራሻዎችን #ብቻ በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ሲል ገልጿል።
    
በዌብ ሳይት፡- eaes.et
በአጭር የጽሁፍ መልዕክት፡- 6284
ቴሌግራም አድራሻ፡- @eaesbot

አገልግሎቱ ከላይ ከተገለጹት የውጤት መግለጫ አማራጮች ውጪ ሌላ የውጤት መግለጫ መንገዶች የሌሉ መሆኑን አሳውቋል።

ተማሪዎች በማመሳሰል " ውጤት እንገልጻለን " ከሚሉ ከማንኛውም አጭበርባሪዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት ተላልፏል።

በተጨማሪ ተቋሙ ውጤት ለማሳየት ምንም ክፍያ የማይጠይቅ መሆኑን አስገንዝቧል።

@Addis_News
16.4K viewsedited  03:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-08 12:07:56 #UPDATE ትምህርት ሚኒስቴር በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ዙሪያ መግለጫ ይሰጣል። ሚኒስቴሩ ነገ መስከረም 28/2016 ዓ.ም ከቀኑ 5:30 ጀምሮ የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን በተመለከተ በሚኒስቴሩ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል። በሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አመለወርቅ ህዝቅኤል ተፈርሞ ለተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን…
13.5K viewsedited  09:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-08 11:58:55
ዛሬ የሚደረግ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታ

12:30 | አርሰናል ከ ማንችስተር ሲቲ 

@Addis_News
12.8K viewsedited  08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-07 20:02:24
በእስራኤልና ፍልስጤም መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ተነገረ!!

እስራኤል በደቡባዊ ግዛቷ ድንገተኛ የሮኬት ጥቃት መድረሱን ተከትሎ ምላሽ ይሆናል ያለችውን የአየር ጥቃት በጋዛ ላይ መውሰድ ጀምራለች፡፡

ሃማስ በደቡባዊ እስራኤል ባካሄደው ድንገተኛ የሮኬት ጥቃት ከ40 በላይ የእስራኤል ዜጎች መገደላቸውንና በርካቶች መቁሰላቸውን ዓለም አቀፍ የዜና ምንጮች እየዘገቡት ይገኛሉ፡፡ ይህን የድንገቴውን ጥቃት ተከትሎም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ "እስራኤል ጦርነት ላይ ናት" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እስራኤል ለጥቃቱ ምላሽ አየር ኃይሏን አሰማርታ በጋዛ ላይ ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት እያካሄደች ሲሆን ዘገባው እስከተጠናቀረበት ድረስ ከ160 በላይ ፍልስጤማዊያን መገደላቸውንና በሺዎች የሚቆጠሩ መቁሰላቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ግጭቱን ተከትሎ የተለያዩ አገራት ምላሽ እየሰጡ ሲሆን ማልታ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ ተሰብስቦ እንዲመክር ጥሪ ስታድርግ ሩሲያ ደግሞ ሁለቱ ወገኖች ጉዳዩን በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ጠይቃለች፡፡

@Addis_News
13.6K viewsedited  17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-07 19:54:56
ሰላም መኪና መግዛት ፈልገው የፈለጉትን አተዋል? ለማንኛውም አይነት የመኪና ፍላጐቶ እና አማራጭዎ የሚያማክሮት አጥተው ተቸግረዋል?

እንግዲያውስ መፍትሔ አለን SAFE AUTO እንሰኛለን አዲስም ሆነ ያገለገለ መኪና መግዛት ከፈለጉ ወይንም አዲስም ሆነ ያገለገለ የሚሸጥ መኪናም ካሎት ሙሉ መረጃና ተንቀሳቃሽ ምስል በመላክ እናሻሽጥሎታለን።

መቀየርም አስበው ከሆነ ያነጋግሩን ምን አለፋዎት እኛ ጋር መተው መፍትሔ አያጡም።

ለበለጠ መረጃ ከስር ያለውን የቴልግራም ቻናል በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ

https://t.me/Safeautomarket2019

በቴሌግራም ለማናገር @solesafe

ለመደወል +251911392793
                    +251912603619
13.5K views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-10-07 14:50:02
ሰበር

እስራኤል በመላ ሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ ጦርነት አዋጅ አወጀች!!

ሐማስ በአስራኤል ላይ የሮኬት ጥቃቶችን ፈፅሟል፣ታጣቂዎቹም ወደ እስራኤል መግባታቸውም ተገልጿል!

በርካታ የእስላማዊው ታጣቂ ቡድን ሐማስ ታጣቂዎች ድንገተኛ ጥቃት ሰንዝረው ወደ ደቡባዊ እስራኤል ክፍል ዘልቀው መግባታቸው ተዘገበ።

ከጥቃቱ ቀደም ብሎ በርካታ ሮኬቶች ወደ አስራኤል ግዛት የተተኮሱ ሲሆን፣በዚህም ሳቢያ በመላዋ አገሪቱ የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ደውሎች ተሰምተዋል።

እስራኤልም በበኩሏ በጋዛ ሰርጥ በሚገኙ ኢላማዎች የአየር ጥቃት ማካሄድ ጀምራለች።

በሮኬት ጥቃቶቹ አስራኤል ውስጥ አንድ ሰው የተገደል ሲሆን፣ በቴላቪቭ አቅራቢያ እና በጋዛ ሰርጥ ዙሪያ ፍንዳታዎች መሰማታቸው ተነግሯል።የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን የሆነው ሐማስ ለተፈጸመው ጥቃት ኃላፊነት የወሰደ ሲሆን፣በ20ደቂቃ ውስጥ 5ሺህ ሮኬቶችን ወደ አስራኤል መተኮሱን ገልጿል።

የእስራኤል ጠ/ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለሕዝባቸው"የእስራኤል ህዝብ ሆይ፤ጦርነት ላይ ነን ፤ ይህን ጦርነትም እናሸንፋለን "ብለዋል።

የእስራኤል የመከላከያ ኃይል ባወጣው መግለጫ“ቡድኑ ሰፊ የሮኬት ጥቃቶችን ወደ እስራኤል ግዛት ከተኮሰ በኋላ”በተለያዩ አቅጣጫዎች ደግሞ ታጣቂዎቹ ወደ እስራኤል ግዛት መግባታቸውን አስታውቋል። መግለጫው አክሎም የእስራኤል ጦር ኃይል ጠቅላይ ማዘዣ በተከፈተው ጥቃት ዙሪያ “ሁኔታዎች ግምገማ” እያካሄደ መሆኑን ጠቅሶ ሐማስ ለተፈጸመው ጥቃት “ኃላፊነት እና የአጸፋ እርምጃ እንደሚከተለው” ገልጿል።

በተጨማሪም በጋዛ ሰርጥ ዙሪያ ያሉ ነዋሪዎች ቤታቸው እንዲቆዩ የተጠየቁ ሲሆን፣ በደቡባዊና በማዕከላዊ የአገሪቱ አካባቢ ያሉ ሲቪል ሰዎች ደግሞ ከጥቃት መጠለያዎች አቅራቢያ እንዲቆዩ ተነግሯቸዋል።

(Via BBC)
@Addis_News
14.8K views11:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ