Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ማክሰኞ | አዲስ ነገር መረጃ

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ማክሰኞ በ29/01/2016 ዓ.ም ከጥዋቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ ብሏል።

ተፈታኞች የሚከተሉትን 3 አማራጭ አድራሻዎችን #ብቻ በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ሲል ገልጿል።
    
በዌብ ሳይት፡- eaes.et
በአጭር የጽሁፍ መልዕክት፡- 6284
ቴሌግራም አድራሻ፡- @eaesbot

አገልግሎቱ ከላይ ከተገለጹት የውጤት መግለጫ አማራጮች ውጪ ሌላ የውጤት መግለጫ መንገዶች የሌሉ መሆኑን አሳውቋል።

ተማሪዎች በማመሳሰል " ውጤት እንገልጻለን " ከሚሉ ከማንኛውም አጭበርባሪዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት ተላልፏል።

በተጨማሪ ተቋሙ ውጤት ለማሳየት ምንም ክፍያ የማይጠይቅ መሆኑን አስገንዝቧል።

@Addis_News