Get Mystery Box with random crypto!

አቢሲኒያ - Times

የቴሌግራም ቻናል አርማ abisiniya_times — አቢሲኒያ - Times
የቴሌግራም ቻናል አርማ abisiniya_times — አቢሲኒያ - Times
የሰርጥ አድራሻ: @abisiniya_times
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 38.80K
የሰርጥ መግለጫ

Description
• ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
•በአለማችን የተከናወኑ አስደናቂ ክስተቶች፣
•የስፖርት እና መዝናኛ መረጃዎች፣
•24 ሰዓት ትኩስ እና አዳዲስ መረጃ ያገኛሉ፣
•እንዲሁም ጠቅላላ እውቀት፣
ለማንኛውም መረጃ፦
#ለአስተማማኝ የመረጃ ምንጭ
https://t.me/abisiniya_times

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-06 17:42:35
1.9K views14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-06 17:38:42
ጎንደር ከተማ ወደ ቀደሞ እንቅስቃሴዋ ተመልሳለች።

@abisiniya_times
@abisiniya_times
2.0K viewsedited  14:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-05 18:24:44
ጎንደር

አብይ አህመድ በይፋ በአማራ ህዝብ ላይ የከፈተውን ጦርነት በመቃወም በጎንደር የቀጠለው ህዝባዊ እምቢተኝነት!

@abisiniya_times
@abisiniya_times
2.6K views15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 18:58:29 አማራ እያለ ያለው አትግደሉኝ፣ አታፈናቅሉኝ ነው።
እንደሌላው በእኩልነት፣ በሠላም ልኑር ነው እያለ ነው። አለበለዚያ በኔ ሞት፣ ደምና አጥንት የምትበልፅግ ኢትዮጵያ የለችም ነው እያለ ያለው። ይህን ጥያቄውን ጠምዝዞ "ፅንፈኛ" እያሉ ወካይ ስም በመስጠት አድበስብሶ ማለፍ ተገቢ አይደለም።

#ድል_ለሰፊው_ህዝብ!
470 viewsedited  15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 18:10:15 የአማራ ሕዝባዊ እምቢተኝነትና አድማው በተሳካ ሁኔታ ቀጥሏል።

(ከአማራ ሕዝባዊ የሕልውና ትግል ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ - አሕትአኮ የተሰጠ መግለጫ)

በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም የጎንደር ከተማ የሕዝባዊ እምቢተኝነት ውሎ የትግሉ አስኳል ሆኖ ታይቷል።

በጀግኖቹ ቀዬ ጎንደር ፋኖ እና ወጣቱ አውራ መንገዶችን እና መጋቢ መንገዶችን ሙሉ በሙሉ ዘግቷል። ከተፈቀደላቸው ዳቦ ቤቶች፣ አምቡላንስ፣ ክሊኒኮች፣ ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች በስተቀር፣ ሌሎች ተቋማትና የንግድ ድርጅቶች ለሁለት ቀናት ዝግ ሆነው እንደሚቀጥሉ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴው ወስኗል። በተመሳሳይ በሸዋ ያለውም ከጎንደሩ ህዝባዊ እምብኝተኝነት ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሁኖ አግኝተነዋል።

የሸዋ ተጋድሎ ውሎ!

ሰሞኑን የአማራ ሕዝብ እየደረሰበትን ያለ ግፍ የደብረሲና፣ የሸዋሮቢት፣ የራሳ፣ የአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ጀግኖች ማጀቴን ጨምሮ አገዛዙን ልጆቻችን አናስነካም በማለት ፊት አዙረው የሞት የሽረት ትግል ሲያደርጉ ውለዋል። በቀጣይ ቀናትም ሕዝባዊ እንቢተኝነቱ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። በቀጣይም ከሚያዝያ 28 ጀምሮ በመላው አማራ ህዝባዊ እምብተኝነቱ አድማሱን አስፍቶ ይቀጥላል።

ይህን ትዕዛዝ ለመጣስ የሞከሩ ካፌዎችና ሱቆች መልሰው እንዲዘጉ ካደረገ በኋላ ከሰአት ሁሉም ተቋማት፣ የንግድ ድርጅቶችና ተሽከርካሪዎች ከእንቅስቃሴቸው በመታቀብ ለኮሚቴው ያላቸውን ታማኝነት አረጋግጠዋል።

አድማው በነገው ዕለትም ይቀጥላል።

በዛሬው ለህልውና በሚደረገው የአድማና የሕዝባዊ እምቢተኝነት ውሏችን የተረዳነው ሀቅ መከላከያ ወደ ሕዝባችን የመተኮስ ፍላጎት የለውም። ነገር ግን ኦነጋዊ የኦህዴድ ወታደራዊ አመራሮች ሕዝብ ላይ እንዲተኮስ ከፍተኛ ግፊት ሲያደርጉ ታይተዋል። በዚህም መሀል ፒያሳ ላይ አንድ ሻለቃ ኃይል የተኩስ እሩምታ ከፍቶ ሁለት ወጣቶች ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል።

ፋኖና ወጣቱ ወሳኝ በሚባሉ የከተማው ስትራቴጂያዊ ስፍራዎች ላይ ስራቸውን በመስራት ላይ ናቸው። ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ መነቃቃት አለ።

በሰሞነኛው የአማራ የህልውና ተጋድሎ ድንጋጤ ውስጥ የገባው ዐቢይ አህመድ የግል ካምፓኒው የሆነውን ብልጽግናን አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ተሰምቷል። የፋሽስቱ ጠቅላይ ምንም ዓይነት ውሳኔ ቢወስን የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል እስከ ነፃነት ድረስ ተጠናክሮ ከመቀጠል ውጪ አማራጭ የለውም።

ሁሉም ሰው ለህልውና ትግሉ የራሱ የሆነ ሚና አለው።

የአማራ ሕዝብ ከገባበት የህልውና አደጋ መውጣት የሚችለው ቢያንስ በአሁን ወቅት አማራጭ ካለመኖሩ አኳያ በክንዱ ብቻ ነው።

ሁሉም ልጆቹ እንደየ መክሊታቸው በህልውና ትግሉ ላይ የራሳቸውን አሻራ ሊያሳርፉ ይገባል።

በቅድሚያ

︎የአማራ ህዝብ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ወሳኝ ደጀን ቀኝ እጅ ነው። ይህንንም በሰሜኑ ጦርነት አብሯቸው በመውደቅም ሆነ የሚያስፈልጋቸውን በማቅረብ በተግባር አሳይቷል። ስለሆነም የሕዝባችን የህልውና ትግል አማራን ለማጥፋት ከሚሰሩ ገዥዎች ጋር እንጂ፣ ከጭቁኑ ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ አብራክ ከወጣው ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር አይደለም።

በመሆኑም የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል የሆናችሁ የኢትዮጵያ ልጆች የክፉ ቀን ደራሽ ጋሻና መከታችሁ ወደሆነው የአማራ ሕዝብ አፈሙዝ ከማዞር ተቆጥባችሁ የህልውና ትግሉን እንድትቀላቀሉ አልያም መንግስት የዘረጋውን የጥፋት እጁን እነዲሰበስብ ታስገድዱ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

1) የአማራ ብሄር ተወላጅ ያልሆናችሁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ ለጥቂት የኦህዴድ ገዥዎች ፍላጎት ብላችሁ ያበላና ያጠጣችሁን፤ ቁስላችሁን የጠረገና ያስታመማችሁ የአማራ ሕዝብ ላይ አፈሙዝ ልታዞሩበት ስለማይገባ ከህሊናችሁ ጋር ትመክሩ ዘንድ እንጠይቃለን።

2) በሰራዊቱ ውስጥ ሰፊ ቁጥር ያላችሁ የኦሮሞ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ልጆች በዚህ የኦሕዴድ ፅንፈኞች ሴራ ተጠልፋችሁ ወገናችሁ ላይ ቃታ እንዳትከፍቱ ታሪካዊ አደራ አለባችሁ። ለምን? በሉ! እምቢ በሉ! መፍትሄ ካልሰጧችሁ አንድም ለጊዜው ካምፓችሁን መልቀቅ፣ ሁለትም የሕዝቡን የህልውና ትግል ተቀላቅላችሁ መንግስት ተገድዶ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ እንዲመጣ የምናደርገውን ትግል አግዙ!!!

3) የአማራ ተወላጅ የሆናችሁ የመከላከያ አባላት፣ ዘመቻው ከህግ ማስከበርም ሆነ ከትጥቅ ማስፈታት ጋር ስለማይገናኝ፣ ይልቁንም አማራን ለማጥፋት እና መንግስት በገጠመው የዶላር እጥረት የተነሳ የምዕራባውያንን ተልዕኮ ለማስፈጸም የጀመረው በመሆኑ ውስጥ ሆናችሁ ምን መስራት እንዳለባችሁ ታውቁታላችሁ።

4) የአማራ ተወላጅ የሆናችሁ የመስመር ኃይሎችና ወታደራዊ መኮንኖች ትክሻችሁ ላይ የወደቀውን ታሪካዊ ኃላፊነት በጥንቃቄ ልትወጡት ይገባል። ወደ ሕዝብ የሚተኩስ ወታደር ደጀን የለውምና፣ የምትመሩትን ሰራዊት ለኦህዴድ ሳይሆን ለኢትዮጵያና ለመላ ሕዝቧ ዘብ እንዲቆም ማድረግ አለባችሁ።

5) የአማራ ልዮ ኃይል፣ ፋኖና ወጣቶች ለህልውናችን ስንል የአርበኛ የአባቶቻችንን ታሪክ የምንደግምበት ጊዜው አሁን መሆኑን አውቃችሁ ትግሉን ያልተቀላቀላችሁ በፍጥነት እንድትቀላቀሉ ጥሪው ቀርቦላችኋል።

6) የአማራ ልጆች የሆናችሁ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች በሁሉም የሚዲያ አማራጮች የአማራ ሕህብን የትግል እውነቶች ለሌሎች እንድታስረዱና የወገናችሁ ድምጽ እንድትሆኑ በድጋሚ ጥሪ ቀርቦላችኋል። የጋራ ትግል መመሪያ በማዘጋጀት ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ እንዲቀጣጠል የትውልድ አሻራችሁን ተወጡ!

7) የአማራ ብልጽግና አመራሮችና ካድሬዎች በአሁኑ ወቅት በህዝብ ተቀባይነት በሌላው መንግሥት ውስጥ ሆናችሁ ሕዝባችሁን ድጋሚ ብትክዱ ከእነ ቤተሰባችሁ አደጋ ላይ ትወድቃላችሁ። ስለዚህም በጊዜ ሰልፋችሁን አስተካክሉ።

8) የአማራ ሚሊሻዎች አፈሙዛችሁን ወደማን ማዞር እንዳለባችሁ ከልጆቻችሁ ፋኖዎች ጋር ምከሩ። ፋኖ ልጅህ ነው። አባት ከልጁ ጎን መሰለፍ ደግሞ የአባት አደር ወጉ ነው።

***
የአማራ ሕዝባዊ የህልውና ተጋድሎ ያሸንፋል!!

የመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነትና እኩልነት እስከሚረጋገጥ ድረስ ትግሉ አይቆምም!!

የአማራ ሕዝባዊ የሕልውና ትግል ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ (አሕትአኮ)

(ማሳሰቢያ፦ የትግሉ ምዕራፍ እያደገ መልክና ቅርጹን እየጨመረ የሚሄድ በመሆኑ ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎችን እናሳውቃለን)

ድል ለአማራ !

@abisiniya_times
@abisiniya_times
708 views15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 18:08:54
649 views15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 16:30:43
ሰበር!

የዐቢይ አህመድ ጦር በጎንደር ወደ ሕዝብ ተኮሰ!

አማራን ለማስገበር የተላከው የዐቢይ አህመድ ጦር በዛሬው ዕለት በጎንደር አማራዎች ላይ ተኩስ ከፍቷል። በተከፈተው ተኩስም በርካታ ንጹሃን መገደላቸው ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

የጎንደር ሕዝብም የተከፈተበትን ወረራ ለመቀልበስ ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረገ መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

የአማራ ሕዝባዊ እንቢተኝነት መሪዎች እና የጎንደር ወጣቶች ወደ ጎንደር የሚያስገቡ በሮች ሁሉ እንዲዘጉ እና አማራዊ ግዴታውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

"ተአማኒ እና ፈጣን መረጃ እንዲደርሶ ቻናሉን ይቀላቀሉ ለሌሎችም #ሼር አድርጉ"

ድል ለአማራ ! #Share

@abisiniya_times
@abisiniya_times
@abisiniya_times
1.1K viewsedited  13:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 15:33:48
በህዝባችን ታሪክ መድፍና ታንክ አይደለም በጀትና በከባባድ መሳሪያዎችም ጦርነት ብርቁ አይደለም።

የጉሬላ ውጊያ ለአማራ ሲከፋው ሸፍቶ የሚኖርበት ሀገር ስትወረር ታጥቆ የሚገጥምበት አብሮት ያደገ ነፍጨኝነት ነው።

መንግስት ነን ለሚሉ ደሞ የጉሬላ ተዋጊ ዘላለማዊ ሰላማቸውን የሚነሳ የውጊያ ስልት ነው።

ለዚህ ደሞ ቅርቡ ማሳያ የኢትዮ ጣልያን ወረራና የአማራ ተጋድሎ ጅማሮ 2008 ትልቅ ማሳያዎች ናቸው!!!

እልፍ ሰራዊት ሺ ታንክ ብትደረድሩ ህዝብን ማንበርከክ አትችሉም ትወድቃላችሁ ወይ የመጨረሻ ካርዳችሁን ሀገሪቷን በትናችሁ ትገነጠላላችሁ በጋራ የምናየው ነው።

@abisiniya_times
1.1K viewsedited  12:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 15:24:24
በአዲስ አበባ የአማራ ተወላጅ አፈሳ ተጀመረ
የፀጥታ መዋቅር ውስጥ ያሉ አማሮች ከስብሰባ እንዲታገዱ ተደረገ።
በአማራ ሕዝብ የተጀመረው መጠነ ሰፊ ጦርነት ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የአማራ ተወላጅ እየታሰሩ መሆኑ ተሰምቷል።

በፖሊስ የፀጥታ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አማሮች ከተለያየ ስብሰባዎች እና ከአመራር ቦታዎች እንዲታገዱ ትህዛዝ መተላለፉ የፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል። በአዲስ አበባ መታወቂያ እየታየ የጅምላ አፈሳዉ ቤት ለቤት ሊቀጥል መሆኑ ከውስጥ የተገኘ ጥቆማ ታውቋል እስካሁን በልደታ ሽሮሜዳ ፈረንሳይ አካባቢ የጅምላ አፈሳ እንደቀጠለ ሲሆን በባጃጅና ሞተር ስራ የሚተዳደሩ ወጣቶች በአማራነታቸው ብቻ ፋኖ ናቸው በማለት የእስር ዘመቻ ተጀምሯል ።

በኦህዴድ/ብልፅግና በአማራ ተወላጆች ላይ የተጀመረው ማሳደድ ከሁለት አመት በፊት በትግራይ ተወላጆች ሲፈጽም የነበረው ማሳደድ ቀጣይ ክፍል በአማራ ላይ መጀመሩ ነዋሪዎች የገለጹ ሲሆን ለማይቀረው የህልውና ትግል ሁሉም አማራ መዘጋጀት አለበት ብለዋል።

ምንጭ ፦አሻራ ሚዲያ

@abisiniya_times
1.1K viewsedited  12:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 15:19:55
#ጎንደር እምቢተኝነቱ ቀጥሏል።

@abisiniya_times
1.0K views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ