Get Mystery Box with random crypto!

ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የሰርጥ አድራሻ: @zdfitsumkebe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.71K
የሰርጥ መግለጫ

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-12-05 17:05:14 "ቤተ ክርስቲያን የምትታገሰው እንደ ሀገር ስለምታስብ መሆኑን መልአክ ሕይወት ቆሞስ አባ ወልደኢየሱስ ሰይፉ ገለጹ"።
*********

ሕዳር ፳፮ ቀን ፳፻ ወ፲፭ ዓ.ም
""""""""""""""""""""""""""""
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
******
ይህ የተገለጸው መልአከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ሰይፉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቋሚና ጊዜያዊ ፕሮጀክት መምሪያ ኃላፊ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ለሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ ነው።

መልአከ ሕይወት በመግለጫቸው ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለይቶ ማየት እስከማይቻል ድረስ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ እድገት ያበረከተችው አበርክቶ እጅግ ትልቅ እንደነበር አስታውሰዋል።

በሀገራዊና በልማት ጉዳይ ላይም ከሌሎች የሀይማኖት ተቋማት ጋርም በመሆን እየሠራች እንደምትገኝ አስታውሰዋል።

በአሁኑ ጊዜ የሚታየውና የሚነገረው ክብረ ነክ ነገር ለቤተ ክርስቲያን አይገባትም ያሉት መልአከ ሕይወት አባ ገብረ ኢየሱስ ሰይፉ በሃይማኖት ሽፋን የሚደረገው ሕገወጥ ድርጊት እጅግ የሚያሳዝን ነው ሲሉም አክለው ገልጸዋል።

ተአምረ ማርያም ቤተ ክርስቲያናዊ መሠረት ያለው መጽሐፍ መሆኑን የገለጹት መልአከ ሕይወት ሰሞኑን በመጽሐፉ ዙሪያ የተሰጠው ትችት ተገቢ ያልሆነና በሕግ የሚያስጠይቅ ተግባር ነው ብለዋል።

እየጠፋን ዝም ብለን የምንታገስ አይሆንም። ቤተ ክርስቲያን ትዕግሥት የምታበዛው መልስ መስጠት አቅቷት ሳይሆን እንደ ሀገር ስለምታስብ ነው። በመሆኑም እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ በጥብቅ እናሳስባለን ብለዋል።

በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አንዱ የአንዱን ሃይማኖት እያከበረ እንዲኖር በሕግ የተቀመጠ ቢሆንም ቤተክርስቲያን የማንንም ድንበር አላፋ ባልሄደችበት ሁኔታ የቤተክርስቲያንን ድንበር አለፈው ለሚመጡ አካላት ተቋሙ በአለው አሰራርና የሥነ ምግባር ደንብ መሰረት ሊጠይቃቸው ይገባል ብለዋል።

በማያያዝም ቤተ ክርስቲያን ሚዛናዊ ሥራ እየሠራችና ሌሎቹን እያከበረች ባለችበት ሁኔታ በሀይማኖት ካባ ተደብቀው ሰላም ሲሆን የማይወዱ አካላት ቤተ ክርስቲያንን የማይገባት ስም እየሠጡ ይገኛሉ። ይህ አግባብም የሚያዛልቅም አይደለም ብለዋል።

እኛ ሌላውን አልነካንም ሌላው ለምን ይነካናል? ቤተ ክርስቲያን የማንም ሥጋት ሆና አታውቅም ሌሎች ሲነሱባት ግን መንግሥት ዝም ማለት የለበትም ሲሉ ሕግና ሥራአት እንዲከበር አሳስበው የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤም በአስቸኳይ ተሰብስቦ ጉዳዩን እንደሚያወግዝና እልባት እንደሚሰጥ እንጠብቃለን ሲሉ መግለጫቸውን አጠቃለዋል ።
2.5K views✞£iŧsûm✞, 14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 17:04:57
2.1K views✞£iŧsûm✞, 14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 08:20:27 ውሻ ምን አገባት ከሰው እርሻ!?
--
በአውደልዳይ (ይቅርታ) በአገልጋይ ዮናታን አክ-ሊሉ ድርጊት ዘሪያ፥ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጠበቅ ያለ የቅሬታ ደብዳቤ፣ ከብሮድካስት ባለሥልጣንና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ጉባኤ ጠንካራ ተግሣጽ እንጠብቃለን። ሰውየው በቁርዓን ላይ ቢያደርገው ምን እንደሚጠብቀው ያውቃል። በካህን ደረጃ የሚነበብን፣ በትውፊታውያን አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ያለን መጽሐፍ፣ አማኞች በሌሉበት፣ ዐይን ላወጣ ሳቅና ስላቅ ማዋል በእርግጥ የአስተዳደግ በደል ማሳያ ነው። ውርጋጥ! ውሻ ምን አገባት ከሰው እርሻ! ድርጊቱ በወንጀልም በፍትሐ ብሔርም ያስጠይቃል።
--
ምሥጢረ ሥጋዌን በክሮሞዘም X እና Y ሊተነተን ሲጋጋጥ የነበረ አውደልዳይ በሚመጥነው ቦታ ሊቀመጥ ይገባል። "አትርሱኝ ነው" እየተባለ ቢታለፍም ሰውዬው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ማነወሩን እንጀራ ማብሰያ አድርጎታል።
--
(እናክርረው ካልን) ቴክኒካሊ፥ እነ ዮናታንና ተዛማጅ የብልፅግና ወንጌል ሰባቂዎች የሚሰብኩት ኢየሱስ ለእኔ የቀራንዮው ወይም የናዝሬቱ ወይም የቆሮንቶሱ ኢየሱስ አይደለም። ጣዖት ነው! በእነርሱ ሥጋዊ ምኞትና ፍትወት ልክ የሚገለገሉበት ጣዖት። ተከባብሮ የመኖር ቀይ መስመር በአጉራ ዘለሎች እየተጣሰ ነው! የፍትሕ ጎማ ትሽከርከር!!!

~በአማን ነጸረ~
1.1K views✞£iŧsûm✞, 05:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 21:04:11
እንኳን ደስ አላችሁ በዩቲዩብ የምናውቀው #ማኅቶት_ቲዩብ አሁን ደግሞ በቴሌግራም መጥታል ለመቀላቀል ከስር Join የሚለውን ንኩት።

https://t.me/+SLPMr-p0D_QzRyzI
57 views✞£iŧsûm✞, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 17:49:27 የቴሌግራም ቻናሎች ክርስቲያናዊ የህይወት ትምህርት ከመስጠት ይልቅ በመርጌታ ስም የቤተክርስቲያንን ስም በሚያጠፍ መተተኞች ማስታወቂያ መጥለቅለቅ በእውነት ያሳዝናል ያማልም ። ማስታወቂያ ሰሪዎቹም አለማስተዋወቅ የሚበሉበትን ትሪ እንደመንጠቅ ነው የሆነባቸው ።
1.6K views✞£iŧsûm✞, edited  14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 13:36:10
"ጌታዬ ሆይ ስለ በደሌ፣ ስለ አበሳዬ ከአንተ እለምን ዘንድ ድፍረት የለኝም። በደሌ ከሰው ሁሉ በደል ይበልጣልና፤ ከሁሉ ፍጥረት ይልቅ እኔ በፊትህ በደልሁ። ከቁጥር ያለፈ ብዙ ጊዜ ስምህን ሰማሁ። ከአቅም በላይ ዝሙትን አበዛሁ። ከዘማውያኑ ጋር ሁሉንም አደረግሁ። ለአንተም ፈጽሞ ባለዕዳ ኾንሁ፤ ዲያብሎስ የኃጢአትና የክፋት ወታደር አደረገኝ። ከሽፍታ የሚበልጥ ሞትን አመጣብኝ፤ እኔ ነፍሰ ገዳይና ፍጹም ዘማዊ ነኝ።

እግዚአብሔር በፈጠረውም ከዘማዊቷ ዝሙትን ፈጸምሁ። ከነነዌ ሰዎች ይልቅም ፈጽሞ ኃጢአትን ሠራሁ፥ ያለ ንስሐም ተቀመጥሁ። በደሌም ከምናሴ ይልቅ ፈጽሞ በእኔ ላይ በዛ። ከከነናዊቷ ሴት ይልቅም ኃጢአቴ ፈጽሞ ከበደ። መሰነካከልን ሁሉ ተሰነካከልሁ፤ ቅዱስና ንጹሕ ስምህን አስቆጣሁ፤ መንፈስህንም አሳዘንሁ። ትእዛዝህንም አልተቀበልሁም። መዝገብህንም በማይገባይ አጠፋሁ። የሰጠኸኝን ልጅነትም በወንጀል አጠፋሁ።

መቅደስህንም አረከስሁ። ይህችም ሥጋዬ ናት፤ ነፍሴንም በርኲሰት አረከስኳት። ይህችውም የአንተ አርአያና አምሳል ናት። የሰጠኸኝን ሀብትም ከጠላቶችህ ጋር ኾኜ በተንሁት (አጠፋሁት)። ትእዛዝህንም አልጠበቅሁም። ያለበስኸኝን ልብስም አሳደፍሁት። በእኔ ላይ ያበራኸውን መብራትም በንዝኅላልነቴ ከውስጤ አጠፋሁት። ..."

ውዳሴ አምላክ ዘዓርብ (የአባ ሲኖዳ ጸሎት)
1.4K views✞£iŧsûm✞, edited  10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-04 08:46:32
"ለጽርሐ ጽዮን እሮጣለሁ" የሚል መንፈሳዊ መሪ ሀሳብን ያነገበ ሩጫ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው ።

መነሻው ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን መድረሻውን ጽርሐ ጽዮን ቅድስት ማሪያም አንድነት ገዳም በማድረግ ነው መንፈሳዊ ሩጫው እየተካሄደ የሚገኘው።

በመንፈሳዊ ሩጫው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ጨምሮ ታላላቅ የአብያተ ክርስቲያኗ አባቶች፣ የመንግሥት የሥራ ኅላፊዎች እና ሕዝበ ክርስቲያኑ በነቂስ እየተሳተፉበት ነው።
585 views✞£iŧsûm✞, edited  05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 22:37:18
እንኳን ደስ አላችሁ በዩቲዩብ የምናውቀው #ማኅቶት_ቲዩብ አሁን ደግሞ በቴሌግራም መጥታል ለመቀላቀል ከስር Join የሚለውን ንኩት።

https://t.me/+SLPMr-p0D_QzRyzI
287 views✞£iŧsûm✞, 19:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 16:07:57 "በሰዎች ዘንድ አጥብቀህ ብትፈልግና ብታንኳኳ ነዝናዛ ተደርገህ ትቆጠራለህ፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን እርሱን ባለማስቸገርህና ባለመነዝነዝህ እጅግ ታሳዝነዋለህ፡፡"

ቅዱስ ዮሐ.አፈ.፣ ማቴ. ድር.፳፫፥፭
104 views✞£iŧsûm✞, 13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-02 21:54:14
ዜና እረፍት

የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ባደረባቸው ሕመም ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸው እየተነገረ ነው።

ቅዱስነታቸው ሰኔ 6 ቀን 2013 ዓ.ም የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አምስተኛ ፓትርያርክ በመሆን በዓለ ሢመታቸውን በአስመራ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ካቴድራል መከናወኑ የሚታወስ ነው።

የቅዱስነታቸው በረከት ከሁላችን ጋር ትሁን!!!
1.0K views✞£iŧsûm✞, edited  18:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ