Get Mystery Box with random crypto!

እስኪ ባህር ማዶ ዘልቀን ትንሽ ስለ ቱርክ አሁናዊ ሁኔታ.. ቱርክ ጋር የማንስማማባቸው የፓለቲካ | አቢሲኒያ - Times

እስኪ ባህር ማዶ ዘልቀን ትንሽ ስለ ቱርክ አሁናዊ ሁኔታ..

ቱርክ ጋር የማንስማማባቸው የፓለቲካ ኩነቶች ቢኖሩም ለህዝቡ ለአገሩ በሚታመን እንደ ኤርዶጋን አይነት መሪ ስታይ አለመቅናት አንችልም። የፓለቲካ ልዩነታችን እንዳለ ሆኖ ለቱሩኩ መሪ ኤርዶጋን አድናቆታችን ላቅ ያለ ነው። የቱሩኩ መሪ ኤርዶጋን ከመነሻ አስተዳደጉ ጥሮ ግሮ ተምሮ እስከ ህዝብ መሪ የደረሰበት ውጣ ውረድ የሚያስተምር ቢሆንም በመሪነት ዘመኑ ግን አገሩን ወደ ከፍታ የወሰደበት ጥበቡ እጅግ የሚደነቅና የሚያስተምር ነው።

ኤርዶጋን ዛሬ ላይ አገሩ ቱርክን በፓለቲካ፣ በድፕሎማሲ፣ በኢኮኖሚ፣ በቱሪዝሙ ብቻ በሁሉም መስክ ከኃያላን አገር ተርታ አሰልፏታል። ኤርዶጋን ቱርክን በሁሉም መልክ ከኃያላን አገር ትከሻ ለትከሻ እንድትለካካ ስላደረጋት፤ ሰሞኑን የቱርክ ምርጫ የአለምን ቀልብ እንዲስብ ሆኗል። ምዕራባውያን የሚገዳደራቸውን መሪ እልባት ሊሰጡት የተለያየ ስልቶችን ሳይጠቀሙ እንዳልቀሩ የሚድያዎቻቸው ፕሮፓጋንዳ ያሳብቃል። የሆነው ሆኖ ህዝብ አይሳሳትም የሚለው ብሂል እውነታን ያረጋገጡ ቱርካውያን ለመሪያቸው ውለታ መልስ ይሆን ዘንድ ካርዳቸውን ለመሪያቸው ሰጥተዋል። የቱርኩ መሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጤና እክል ቢገጥመውም የቱርክ ህዝብ በጤናው መቃወስ ቢጨነቅም ለመሪያቸው ታመነው ተገኝተዋል።

የጥንቷ ቱርክ ገናና ታሪክ የነበራት ሲሆን በጥቂት ዘመናት በፊት የነበረች ቱርክ ደግሞ አቅመ ቢስነት የተጣባት ሆና ትታይ ነበር። የሆነው ሆኖ ከባዶ ወደ ከፍታ ማማ የመለሰ፤ የገናናዋን ቱርክ ታሪክ እንዲታደስ ያደረገ መሪ ኤርዶጋን መሆኑ አለም ይመሰክርለታል። የተዘነጋች ቱርክን ወደ ጥንተ ከፍታዋ የመለሳት መሪን ዳግም ለ5 ዓመት እንዲመራቸው ቱርካውያን መርጠውታል።

በእውነቱ በህዝቡም በመሪውም አለመቅናት አይቻልም!

@abisiniya_times