Get Mystery Box with random crypto!

ልዩ መረጃ ኦሮሚያ ክልል ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በኦነግ ሸኔ ቁጥጥር ውስጥ | አቢሲኒያ - Times

ልዩ መረጃ

ኦሮሚያ ክልል ሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በኦነግ ሸኔ ቁጥጥር ውስጥ ሆኗል።

በሆሮጉድሩ 14 የመንግስት ባለስልጣናት በታጣቂው ኃይል መገደላቸውን ከአካባቢው ባገኘነው መረጃ መሰረት አረጋግጠናል።

በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በሚገኘው ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት፤ 11 የፋብሪካው ሰራተኞች እና ሶስት የአካባቢው ነዋሪዎች እንደተገደሉ እና ፋብሪካው በተፈጸመበት በዚሁ ጥቃት እና ዘረፋ ምክንያት ስራ ማቋሙንም የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” መግለጹ ይታወሳል።

ከአዲስ አበባ በ350 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኘው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ላይ ጥቃቱ የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ግንቦት 12 ቀን 2015 መሆኑን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ የህዝብ ግንኙነት እና ተሳትፎ ክፍል ኃላፊ አቶ ረታ ደመቀ ናቸው የገለጹት

እንዲሁም የአርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካም በታጣቂው ስር ቁጥጥር ስር እንደሚገኝ ታውቋል።

በቦታው የነበረው መከላከያ "ከላይ በመጣ ትዕዛዝ " እንዲሸሽ ተደርጎ አካባቢው ለሸኔ ተላልፎ እንደተሰጠ ነዋሪዎች እና አመራሮች ተናግረዋል።

የመከላከያውን መውጣት የተመለከቱ እና ስጋት ያደረባቸው የአካባቢው ነዋሪችም ወደ ሌላው ወለጋ አካባቢ እና ምዕራብ ሸዋ እየተሰደዱ ይገኛሉ።

ሆኖም የሕዝብ ጭፍጨፋና ማፈናቀል፣ የአመራር ግድያ እና የተቋማት ውድመት የሚፈፅመው የኦሮሚያ ታጣቂ ባለበት ከአገር መከላከያ ጋር ሆኖ ለሕዝብና አገር የሞተው የአማራ ፋኖ እና ልዩ ኃይል ላይ "የማፅዳት ዘመቻ" በሚል ጦርነት ከከፈቱ አንድ ወር ተቆጥሯል።

ምንጭ ፦ ጋዜጠኛ ሙልጌታ አንበርብር

@abisiniya_times
@abisiniya_times