Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ከአምስት በላይ ወረዳዎች የመንግሥት ሠራተኞች የመስከረም ወር ደመ | አዲስ ነገር መረጃ

በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ከአምስት በላይ ወረዳዎች የመንግሥት ሠራተኞች የመስከረም ወር ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ዋዜማ ተረድታለች።

የመስከረም ወር ደመወዝ እስካሁን ካልተከፈላቸው መካከል፣ በመርጡ ለማርያም፣ ሸበል፣ ቢቡኝ፣ የጁቤ፣ ቁይ እና ደብረ ኤልያስ ወረዳዎች የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ይገኙበታል።

ዋዜማ ያነጋገረቻቸው አንዳንድ የመንግሥትን ሠራተኞች፣ የወረዳዎች የፋይናስ ቢሮ ገንዘብ እንዳልተለቀቀለት መናገሩንና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ግን ያገድኩት ገንዘብ የለም የሚል ምላሽ መስጠቱን ተናግረዋል። ዋዜማ ከክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ምላሽ ለማግኘት ሙከራ አልተሳካም።

ኾኖም ደመወዝ ያልተከፈለው፣ አብዛኞቹ ወረዳዎች የፋኖ ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱባቸው በመኾናቸው ሳይኾን እንደማይቀር አንዳንድ ሠራተኞች ግምታቸውን ሰጥተዋል።

@addis_news