Get Mystery Box with random crypto!

#ፍትህ_ለእህታችን_ፀጋ_በላቸው ! በሐዋሳ ከተማ ከንቲባ የግል ጠባቂ የተጠለፈችው ፀጋ በላቸው | አቢሲኒያ - Times

#ፍትህ_ለእህታችን_ፀጋ_በላቸው !

በሐዋሳ ከተማ ከንቲባ የግል ጠባቂ የተጠለፈችው ፀጋ በላቸው !

የዳሽን ባንክ ሐዋሳ ዋርካ ቅርንጫፍ ሰራተኛ ነች ። ፀጋ በላቸው ትባላለች፤ ለማግባት ጥቂት ጊዜ ቀርቷት በዝግጅት ላይ ነበረች።

ሆኖም ግን ፤ ግንቦት 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ከስራ ወደቤት ስታቀና ፤ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ጠባቂ የሆነው ኮንስታብል የኋላመብራት ወ/ማሪያም ጠልፎ ተሰውሯል ።

ጉዳዩን ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በማሳወቅና የፍርድ ቤት መጥሪያ በማውጣት ተጠርጣሪውን ለመያዝ ቤተሰቦች የቻሉትን ቢያደርጉም ፤የሲዳማ ክልል ፓሊስ ጉዳዩን በቸልተኝነት አለፍ ሲልም ተባባሪ በሚመስል መልኩ ጉዳዮን ይዞት፤ ለባለፉት 7 ቀናት ፀጋ በላቸው የት እንዳለች አናውቅም በማለት ፤ ቤተሰብ ጭንቅት ላይ ነው።
ሼር
#ፍትህ_ለእህታችን_ፀጋ_በላቸው

@abisiniya_times
@abisiniya_times