Get Mystery Box with random crypto!

የዓለም የምግብ ድርጅት በኢትዮጵያ ለፍልሰተኞች የሚያደርገውን ርዳታ ቀጠለ! የርዳታ ምግብ ላልታሰ | አዲስ ነገር መረጃ

የዓለም የምግብ ድርጅት በኢትዮጵያ ለፍልሰተኞች የሚያደርገውን ርዳታ ቀጠለ!

የርዳታ ምግብ ላልታሰበለት ዓላማ እየዋለ እና ተሰርቆ ለገበያ እየቀረበ ነው በሚል ባለፈው ሰኔ በኢትዮጵያ የሚያደርገውን የምግብ ስርጭት አቋርጦ የነበረው የዓለም ምግብ ፕሮግራም፣ 900 ሺሕ ለሚሆኑ ፍልሰተኞች ምግብ በማደል ፕሮግራሙን መልሶ ጀምሯል።

ዕደላውን መልሶ የጀመረው፣ የቁጥጥር ሥርዐቱን በማሻሻል እንደሆነም ታውቋል። በፍልሰተኞች መጠለያ የሚገኙት 24 ማከማቻዎች አሁን ድርጅቱ እንደሚቆጣጠራቸውና፣ የተረጂዎች ምዝገባም በዘመናዊ መንገድ እንደሚደረግ ድርጅቱ ገልጿል።

በአምስት ክልሎች ባሉ የስደተኞች መጠለያ የሚገኙ ሰዎች እንዲሁም አዲስ ከሱዳን የገቡ ፍልሰተኞች የምግብ ዕደላ እየተደረገላቸው እንደሆነ ድርጅቱ ሮም ከሚገኘው ጽ/ቤቱ ዛሬ አስታውቋል። ባለፉት ስድስት ወራቶች ውስጥ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የገቡ 35ሺሕ የሚሆኑ ፍልሰተኞች በአስቸኳይ ምግብ እንደሚያስፈልጋቸው፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ፤ ከሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ የመጡ 850 ሺሕ የሚሆኑ ፍልሰተኞችን በማስተናገድ ላይ መሆኗል ድርጅቱ ገልጿል።

በኢትዮጵያ የምግብ ርዳታ ለሚያሻቸው ዕደላው እንዲቀጥልም፣ የቁጥጥር ሥርዐቱን ለማሻሻል እያደረገ ያለው ሙከራ መልካም ውጤት እያሳየ እንደሆነ የምግብ ድርጅቱ ጨምሮ ገልጿል።

Via VoA
@Addis_News