Get Mystery Box with random crypto!

'ቤተ ክርስቲያን የምትታገሰው እንደ ሀገር ስለምታስብ መሆኑን መልአክ ሕይወት ቆሞስ አባ ወልደኢየሱ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

"ቤተ ክርስቲያን የምትታገሰው እንደ ሀገር ስለምታስብ መሆኑን መልአክ ሕይወት ቆሞስ አባ ወልደኢየሱስ ሰይፉ ገለጹ"።
*********

ሕዳር ፳፮ ቀን ፳፻ ወ፲፭ ዓ.ም
""""""""""""""""""""""""""""
አዲስ አበባ-ኢትዮጵያ
******
ይህ የተገለጸው መልአከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ሰይፉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቋሚና ጊዜያዊ ፕሮጀክት መምሪያ ኃላፊ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ለሚዲያዎች በሰጡት መግለጫ ነው።

መልአከ ሕይወት በመግለጫቸው ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለይቶ ማየት እስከማይቻል ድረስ ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ እድገት ያበረከተችው አበርክቶ እጅግ ትልቅ እንደነበር አስታውሰዋል።

በሀገራዊና በልማት ጉዳይ ላይም ከሌሎች የሀይማኖት ተቋማት ጋርም በመሆን እየሠራች እንደምትገኝ አስታውሰዋል።

በአሁኑ ጊዜ የሚታየውና የሚነገረው ክብረ ነክ ነገር ለቤተ ክርስቲያን አይገባትም ያሉት መልአከ ሕይወት አባ ገብረ ኢየሱስ ሰይፉ በሃይማኖት ሽፋን የሚደረገው ሕገወጥ ድርጊት እጅግ የሚያሳዝን ነው ሲሉም አክለው ገልጸዋል።

ተአምረ ማርያም ቤተ ክርስቲያናዊ መሠረት ያለው መጽሐፍ መሆኑን የገለጹት መልአከ ሕይወት ሰሞኑን በመጽሐፉ ዙሪያ የተሰጠው ትችት ተገቢ ያልሆነና በሕግ የሚያስጠይቅ ተግባር ነው ብለዋል።

እየጠፋን ዝም ብለን የምንታገስ አይሆንም። ቤተ ክርስቲያን ትዕግሥት የምታበዛው መልስ መስጠት አቅቷት ሳይሆን እንደ ሀገር ስለምታስብ ነው። በመሆኑም እነዚህ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ በጥብቅ እናሳስባለን ብለዋል።

በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አንዱ የአንዱን ሃይማኖት እያከበረ እንዲኖር በሕግ የተቀመጠ ቢሆንም ቤተክርስቲያን የማንንም ድንበር አላፋ ባልሄደችበት ሁኔታ የቤተክርስቲያንን ድንበር አለፈው ለሚመጡ አካላት ተቋሙ በአለው አሰራርና የሥነ ምግባር ደንብ መሰረት ሊጠይቃቸው ይገባል ብለዋል።

በማያያዝም ቤተ ክርስቲያን ሚዛናዊ ሥራ እየሠራችና ሌሎቹን እያከበረች ባለችበት ሁኔታ በሀይማኖት ካባ ተደብቀው ሰላም ሲሆን የማይወዱ አካላት ቤተ ክርስቲያንን የማይገባት ስም እየሠጡ ይገኛሉ። ይህ አግባብም የሚያዛልቅም አይደለም ብለዋል።

እኛ ሌላውን አልነካንም ሌላው ለምን ይነካናል? ቤተ ክርስቲያን የማንም ሥጋት ሆና አታውቅም ሌሎች ሲነሱባት ግን መንግሥት ዝም ማለት የለበትም ሲሉ ሕግና ሥራአት እንዲከበር አሳስበው የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤም በአስቸኳይ ተሰብስቦ ጉዳዩን እንደሚያወግዝና እልባት እንደሚሰጥ እንጠብቃለን ሲሉ መግለጫቸውን አጠቃለዋል ።