Get Mystery Box with random crypto!

በእስራኤልና ፍልስጤም መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ተነገረ!! እስራኤል በደቡባዊ ግ | አዲስ ነገር መረጃ

በእስራኤልና ፍልስጤም መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ተነገረ!!

እስራኤል በደቡባዊ ግዛቷ ድንገተኛ የሮኬት ጥቃት መድረሱን ተከትሎ ምላሽ ይሆናል ያለችውን የአየር ጥቃት በጋዛ ላይ መውሰድ ጀምራለች፡፡

ሃማስ በደቡባዊ እስራኤል ባካሄደው ድንገተኛ የሮኬት ጥቃት ከ40 በላይ የእስራኤል ዜጎች መገደላቸውንና በርካቶች መቁሰላቸውን ዓለም አቀፍ የዜና ምንጮች እየዘገቡት ይገኛሉ፡፡ ይህን የድንገቴውን ጥቃት ተከትሎም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ "እስራኤል ጦርነት ላይ ናት" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እስራኤል ለጥቃቱ ምላሽ አየር ኃይሏን አሰማርታ በጋዛ ላይ ሰፊ ወታደራዊ ጥቃት እያካሄደች ሲሆን ዘገባው እስከተጠናቀረበት ድረስ ከ160 በላይ ፍልስጤማዊያን መገደላቸውንና በሺዎች የሚቆጠሩ መቁሰላቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

ግጭቱን ተከትሎ የተለያዩ አገራት ምላሽ እየሰጡ ሲሆን ማልታ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ ተሰብስቦ እንዲመክር ጥሪ ስታድርግ ሩሲያ ደግሞ ሁለቱ ወገኖች ጉዳዩን በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲፈቱ ጠይቃለች፡፡

@Addis_News