Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ የአማራ ተወላጅ አፈሳ ተጀመረ የፀጥታ መዋቅር ውስጥ ያሉ አማሮች ከስብሰባ እንዲታገዱ | አቢሲኒያ - Times

በአዲስ አበባ የአማራ ተወላጅ አፈሳ ተጀመረ
የፀጥታ መዋቅር ውስጥ ያሉ አማሮች ከስብሰባ እንዲታገዱ ተደረገ።
በአማራ ሕዝብ የተጀመረው መጠነ ሰፊ ጦርነት ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የሚኖሩ የአማራ ተወላጅ እየታሰሩ መሆኑ ተሰምቷል።

በፖሊስ የፀጥታ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ አማሮች ከተለያየ ስብሰባዎች እና ከአመራር ቦታዎች እንዲታገዱ ትህዛዝ መተላለፉ የፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል። በአዲስ አበባ መታወቂያ እየታየ የጅምላ አፈሳዉ ቤት ለቤት ሊቀጥል መሆኑ ከውስጥ የተገኘ ጥቆማ ታውቋል እስካሁን በልደታ ሽሮሜዳ ፈረንሳይ አካባቢ የጅምላ አፈሳ እንደቀጠለ ሲሆን በባጃጅና ሞተር ስራ የሚተዳደሩ ወጣቶች በአማራነታቸው ብቻ ፋኖ ናቸው በማለት የእስር ዘመቻ ተጀምሯል ።

በኦህዴድ/ብልፅግና በአማራ ተወላጆች ላይ የተጀመረው ማሳደድ ከሁለት አመት በፊት በትግራይ ተወላጆች ሲፈጽም የነበረው ማሳደድ ቀጣይ ክፍል በአማራ ላይ መጀመሩ ነዋሪዎች የገለጹ ሲሆን ለማይቀረው የህልውና ትግል ሁሉም አማራ መዘጋጀት አለበት ብለዋል።

ምንጭ ፦አሻራ ሚዲያ

@abisiniya_times