Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ሕዝባዊ እምቢተኝነትና አድማው በተሳካ ሁኔታ ቀጥሏል። (ከአማራ ሕዝባዊ የሕልውና ትግል | አቢሲኒያ - Times

የአማራ ሕዝባዊ እምቢተኝነትና አድማው በተሳካ ሁኔታ ቀጥሏል።

(ከአማራ ሕዝባዊ የሕልውና ትግል ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ - አሕትአኮ የተሰጠ መግለጫ)

በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም የጎንደር ከተማ የሕዝባዊ እምቢተኝነት ውሎ የትግሉ አስኳል ሆኖ ታይቷል።

በጀግኖቹ ቀዬ ጎንደር ፋኖ እና ወጣቱ አውራ መንገዶችን እና መጋቢ መንገዶችን ሙሉ በሙሉ ዘግቷል። ከተፈቀደላቸው ዳቦ ቤቶች፣ አምቡላንስ፣ ክሊኒኮች፣ ጤና ጣቢያዎችና ሆስፒታሎች በስተቀር፣ ሌሎች ተቋማትና የንግድ ድርጅቶች ለሁለት ቀናት ዝግ ሆነው እንደሚቀጥሉ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴው ወስኗል። በተመሳሳይ በሸዋ ያለውም ከጎንደሩ ህዝባዊ እምብኝተኝነት ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሁኖ አግኝተነዋል።

የሸዋ ተጋድሎ ውሎ!

ሰሞኑን የአማራ ሕዝብ እየደረሰበትን ያለ ግፍ የደብረሲና፣ የሸዋሮቢት፣ የራሳ፣ የአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ ጀግኖች ማጀቴን ጨምሮ አገዛዙን ልጆቻችን አናስነካም በማለት ፊት አዙረው የሞት የሽረት ትግል ሲያደርጉ ውለዋል። በቀጣይ ቀናትም ሕዝባዊ እንቢተኝነቱ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። በቀጣይም ከሚያዝያ 28 ጀምሮ በመላው አማራ ህዝባዊ እምብተኝነቱ አድማሱን አስፍቶ ይቀጥላል።

ይህን ትዕዛዝ ለመጣስ የሞከሩ ካፌዎችና ሱቆች መልሰው እንዲዘጉ ካደረገ በኋላ ከሰአት ሁሉም ተቋማት፣ የንግድ ድርጅቶችና ተሽከርካሪዎች ከእንቅስቃሴቸው በመታቀብ ለኮሚቴው ያላቸውን ታማኝነት አረጋግጠዋል።

አድማው በነገው ዕለትም ይቀጥላል።

በዛሬው ለህልውና በሚደረገው የአድማና የሕዝባዊ እምቢተኝነት ውሏችን የተረዳነው ሀቅ መከላከያ ወደ ሕዝባችን የመተኮስ ፍላጎት የለውም። ነገር ግን ኦነጋዊ የኦህዴድ ወታደራዊ አመራሮች ሕዝብ ላይ እንዲተኮስ ከፍተኛ ግፊት ሲያደርጉ ታይተዋል። በዚህም መሀል ፒያሳ ላይ አንድ ሻለቃ ኃይል የተኩስ እሩምታ ከፍቶ ሁለት ወጣቶች ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል።

ፋኖና ወጣቱ ወሳኝ በሚባሉ የከተማው ስትራቴጂያዊ ስፍራዎች ላይ ስራቸውን በመስራት ላይ ናቸው። ከፍተኛ የሆነ የሕዝብ መነቃቃት አለ።

በሰሞነኛው የአማራ የህልውና ተጋድሎ ድንጋጤ ውስጥ የገባው ዐቢይ አህመድ የግል ካምፓኒው የሆነውን ብልጽግናን አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ተሰምቷል። የፋሽስቱ ጠቅላይ ምንም ዓይነት ውሳኔ ቢወስን የአማራ ሕዝብ የህልውና ትግል እስከ ነፃነት ድረስ ተጠናክሮ ከመቀጠል ውጪ አማራጭ የለውም።

ሁሉም ሰው ለህልውና ትግሉ የራሱ የሆነ ሚና አለው።

የአማራ ሕዝብ ከገባበት የህልውና አደጋ መውጣት የሚችለው ቢያንስ በአሁን ወቅት አማራጭ ካለመኖሩ አኳያ በክንዱ ብቻ ነው።

ሁሉም ልጆቹ እንደየ መክሊታቸው በህልውና ትግሉ ላይ የራሳቸውን አሻራ ሊያሳርፉ ይገባል።

በቅድሚያ

︎የአማራ ህዝብ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ወሳኝ ደጀን ቀኝ እጅ ነው። ይህንንም በሰሜኑ ጦርነት አብሯቸው በመውደቅም ሆነ የሚያስፈልጋቸውን በማቅረብ በተግባር አሳይቷል። ስለሆነም የሕዝባችን የህልውና ትግል አማራን ለማጥፋት ከሚሰሩ ገዥዎች ጋር እንጂ፣ ከጭቁኑ ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ አብራክ ከወጣው ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር አይደለም።

በመሆኑም የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባል የሆናችሁ የኢትዮጵያ ልጆች የክፉ ቀን ደራሽ ጋሻና መከታችሁ ወደሆነው የአማራ ሕዝብ አፈሙዝ ከማዞር ተቆጥባችሁ የህልውና ትግሉን እንድትቀላቀሉ አልያም መንግስት የዘረጋውን የጥፋት እጁን እነዲሰበስብ ታስገድዱ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

1) የአማራ ብሄር ተወላጅ ያልሆናችሁ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፣ ለጥቂት የኦህዴድ ገዥዎች ፍላጎት ብላችሁ ያበላና ያጠጣችሁን፤ ቁስላችሁን የጠረገና ያስታመማችሁ የአማራ ሕዝብ ላይ አፈሙዝ ልታዞሩበት ስለማይገባ ከህሊናችሁ ጋር ትመክሩ ዘንድ እንጠይቃለን።

2) በሰራዊቱ ውስጥ ሰፊ ቁጥር ያላችሁ የኦሮሞ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ልጆች በዚህ የኦሕዴድ ፅንፈኞች ሴራ ተጠልፋችሁ ወገናችሁ ላይ ቃታ እንዳትከፍቱ ታሪካዊ አደራ አለባችሁ። ለምን? በሉ! እምቢ በሉ! መፍትሄ ካልሰጧችሁ አንድም ለጊዜው ካምፓችሁን መልቀቅ፣ ሁለትም የሕዝቡን የህልውና ትግል ተቀላቅላችሁ መንግስት ተገድዶ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ እንዲመጣ የምናደርገውን ትግል አግዙ!!!

3) የአማራ ተወላጅ የሆናችሁ የመከላከያ አባላት፣ ዘመቻው ከህግ ማስከበርም ሆነ ከትጥቅ ማስፈታት ጋር ስለማይገናኝ፣ ይልቁንም አማራን ለማጥፋት እና መንግስት በገጠመው የዶላር እጥረት የተነሳ የምዕራባውያንን ተልዕኮ ለማስፈጸም የጀመረው በመሆኑ ውስጥ ሆናችሁ ምን መስራት እንዳለባችሁ ታውቁታላችሁ።

4) የአማራ ተወላጅ የሆናችሁ የመስመር ኃይሎችና ወታደራዊ መኮንኖች ትክሻችሁ ላይ የወደቀውን ታሪካዊ ኃላፊነት በጥንቃቄ ልትወጡት ይገባል። ወደ ሕዝብ የሚተኩስ ወታደር ደጀን የለውምና፣ የምትመሩትን ሰራዊት ለኦህዴድ ሳይሆን ለኢትዮጵያና ለመላ ሕዝቧ ዘብ እንዲቆም ማድረግ አለባችሁ።

5) የአማራ ልዮ ኃይል፣ ፋኖና ወጣቶች ለህልውናችን ስንል የአርበኛ የአባቶቻችንን ታሪክ የምንደግምበት ጊዜው አሁን መሆኑን አውቃችሁ ትግሉን ያልተቀላቀላችሁ በፍጥነት እንድትቀላቀሉ ጥሪው ቀርቦላችኋል።

6) የአማራ ልጆች የሆናችሁ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች በሁሉም የሚዲያ አማራጮች የአማራ ሕህብን የትግል እውነቶች ለሌሎች እንድታስረዱና የወገናችሁ ድምጽ እንድትሆኑ በድጋሚ ጥሪ ቀርቦላችኋል። የጋራ ትግል መመሪያ በማዘጋጀት ሕዝባዊ እምቢተኝነቱ እንዲቀጣጠል የትውልድ አሻራችሁን ተወጡ!

7) የአማራ ብልጽግና አመራሮችና ካድሬዎች በአሁኑ ወቅት በህዝብ ተቀባይነት በሌላው መንግሥት ውስጥ ሆናችሁ ሕዝባችሁን ድጋሚ ብትክዱ ከእነ ቤተሰባችሁ አደጋ ላይ ትወድቃላችሁ። ስለዚህም በጊዜ ሰልፋችሁን አስተካክሉ።

8) የአማራ ሚሊሻዎች አፈሙዛችሁን ወደማን ማዞር እንዳለባችሁ ከልጆቻችሁ ፋኖዎች ጋር ምከሩ። ፋኖ ልጅህ ነው። አባት ከልጁ ጎን መሰለፍ ደግሞ የአባት አደር ወጉ ነው።

***
የአማራ ሕዝባዊ የህልውና ተጋድሎ ያሸንፋል!!

የመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነፃነትና እኩልነት እስከሚረጋገጥ ድረስ ትግሉ አይቆምም!!

የአማራ ሕዝባዊ የሕልውና ትግል ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ (አሕትአኮ)

(ማሳሰቢያ፦ የትግሉ ምዕራፍ እያደገ መልክና ቅርጹን እየጨመረ የሚሄድ በመሆኑ ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎችን እናሳውቃለን)

ድል ለአማራ !

@abisiniya_times
@abisiniya_times