Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር እስራኤል በመላ ሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ ጦርነት አዋጅ አወጀች!! ሐማስ በአስራኤል ላይ የ | አዲስ ነገር መረጃ

ሰበር

እስራኤል በመላ ሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ ጦርነት አዋጅ አወጀች!!

ሐማስ በአስራኤል ላይ የሮኬት ጥቃቶችን ፈፅሟል፣ታጣቂዎቹም ወደ እስራኤል መግባታቸውም ተገልጿል!

በርካታ የእስላማዊው ታጣቂ ቡድን ሐማስ ታጣቂዎች ድንገተኛ ጥቃት ሰንዝረው ወደ ደቡባዊ እስራኤል ክፍል ዘልቀው መግባታቸው ተዘገበ።

ከጥቃቱ ቀደም ብሎ በርካታ ሮኬቶች ወደ አስራኤል ግዛት የተተኮሱ ሲሆን፣በዚህም ሳቢያ በመላዋ አገሪቱ የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያ ደውሎች ተሰምተዋል።

እስራኤልም በበኩሏ በጋዛ ሰርጥ በሚገኙ ኢላማዎች የአየር ጥቃት ማካሄድ ጀምራለች።

በሮኬት ጥቃቶቹ አስራኤል ውስጥ አንድ ሰው የተገደል ሲሆን፣ በቴላቪቭ አቅራቢያ እና በጋዛ ሰርጥ ዙሪያ ፍንዳታዎች መሰማታቸው ተነግሯል።የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን የሆነው ሐማስ ለተፈጸመው ጥቃት ኃላፊነት የወሰደ ሲሆን፣በ20ደቂቃ ውስጥ 5ሺህ ሮኬቶችን ወደ አስራኤል መተኮሱን ገልጿል።

የእስራኤል ጠ/ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ለሕዝባቸው"የእስራኤል ህዝብ ሆይ፤ጦርነት ላይ ነን ፤ ይህን ጦርነትም እናሸንፋለን "ብለዋል።

የእስራኤል የመከላከያ ኃይል ባወጣው መግለጫ“ቡድኑ ሰፊ የሮኬት ጥቃቶችን ወደ እስራኤል ግዛት ከተኮሰ በኋላ”በተለያዩ አቅጣጫዎች ደግሞ ታጣቂዎቹ ወደ እስራኤል ግዛት መግባታቸውን አስታውቋል። መግለጫው አክሎም የእስራኤል ጦር ኃይል ጠቅላይ ማዘዣ በተከፈተው ጥቃት ዙሪያ “ሁኔታዎች ግምገማ” እያካሄደ መሆኑን ጠቅሶ ሐማስ ለተፈጸመው ጥቃት “ኃላፊነት እና የአጸፋ እርምጃ እንደሚከተለው” ገልጿል።

በተጨማሪም በጋዛ ሰርጥ ዙሪያ ያሉ ነዋሪዎች ቤታቸው እንዲቆዩ የተጠየቁ ሲሆን፣ በደቡባዊና በማዕከላዊ የአገሪቱ አካባቢ ያሉ ሲቪል ሰዎች ደግሞ ከጥቃት መጠለያዎች አቅራቢያ እንዲቆዩ ተነግሯቸዋል።

(Via BBC)
@Addis_News