Get Mystery Box with random crypto!

አቢሲኒያ - Times

የቴሌግራም ቻናል አርማ abisiniya_times — አቢሲኒያ - Times
የቴሌግራም ቻናል አርማ abisiniya_times — አቢሲኒያ - Times
የሰርጥ አድራሻ: @abisiniya_times
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 38.80K
የሰርጥ መግለጫ

Description
• ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
•በአለማችን የተከናወኑ አስደናቂ ክስተቶች፣
•የስፖርት እና መዝናኛ መረጃዎች፣
•24 ሰዓት ትኩስ እና አዳዲስ መረጃ ያገኛሉ፣
•እንዲሁም ጠቅላላ እውቀት፣
ለማንኛውም መረጃ፦
#ለአስተማማኝ የመረጃ ምንጭ
https://t.me/abisiniya_times

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-05-31 21:13:00
ባህር ዳር አሁን!

ከባህር ዳር ከተማ ዙሪያ እና አካባቢው የተሰባሰቡ የአማራ ገበሬዎች በድጋሚ በአፈር ማዳበሪያ እጦት ምክንያት መሬታችን ጦም ሊያድር ነው ።እህል መዝራት አልቻልንም በማለት በአሁኑ ሰዐት በባህር ዳር ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው ።

የከተማው ህዝብ ከገበሬዎች ጎን ፤ከወገኖቻችን ጎን የመሆን ታሪካዊም ፣የሞራልም እንዲሁም የውዴታ ግዴታ ነው ።ነገ ይህ አርሶ አደር ካላመረተ ፣የምርት እጥረት ይገጥማል የዚህ ችግር ዋና ገፈት ቀማሹ የከተሜው ህዝብ ነው ።

የአማራ ወጣቶች ማህበር(አወማ) ከአማራ አርሶ አደሮች ጎን ነን ።የአማራ ገበሬዎችን ሆን ተብሎ ለማደኸየት ፣ለማጎሳቆል እና ለማስገበር የሚደረግ የስርዓቱ ሴራ በፅኑ እናወግዛለን ።

የአማራ ወጣቶች ማህበር(አወማ)
@abisiniya_times
3.0K viewsedited  18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-31 20:04:01
ጌታቸው ረዳ "ህውሓት ትጥቅ አስረከበ የሚለው ዜና ድራማ መሆኑን.... ጥበብ በተሞላበት መንገድ የአማራን ልዩ ሃይል ማፍረስ መቻሉን... እንዲሁም ባሁኑ ሰዓት በአማራ ክልል ምንም አይነት የተደራጀ ሃይል አለመኖሩን..." ተናገረ የሚል መረጃ ሲንሸራሸር እያየሁ ነው።

እኔ ግን እላለሁኝ...

የአማራ ልዩ-ሃይልን ያፈረሰው ብአዴን የተባለ ጸረ ሕዝብ ድርጅት እንጂ የጌታቸው ረዳ ጥበብ አይደለም። ፋኖን በከባድ መሣሪያ የሚያስደበድበውም የኦነግ ቅጥረኛ የሆነው የብአዴን አመራር እንጂ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አይደለም።በተረፈ ልዩ ሃይል ሲበተን ሕዝባዊ ሃይል እንደሚወለድ አያጠራጥርም።

@abisiniya_times
@abisiniya_times
2.9K viewsedited  17:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 22:54:10
የእህታችን ፀጋ በላቸው ጉዳይ ነገሩ እንዲህ ነው...

> ጠላፊ (የከተማው ከንቲባ) - "ሽማግሌ እልካለው ተቀበሉ"
"የከንቲባው የግል ጠባቂ ነኝ ምንም አታመጡም!"
ከቀናት በፊት ቤተሰብ ጋር ደወሎ የተናገረው።

እና በዚህ ልክ የመንግሥትን ስልጣን ተማምኖ እንዲህ ያለ ወንጀል ሲሰራ ሲታበይ የከተማው ከንቲባም ሆነ በተዋረድ ያሉ የስራ ሐላፊዎች /በሴቶች ዙሪያ የሚሰሩ ቢሮዎች/ ከለላ እያደረጉለት ካልሆነ በቀር እሱን ለህግ ማቅረብ እሷንም ነፃ ማውጣት ትልቅ ነገር ሆኖ ነው?

@abisiniya_times
@abisiniya_times
3.2K viewsedited  19:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-29 22:35:18
#ፍትህ_ለእህታችን_ፀጋ_በላቸው !

በሐዋሳ ከተማ ከንቲባ የግል ጠባቂ የተጠለፈችው ፀጋ በላቸው !

የዳሽን ባንክ ሐዋሳ ዋርካ ቅርንጫፍ ሰራተኛ ነች ። ፀጋ በላቸው ትባላለች፤ ለማግባት ጥቂት ጊዜ ቀርቷት በዝግጅት ላይ ነበረች።

ሆኖም ግን ፤ ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ከስራ ወደቤት ስታቀና ፤ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ጠባቂ የሆነው ኮንስታብል የኋላመብራት ወ/ማሪያም ጠልፎ ተሰውሯል ።

ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በማሳወቅና የፍርድ ቤት መጥሪያ በማውጣት ተጠርጣሪውን ለመያዝ ቤተሰቦች የቻሉትን ቢያደርጉም ፤የሲዳማ ክልል ፓሊስ ጉዳዩን በቸልተኝነት አለፍ ሲልም ተባባሪ በሚመስል መልኩ ጉዳዮን ይዞት፤ ለባለፉት 7 ቀናት ፀጋ በላቸው የት እንዳለች አናውቅም በማለት ፤ ቤተሰብ ጭንቅት ላይ ነው።
ሼር
#ፍትህ_ለእህታችን_ፀጋ_በላቸው

@abisiniya_times
@abisiniya_times
2.9K viewsedited  19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 23:25:51
ኢትዮጵያ አየር መንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ለሚያደርጉ ሰዎች እና ኩላሊት ለሚለግሱ ሰዎች እንዲሁም ለአስታማሚ ችግረኛ ቤተሰብ ነፃ የአየር ትራንስፖርት ሊሰጥ መሆኑን ከኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ ከአቶ ሰለሞን አሰፋ ሰማን።
ሼር
@abisiniya_times
@abisiniya_times
3.2K viewsedited  20:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 21:55:07
እስኪ ባህር ማዶ ዘልቀን ትንሽ ስለ ቱርክ አሁናዊ ሁኔታ..

ቱርክ ጋር የማንስማማባቸው የፓለቲካ ኩነቶች ቢኖሩም ለህዝቡ ለአገሩ በሚታመን እንደ ኤርዶጋን አይነት መሪ ስታይ አለመቅናት አንችልም። የፓለቲካ ልዩነታችን እንዳለ ሆኖ ለቱሩኩ መሪ ኤርዶጋን አድናቆታችን ላቅ ያለ ነው። የቱሩኩ መሪ ኤርዶጋን ከመነሻ አስተዳደጉ ጥሮ ግሮ ተምሮ እስከ ህዝብ መሪ የደረሰበት ውጣ ውረድ የሚያስተምር ቢሆንም በመሪነት ዘመኑ ግን አገሩን ወደ ከፍታ የወሰደበት ጥበቡ እጅግ የሚደነቅና የሚያስተምር ነው።

ኤርዶጋን ዛሬ ላይ አገሩ ቱርክን በፓለቲካ፣ በድፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚ፣ በቱሪዝሙ ብቻ በሁሉም መስክ ከኃያላን አገር ተርታ አሰልፏታል። ኤርዶጋን ቱርክን በሁሉም መልክ ከኃያላን አገር ትከሻ ለትከሻ እንድትለካካ ስላደረጋት፤ ሰሞኑን የቱርክ ምርጫ የአለምን ቀልብ እንዲስብ ሆኗል። ምዕራባውያን የሚገዳደራቸውን መሪ እልባት ሊሰጡት የተለያየ ስልቶችን ሳይጠቀሙ እንዳልቀሩ የሚድያዎቻቸው ፕሮፓጋንዳ ያሳብቃል። የሆነው ሆኖ ህዝብ አይሳሳትም የሚለው ብሂል እውነታን ያረጋገጡ ቱርካውያን ለመሪያቸው ውለታ መልስ ይሆን ዘንድ ካርዳቸውን ለመሪያቸው ሰጥተዋል። የቱርኩ መሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጤና እክል ቢገጥመውም የቱርክ ህዝብ በጤናው መቃወስ ቢጨነቅም ለመሪያቸው ታመነው ተገኝተዋል።

የጥንቷ ቱርክ ገናና ታሪክ የነበራት ሲሆን በጥቂት ዘመናት በፊት የነበረች ቱርክ ደግሞ አቅመ ቢስነት የተጣባት ሆና ትታይ ነበር። የሆነው ሆኖ ከባዶ ወደ ከፍታ ማማ የመለሰ፤ የገናናዋን ቱርክ ታሪክ እንዲታደስ ያደረገ መሪ ኤርዶጋን መሆኑ አለም ይመሰክርለታል። የተዘነጋች ቱርክን ወደ ጥንተ ከፍታዋ የመለሳት መሪን ዳግም ለ5 ዓመት እንዲመራቸው ቱርካውያን መርጠውታል።

በእውነቱ በህዝቡም በመሪውም አለመቅናት አይቻልም!

@abisiniya_times
2.9K viewsedited  18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 21:21:35
ልዩ መረጃ

ኦሮሚያ ክልል ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በኦነግ ሸኔ ቁጥጥር ውስጥ ሆኗል።

በሆሮጉድሩ 14 የመንግስት ባለስልጣናት በታጣቂው ኃይል መገደላቸውን ከአካባቢው ባገኘነው መረጃ መሰረት አረጋግጠናል።

በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በሚገኘው ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት፤ 11 የፋብሪካው ሰራተኞች እና ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች እንደተገደሉ እና ፋብሪካው በተፈጸመበት በዚሁ ጥቃት እና ዘረፋ ምክንያት ስራ ማቋሙንም የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” መግለጹ ይታወሳል።

ከአዲስ አበባ በ350 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ግንቦት 12 ቀን 2015 መሆኑን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የህዝብ ግንኙነት እና ተሳትፎ ክፍል ኃላፊ አቶ ረታ ደመቀ ናቸው የገለጹት

እንዲሁም የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካም በታጣቂው ስር ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ታውቋል።

በቦታው የነበረው መከላከያ "ከላይ በመጣ ትዕዛዝ " እንዲሸሽ ተደርጎ አካባቢው ለሸኔ ተላልፎ እንደተሰጠ ነዋሪዎች እና አመራሮች ተናግረዋል።

የመከላከያውን መውጣት የተመለከቱ እና ስጋት ያደረባቸው የአካባቢው ነዋሪችም ወደ ሌላው ወለጋ አካባቢ እና ምዕራብ ሸዋ እየተሰደዱ ይገኛሉ።

ሆኖም የሕዝብ ጭፍጨፋና ማፈናቀል፣ የአመራር ግድያ እና የተቋማት ውድመት የሚፈፅመው የኦሮሚያ ታጣቂ ባለበት ከአገር መከላከያ ጋር ሆኖ ለሕዝብና አገር የሞተው የአማራ ፋኖ እና ልዩ ኃይል ላይ "የማፅዳት ዘመቻ" በሚል ጦርነት ከከፈቱ አንድ ወር ተቆጥሯል።

ምንጭ ፦ ጋዜጠኛ ሙልጌታ አንበርብር

@abisiniya_times
@abisiniya_times
2.7K viewsedited  18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 15:59:44 ከ98% በላይ አማኝ ህዝብ ያለበት ሀገር እየመራ ቤተ እምነቶችን መተናኮል ፣ ማጥቃት፣ ማፍረስ ዋጋ ያስከፍላል ይህንን ነውር የሆነ ነገር እያየን ማለፍ አንችልም።
ዛሬ መርካቶ አንዋር መስኪድ የተፈጸመው ይህንን አሳፋሪ ተግባር አጥብቀን እንቃወማለን።

@abisiniya_times
@abisiniya_times
3.2K viewsedited  12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-26 15:48:40
#አሳዛኝ ዜና

#መርካቶ ጭድ ተራ አከባቢ"መስጊድ ለምን ይፈርሳል"በሚል ሰላማዊ ጥያቄ ያነሳ አንድ የእስልምና ዕምነት ተከታይ መገደሉን ምንጮች ገለፁ።

ከሰሞኑን"ሸገር ከተማን" እንመሰርታለን በሚል በርካታ መስጅዶች መፍረሳቸው ይታወሳል።

#ተጨማሪ መረጃ @abisiniya_times
3.1K views12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 21:39:02 የአብይ አገዛዝ መዲናዋ ላይ 'ደሀ ባይኔ እንዳላይ' ብሏል። "ድህነትን እናጠፋለን" የሚለውን የኢሕአዴግ መፈክር "ደሀን እናጠፋለን" በሚል ተክተውታል። አዲስአበባ እየሆነ ያለው እጅግ ያስደነግጣል።
በፒያሳ፣ በአምስት ኪሎ፣ በሽሮ ሜዳ ማለፍ አሰቃቂ ሆኗል። ሺዎች በ'ጸጥታ ሞት' እያሸለቡ ነው።
ሆ ብለን እስካልተነሳን ድረስ ሞቱም፣ መፈናቀሉም የአዘቦት ክስተት ሆኖ ይቀጥላል.…

@abisiniya_times
@abisiniya_times
790 views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ