Get Mystery Box with random crypto!

ባህር ዳር አሁን! ከባህር ዳር ከተማ ዙሪያ እና አካባቢው የተሰባሰቡ የአማራ ገበሬዎች በድጋሚ በ | አቢሲኒያ - Times

ባህር ዳር አሁን!

ከባህር ዳር ከተማ ዙሪያ እና አካባቢው የተሰባሰቡ የአማራ ገበሬዎች በድጋሚ በአፈር ማዳበሪያ እጦት ምክንያት መሬታችን ጦም ሊያድር ነው ።እህል መዝራት አልቻልንም በማለት በአሁኑ ሰዐት በባህር ዳር ከተማ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው ።

የከተማው ህዝብ ከገበሬዎች ጎን ፤ከወገኖቻችን ጎን የመሆን ታሪካዊም ፣የሞራልም እንዲሁም የውዴታ ግዴታ ነው ።ነገ ይህ አርሶ አደር ካላመረተ ፣የምርት እጥረት ይገጥማል የዚህ ችግር ዋና ገፈት ቀማሹ የከተሜው ህዝብ ነው ።

የአማራ ወጣቶች ማህበር(አወማ) ከአማራ አርሶ አደሮች ጎን ነን ።የአማራ ገበሬዎችን ሆን ተብሎ ለማደኸየት ፣ለማጎሳቆል እና ለማስገበር የሚደረግ የስርዓቱ ሴራ በፅኑ እናወግዛለን ።

የአማራ ወጣቶች ማህበር(አወማ)
@abisiniya_times