Get Mystery Box with random crypto!

'ተማሪዎች በዚህ ልክ በፈተና አለማለፋቸው የትምህርት ጥራትን አያረጋግጥም' ከመጀመሪያ ደረጃ ጀም | አዲስ ነገር መረጃ

"ተማሪዎች በዚህ ልክ በፈተና አለማለፋቸው የትምህርት ጥራትን አያረጋግጥም"

ከመጀመሪያ ደረጃ ጀምሮ ሳይሰራ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ላይ ተማሪዎች በብዛት አለማለፋቸው የተፈለገውን የትምህርት ጥራት ሊያመጣ የማይችል መሆኑን የትምህርት ባለሙያዎች ለመናኸሪያ ሬድዮ አስታውቀዋል፡፡ ይልቁኑም ጥራት ከታሰበ ከመጀመሪያ ደረጃ ጀምሮ ሊሰራ ይገባ ነበር ያሉት የትምህርት ባለሙያው ፕሮፊሰር ጥሩሰው ተፈራ ናቸው፡፡

ፈተና የተማሪዎች መለኪያ አንዱ መስፈርት ቢሆንም በዚህ መለኩ መሆኑ የሃገሪቱን የትምህርት ጥራት እንዲጠብቅ ማድረግ እደማይቻል ደግሞ ሌላኛዉ የትምህርት ባለሙያ አቶ በኒያም ገብረእየሱስ ይናገራሉ፡፡ 

ከመጀመሪያ ደረጃ ጀምሮ መሰራት ይገባቸው የነበሩ ስራዎች ባለመሰራታቸው ነዉ አሁን ላይ ተማሪዎች በዚህ መልኩ ዉጤት ሊያመጡ የቻሉት ስለዚህ ከስር መሰረቱ ጀምሮ በትኩረት ሊሰራበት ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

ከመሰረቱ ጀምሮ ለተማሪዎች ብቁ የሆኑ መፅሃፍቶች ፤በቃት ያላቸዉ መምህራን እና ቤተመፀሃፍቶች በበቂ ሁኔታ ተሟልቶ ጥራት ላይ ከጅማሬዉ ሊሰራ እንደሚገባ ያነሱት ባለሙያዎቹ በተጨማሪም ወላጆች እና መምህራና እንዲሁም ሁሉም ባለድርሻ አካላት አመትን ጠብቀው በሚመጡ ውጤቶች  ላይ ቅሬታን ከማቅረብ በላይ ሃላፊነታቸዉን ሊወጡ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

መናኸሪያ ኤፍኤም
@Addis_News
@Addis_News