Get Mystery Box with random crypto!

አቢሲኒያ - Times

የቴሌግራም ቻናል አርማ abisiniya_times — አቢሲኒያ - Times
የቴሌግራም ቻናል አርማ abisiniya_times — አቢሲኒያ - Times
የሰርጥ አድራሻ: @abisiniya_times
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 38.80K
የሰርጥ መግለጫ

Description
• ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
•በአለማችን የተከናወኑ አስደናቂ ክስተቶች፣
•የስፖርት እና መዝናኛ መረጃዎች፣
•24 ሰዓት ትኩስ እና አዳዲስ መረጃ ያገኛሉ፣
•እንዲሁም ጠቅላላ እውቀት፣
ለማንኛውም መረጃ፦
#ለአስተማማኝ የመረጃ ምንጭ
https://t.me/abisiniya_times

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-03-01 18:07:08
ADEWA
@abisiniya_times
902 views15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-01 18:03:31
@abisiniya_times
887 views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 15:06:12 እነጌታቸው ረዳ አዲስ አበባ እንዳሉ ይሰማል። ቅዳሜና እሁድ በዳውሮ ዞን ሃላላ ሎጅ እንደነበሩም ሹክ ተብለናል። ለሁለተኛ ጊዜ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተገናኝተዋል። ከጥል በኋላ ፍቅር አይጣል ነው። ብልጽግና ሲደመር ህወሀት የቀድሞ ኢህአዴግ ሊሆን ዳርዳርታው ወደ መሀል እየመጣ ይመስላል። የባለፈው የሃላላው ግንኙነታቸው የፕሪቶሪያውንና የናይሮቢውን የስምምነት ወረቀቶች እንዲቀዳደዱና በሃላላው መዝገብ አዲስ ቃለመሃላ እንዲፈጽሙ ማድረጉን ማስተባበያ የሚያስፈልገው አይሆንም። የሃላላው ቃለመሀላ ስጋ ለብሶ ትግራይን እየመራት ነው። የእነጌታቸው የዚህኛው ዙር አመጣጥ ደግሞ ከፌደራሉ መንግስት የድርሻቸውን ስልጣን ለመዝገን እንደሆነ ይገመታል። በቅርቡ ሪፖርተር እንግሊዘኛው ላይ እንደተዘገበው አቶ ጌታቸው የፌደራል መንግስቱን ስልጣን ለመጋራት ከጠሚ/ሩ ጋር ንግግር መጀመሩን ገልጸዋል። ህወሀት በምን አይነት ቅርጽና መልክ ዳግም ወደስልጣን ማማው እየወጣ እንዳለ ግልጽ አይደለም። ህወሀት አብቅቶለታል ብላችሁ ለተዘናጋችሁ እንግዲያውስ እርማችሁን አውጡ። ይሄኛው ህወሀት ቂም በሆዱ ያረገዘ፡ ለበቀል ጥርሱን እያፏጨ ያለ፡ ከበፊት ጭካኔው መቶ እጥፍ ጨምሮ የሚመጣ ነው።
ህወሀት የጦርነት ሞተሩን እያሞቀው ነው። ፉከራ ቀረርቶው የያን ሰሞን፡ ምስራቅ አፍሪካ ላይ የሚችለን የለም አይነት ፕሮፖጋንዳውን ዳግም ጀምሮታል። የፈረደበት የትግራይ ወጣት ለሌላ ዙር ጦርነት ስልጠና እንዲገባ እየተደረገ ነው። ወልቃይት ዒላማ ተደርጋለች። ሰሞኑን ከወደወልቃይት ያነጋገርኳቸው የአከባቢው አመራሮች እንደሚሉት ህወሀቶች ''በቅርቡ በመዳፋችን ትገባላችሁ። አይቀርላችሁም'' እያሉ መልዕክት እንደሚልኩባቸው ገልጸውልኛል። ከዛቻና ፉከራው ባሻገር በቅርብ ርቀት ምሽግ እየማሱም እንደሆነ መረጃው እንዳላቸው አውግተውኛል። የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከመሀል ትግራይ ወጥቶ የህወሀት ሰራዊት ተረክቦታል። ይህ መሆኑ ለወልቃይቶች አይናቸውን ለአፍታም እንዳይከድኑ እንዳደረጋቸው ይናገራሉ። እንደአመጣጡ እንመልሰዋለን የሚለው ወኔ እንደእቶን እሳት ውስጣቸው ይንቀለቀላል። አልፈርድባቸውም። የሚያሳዝነው የወልቃይት ጉዳይ የእነሱ ብቻ ይመስል ሌላው በዝምታ ርቆ መቀመጡ ነው። የወልቃይት ጉዳይ የኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ ነው።
የፌደራል መንግስቱ በተለይም የኦሮሚያ ብልጽግና ከወልቃይት አንጻር አቋሙ በግልጽ ባይታወቅም ደምቀው የሚሰሙ ጭምጭምታዎች ግን ''ጉዳዩ የሁለት ክልሎች ነው። ፌደራል መንግስት ጣልቃ አይገባም'' አይነት እንደሆነ ያመላክታሉ። ባለፈው ጥር ወር መጀመሪያ ላይ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያነጋገሩት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ይህቺን ሀሳብ አነሱና '' ጦርነቱ እኮ የግዛት ማስመለስ አይደለም'' የምትል ውስጠ ወይራ ንግግር ጣል አደረጉባት። ለሚገባው በደንብ ይገባዋል። እስከአሁንም ወልቃይቶች በጀት የተነፈጋቸው፡ የመሰረተ ልማት አውታሮች የራቋቸው፡ የትግራይ ከተሞች በመብራትና ኢንተርኔት ሲንበሸበሹ አሁን ድረስ የወልቃይት አከባቢ በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እንዲሰነብት የተፈረደበት ስለምን ተብሎ እንደሆነ መጨረሻው እስኪነገረን መጠበቅ ያለብን አይመስለንም።
መጪው ጊዜ አጓጊና አስጨናቂ ነው። ህወሀቶች ወልቃይትን ለመሰልቀጥ ተዘጋጅተዋል። ፌደራል መንግስቱ አንድ ሱሪ አብረን እናጥልቅ በሚል ግንኙነት ከህወሀት ጋር በአዲስ ፍቅር ከንፏል። ነገ ከነገ ወዲያ ህወሀቶች አፈሙዛቸውን ወደወልቃይት ቢያዞሩ የፌደራል መንግስቱ ምን አቋም ሊወስድ ይችል ይሆን? በሁለት ክልሎች ጸብ አልገባም? በእርግጠኝነት ጠሚ/ሩ ስልጣናቸውና ቀጣይ ጉዞአቸው በወልቃይት ላይ በሚኖራቸው አቋም ላይ የሚወሰን ይሆናል። ወልቃይት ለእሳቸው እጣ ፈንታ የሪፈረንደም ያህል ተቀምጣለች።
messay mekonen
@abisiniya_times
1.2K views12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 13:03:26 "መንግስት ጋ ስምምነት ላይ በመድረሳችን የተግባር ጊዜ በማስፈለጉ ተጠርቶ የነበረው ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሟል "

@abisiniya_times
1.0K viewsedited  10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 13:02:24 ያዕቆብ መልእክት ፩፤፪-፫ “ወንድሞቼ ሆይ የእምነታችሁ
መፈተን ትእግስትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፤ ልዩ ልዩ
ፈተና ሲደርስባችሁ እንደሙሉ ደስታ ቁጠሩት”
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
የካቲት ፬ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

@abisiniya_times
1.0K viewsedited  10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 13:02:24 በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ ጉዳይ ከመንግሥት ጋር
እየተደረገ ስለሆነው ውይይት እና የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊደረግ ስለታሰበው ሰላማዊ ሰልፍ አስመክቶ የተሰጠ መግለጫ
ሮሜ ፭፤፫-፬ “ መከራ ትእግስትን እንዳያደርግ፤ ትእግስትም
ፈተናን፤ ፈተናም ተስፋን እንዳያደርግ እያወቅን በመከራችን
ደግሞ እንመካለን”

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ ከቤተ ክርስቲያናችን
ሃይማኖታዊ፤ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ሥርዓት ፍጹም ሕገ
ወጥ በሆነ መንገድ በመደራጀት የቤተ ክርስቲያንን መብትና
ጥቅም የጎዳ ተግባር መፈጸሙ ይታወሳል፡፡ የተከበረውን
የአበው ሐዋርያዊ ሢመተ ኤጲስ ቆጶስነት ሥርዓት
በመፈጸማቸው ምክንያት በተፈጠረው የቤተ ክርስቲያንን
ሉዓላዊ ክብርና ልዕልና የማቃለል፣ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ
ውለታ የዘነጋ፣ ሕልውናዋን እና አንድነቷን ለመናድ የተደረገ
ከፍተኛ ጥቃት በመፈጸሙና መንግሥትም የቤተ
ክርስቲያናችንን ሕግና ሥርዓት፣ እንዲሁም ተቋማዊ ሕልውና
እንዳያስከብር እና እንዳያከብር በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ቆይቷል፡፡

ከዚህም ውስጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
ባወጣው መግለጫ መንግሥት በዚሁ አካሄድ ሕግ እየጣሰ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እና ልእልና እያዋረደ የሚቀጥል
ከሆነ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት የጣሰውን ሕግ መሠረት
በማድረግ መብቷን ለማስከበር እስከ አሁን ድረስ ፍጹም
ሰላማዊ የሆነውን እንቅስቃሴዋን አድማሱን በማስፋት በየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለማድረግ ያቀደችውንና ያሳወቀችውን ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይነትበራሷ አደባባይ የምታከናውን መሆኑን ስታሳውቅ ቆይታለች፡፡

በዚሁ መሠረት መንግሥት ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው
የሰጠውን ቀነ ገደብ ከግምት ውስጥ በማስገባትና ጥሪውን
በመቀበል በየካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለአስቸኳይ ውይይት
ዝግጁ መሆኑን በተመረጡ የሀገር ሽማግልዎች አማካኝነት
መልእክቱ ሲደርሰን ካለው ወቅታዊ የሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ
አንጻር ጥሪውን በመቀበላችን በብፁዕ ወቅዱስፓትርያርክ
የተመራ አሥራ ሁለት ብፁዓን ሉቃነ ጳጳሳት ፣ የኢፌዴሪ
ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣
ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የሀገር
ሽማግልዎች በተገኙበት ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱም የተነሱት ነጥቦች በዋንኛነት ቤተ ክርስቲያን
ሃይማኖታዊ፤ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ሕግን መሠረት ባደረገ
መልኩ ጠብቃ የምትሠራ እና ከዚህ ውጭ ምንም አይነት
ድርድር የልለው መሆኑን ገልጻለች፡፡ በዚህም መነሻ መንግሥት የቤተ ክርስቲያንን አቋም በመቀበል ወደፊትም የቤተ ክርስቲያንን አንድነት እና ሉዓላዊነትን በጠበቀ መንገድ
እንደሚሠራ አረጋግጧል፡፡

በዚህ የፈተና ጊዜ ውስጥ የቅዱስ ሲኖዶስን መመሪያ በመቀበል ራስን የቤተ ክርስቲያን ሕልውና መስዋእት አድርጎ በማቅረብ፤ በክርስቶስ ደም የከበረችውን ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ እና የማስጠበቅ ከጸጉር መላጨት እስከ ገመድ መታጠቅ በእንባና በዋይታ መላው ሕዝበ ክርስቲያን ሀዘናችሁን የገለጻችሁበት መንገድ የቤተ ክርስቲያን ሕልውና ማስጠበቅ መሠረት ሆኗል፡፡

በዚህም ሂደት ሕይወታቸውን በሰማእትነት፤ አካላችሁን ለአካል ጉዳት፤ ኑሯችሁን ለፈተና ፤ ለስደት፤ ለእንግልት እንዲሁም ለእስራት አሳልፋችሁ የሰጣችሁ ልጆቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ ሁልጊዜም ውለታችሁን ሲያስታውስ የሚኖር ሲሆን የጉዳት ሰለባ ለሆኑቱም መንግሥት የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለይቶ በሕግ አግባብ ተጠያቂ እንደሚያደርግ እና አሁን ላይ እስር፤ ወከባ፤ እንግልት እየተፈጸመባቸው ያለት ብፁዓን ሉቃነ ጳጳሳት፤ የሀገረ ስብከት ሠራተኞች፤ አገልጋይ ካህናት እና በተለያዩ አደረጃጀቶች የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ችግሩ በአስቸኳይ እንዲቆምና የታሠሩትም እንዲፈቱ፤
አገልግልታቸውን በሰላምና በነጻነት መስጠት እንዲችሉ
ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

በትናትናው እለት ከመንግሥት ጋር ባደረግነው ውይይት
መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም ሙሉ በሙሉ የተቀበለ
ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ እሁድ የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም እንዲካሔድ የተወሰነው ሀገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

በዚሁ እለትም ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁለም በየአጥቢያችሁ
በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ዓውደ ምሕረት ላይ ባለመቅረት የተለመደውን የእለተ ሰንበት የሥርዓተ ቅዳሴ፤ የጸሎት፣ የምሕላ እና የትምህርተ ወንጌል ከወትሮው በተለየ የመንፈሳዊ ሥርዓት በማከናወን እንድታሳልፉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ የተከበራችሁ ውድ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን፤
ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የጠራውን ሀገር
አቀፍና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰኑ ቀናት
እንዲተላለፍ ያደረገው የአቋም ለውጥ አድርጎ ሳይሆን
አስቀድማ ቤተ ክርስቲያናችን በሮቿን ለሰላም ክፍት በማድረግ ባስተላለፈችው ጥሪ እና በአስቀመጠችው ቀነ ገደብ መሠረት በመንግሥት በኩል ወዲያውኑ ችግሩን ለመፍታት ፍላጎት በማሳየቱ ምክንያት ብቻ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡ ነገር ግን መንግሥት የገባውን ቃል እና የወሰነውን ውሳኔ የማይፈጽም ከሆነ መንፈሳዊ ተጋድሏችን የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ይህ ሂደት በባህሪው ረዥም ተጋድል እና ጽናት የሚጠይቅ
በመሆኑ እስከ አሁንም በፍጹም አንድነት እና መደማመጥ
የቅዱስ ሲኖዶሱን ድምጽ እየሰማችሁ በአንድነት እና በሕብረት እንደቆማችሁት ሁሉ ወደፊትም የቅዱስ ሲኖዶስን ድምጽ በትጋት እንድትጠብቁ እያሳሰብን በሕግ የተያዙት ጉዳዮችም የሕግ ሂደታቸውን ተከትለው የሚቀጥሉ መሆኑን እና እኛም በልዩ ሁኔታ የምናውቃቸው መሆኑን እንገልጻለን፡፡
መንግሥትም የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ተቀብሎ የውይይት
መድረክ በማዘጋጀት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በማክበር
በውሳኔው መሠረት የሚፈጸም መሆኑን ስላረጋገጠልን ቤተ
ክርስቲያን ታመሰግናለች፡፡

በተጨማሪም በዚህ የፈተና ወቅት በየደረጃው የምትገኙ በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም የምትገኙ የቤተ ክርስቲያናችን የሥራ ኃላፊዎች፤ ሉቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ መነኮሳት፤ አገልጋይ ካህናት፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፤ ልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ማህበራት እና መላው ምእመናንና ምዕመናት እንዲሁም ከቤተ ክርስቲያኗ ጎን የቆማችሁ እና አጋርነታችሁን የገለጻችሁ የሃይማኖትተቋማት፤ የሕግ ባለሙያዎች፤ ግለሰቦች፤ የማህበረሰብ አንቂዎች፤ የጥበብ ሰዎች፤ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እና በዚህ ሂደት ውስጥ ድጋፍ ስትሰጡ የነበራችሁ የተለያዩ አካላት ቤተ ክርስቲያን እያመሠገነች ወደፊትም ልዩ ዕውቅና የምትሰጥ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

በመጨረሻም ቅዱስ ሲኖዶስ በጀመረው ፍጹም ሰላማዊ ና ሕጋዊ መንገድ ከመንግሥት ጋር የደረስንበትን ውጤት በየጊዜው የምናሳውቃችሁ ስለሆነ እንደዚህ ቀደሙ ፍፁም በሆነ መንፈሳዊ ጨዋነት የቅዱስ ሲኖዶስን መልእክት እንድትጠባበቁ፤ አሁንም ቢሆን ያለመዘናጋት ቤተ
ክርስቲያናችሁን በጥብቅ ሁኔታ እንድትጠብቁ እና ቤተ
ክርስቲያናችሁ ላይ የሚያጋጥሙትን ችግሮች ሁሉ በተዋረድ
ላለው መዋቅራችሁ እንድታሳውቁ አባታዊ መልእክታችንን
እናስተላልፋለን፡፡
1.0K views10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-11 13:02:19
936 views10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 19:07:43 EOTC Broadcasting service agency
@abisiniya_times
1.3K views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 16:52:31
በአቅራቢያችን ያሉ የሌላ ሀይማኖት ቤተ እምነቶችንም በጥፋት እጆች እንዳይነኩ እንጠብቅ ፤ የክፉዎች ሴራ ብዙ ነውና ።

አሁንም ከአኛ አንዳችም መጥፎ ተግባር እንዳይገኝ በማድረግ ፤ይህን ክፉ መንፈስ አንገቱን እናስደፋው !!
767 views13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 19:41:26
"ምንትስ ይምራ!" የሚሉት እነማን እንደሆኑ ይታወቃል። የብልጽግና ቀሽም ድራማ ከማንም የተሰወረ ስላልሆነ አገር ወዳዱ ኢትዮጵያዊ ምንም ቀሽም ድራማ አያይም፥ አይሰማም!

ብልጽግና "ኢህገዴግ ቁጥር 2" ነው የሚባለው በምክንያት ነው
1.2K viewsedited  16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ