Get Mystery Box with random crypto!

ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የሰርጥ አድራሻ: @zdfitsumkebe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.71K
የሰርጥ መግለጫ

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-12-14 17:36:13 ለስኬታማና ደስታ የተሞላበት የትዳር ህይወት ውስጥ ሊኖሩ የሚገቡ ወሳኝ አመለካከቶች

ተጻፈ፣ በስነ-ልቦና ባለሙያ

          . . . Bini Girmachew

1. ትዳር ፈጣሪን የሚያስደስቱበት ቀና እሳቤ መሆኑን አውቆ መግባት ፦

ሁለቱም ተጣማጆች ትዳር የተቀደሰና ንፁህ ተቋም እንደሆነ ተገንዝበው መግባትና ክብር መስጠትም አለባቸው እነሱ ካከበሩ በትዳራቸው ፈጣሪ እንደሚከበር መረዳትም ያስፈልጋል።

2. ባል ወይም ሚስት በፈጣሪ ወንድም (እህት) እንደሆኑ ልብ ማለት

ለአጠቃላይ እህትና ወንድም የሚደረግ አክብሮት ለትዳር ተጓዳኝ መደረግ ይኖርበታል...ሙሉውን ለማንበብ

                
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun

በYoutube ለመከታተል
              
https://www.youtube.com/channel/UCawJZOERphyparnxlMZwa6w
62 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-14 16:25:05 +++‹‹አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም›› ሉቃ 6፡37+++

ብዙ ጊዜ ምንም ዓይነት የጥፋተኝነት ስሜት ሳይሰማን ከምንሠራቸው ኃጢአቶች መካከል አንዱ ‹‹በሌሎች ላይ መፍረድ›› ነው፡፡ ደግሞ ነገሩን ከባድ የሚያደርገው የምንፈርድባቸው የወንድሞቻችንን ውድቀት በዓይናችን ማየታችን በጆሯችን መስማታችን ነው፡፡ ያዩትን አይተው፣ የሰሙትን ሰምተው ሲጨርሱ ወዲያው አለመፍረድ እንደ ተራራ የረጋ ትልቅ ሰብዕናን ይፈልጋል፡፡ ትሑት የሆነ ሰው የሌሎች ሰዎችን ድክመት ለማየት የሚገለጥ ዓይን የለውም፡፡ ዘወትር ራሱን እየመረመረ ድክመቶቹን በመቁጠር ላይ ይጠመዳል፡፡ ዓይኖቹም እንደ አሸዋ በበዛው በገዛ ኃጢአቱ ላይ ብቻ ናቸው፡፡ ደግሞ ወደ ሌላው ከተመለከቱ ሊያመሰግኑ እና ሊራሩ እንጂ ሊንቁና ሊፈርዱ አይደለም፡፡

በወንድሞች ላይ መፍረድ የእግዚአብሔር የሆነውን የጌትነቱን ንብረት እንደ መስረቅ፣ በክርስቶስም የፍርድ ዙፋን ላይ ራስን እንደማስቀመጥ ይቆጠራል፡፡ ታዲያ ከዚህ በላይ ድፍረት፣ ከዚህ የሚበልጥ ኃጢአትስ ከየት ይገኛል? አበው ‹ሌሎች ላይ መፍረድ› የትዕቢት ታማኝ ልጅ ሲሆን፣ መጋቢና አሳዳጊውም እርሱው (ትዕቢት) እንደ ሆነ ይናገራሉ፡፡ ራስን መውደድ እና በራስ አስተዋይነት ላይ መደገፍ ሌላው ላይ ጨክኖ ከመፍረድ እንደሚያደርስም ያስተምራሉ፡፡ በርግጥ በሌሎች መፍረድ የሚወድ ሰው ‹‹ክፉ ሲደረግ ተመልክቼ ማለፍ አልችልም!›› እያለ ለከሳሽነቱ ምክንያት ይደረድር ይሆናል፡፡ ይሁን እንጂ በሰዎች ላይ የመፍረድ ኃጢአት ምንጩ የሌሎች ደካማ ምግባር ሳይሆን የተመልካቹ (የፈራጁ) የልብ ክፋት መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡ የልብ ቅንነቱ ቢኖርማ በተሳሳተ ወንድሙ ፊት ቆሞ ወይ የራሱን ድክመት እያሰበ የሚያለቅስ፣ አልያም ደግሞ ለወደቀው ወንድሙ እየራራ የሚመክርና የሚጸልይ ይሆን ነበር፡፡

በሌሎች መፍረድና አቃቂር ማውጣት የለመደ ሰው ዓለሙ ሁሉ በእርሱ ፊት ሞኝ ሆኖ ይታየዋል፡፡ ሰው ሁሉ አስተዋይነት በጠፋበት ሰፊ ጎዳና ሲርመሰመስ፣ እርሱ ግን ከፍ ካለው የብስለት ሰገነት ላይ እንደ ቆመ ስለሚሰማው፣ ቁልቁል እያየ የሚሰጠው እርማትና የትዝብት እይታው አይጣል ነው፡፡ ፈራጅ ‹እኔ ተሳስቼ ይሆን?› የሚል ትሑት ሕሊና የለውም፡፡ ልክ በአገጩ ላይ ያለው ሪዝ (ጽሕም) ከመቆሸሹ የተነሣ በፈጠረው መጥፎ ጠረን በሄደበት ሁሉ አፍንጫው ሲረበሽ (መጥፎ ጠረን ሲሸተው) ‹ዓለሙ ሁሉ ሸቷል› እንዳለው ሰው፣ በራሱ ድክመት ምክንያት በተፈጠረበት የእይታ መንሸዋረር ሁሉን ሲተች በሁሉ ሲፈርድ ይኖራል፡፡ የሥነ ልቡና ሳይንሱም እንደሚናገረው አንዳንድ ጊዜ በራስ ውስጥ ያለ የዕውቀት እና የልምድ ክምችት እያነሰ ሲመጣ፣ በሰው ፊት ዝቅ ብሎ ላለመታየት ሲባል በሁሉን ፈራጅና ነቃፊነት መጋረጃ ራሳችንን ልንከልል እንሞክራለን። ይህም አንዱ የሰብዕና መቃወስ (personality disorder) ምልክት ነው።

ቅዱስ አንስታስዮስ ዘሲና ‹‹ማንም ላይ አለመፍረድ››ን በተመለከተ በአንድ ወቅት በገዳሙ ይኖር ስለ ነበረ ደግ መነኩሴ ታሪክ የተናገረውን አንሥተን ጽሑፋችንን እንቋጭ፡፡ ይህም መነኩሴ እርሱ በሚኖርበት ገዳም እንዳሉት ሌሎች መነኮሳት ከፍ ያለ ትጋት አልነበረውም፡፡ ታዲያ የሚሞትበት ቀን ደርሶ በአልጋው ላይ ሳለ ከሞት ፍርሐት ይልቅ በፊቱ ላይ የሚነበበው ታላቅ ደስታ ነበር፡፡ በሁኔታው የተገረሙት በዙሪያው የተቀመጡ መነኮሳትም ‹‹ወንድማችን ሆይ! ሕይወትህን በስንፍና (ትጋት ሳታበዛ) እንዳሳለፍክ እናውቃለን፡፡ አንተስ ይህን ስታውቅ በዚህ በመጨረሻው ሰዓት ስለ ምን ደስተኛ ሆንክ? ምሥጢሩን ልናውቅ አልተቻለንም›› ሲሉ ጠየቁት፡፡ ያም ደግ መነኩሴ ‹‹አዎን! ክቡራን አባቶቼ! ሕይወቴን ሁሉ በስንፍና እና በእንቅልፍ ነው ያሳለፍኩት፡፡ ነገር ግን አሁን በዚህች ሰዓት መላእክት መነኩሴ ከሆንኩበት ጊዜ ጀምሮ የሠራኋቸው ሥራዎች ሁሉ የተመዘገቡበትን አንድ መጽሐፍ አምጥተውልኛል፡፡ ይህንንም መጽሐፍ ስመለከት በማንም ላይ እንዳልፈረድኩ፣ ማንንም እንዳልጠላኹ፣ በማንም እንዳልተቆጣኹ ተረዳኹ፡፡ ስለዚህም ‹አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም› የሚለው የጌታዬ ቃል በእኔ ላይ እንደሚፈጸም ተስፋ አደረኩ፡፡ በዚህም ቅጽበት ይህችን ትንሽ ሕግ ስለፈጸምኩ ሌላው ሁሉ የዕዳ ጽሕፈቶቼ ተቀደዱልኝ›› አላቸው፡፡ ይህንንም ከተናገረ በኋላ ነፍሱ ከሥጋው ተለየች፡፡ መነኮሳቱም በምክሩ ተምረው የእግዚአብሔርን ሥራ እያደነቁ በምሥጋና ቀበሩት፡፡

በእውነትም ‹‹አትፍረዱ አይፈረድባችሁም›› የሚለው የመድኃኒታችን ቃል በዚህ ታሪክ ውስጥ ትክክለኛ ትርጉሙን አግኝቷል፡፡ በወንድሞች ድክመት አለመሳለቅና በውድቀታቸው አለመፍረድ ወደ ዘላለማዊው እሳት ከመጣል ያድናል፡፡

+++እግዚአብሔር በሰው ያልፈረዱ ቅዱሳን ካሉበት ገነት በቸርነቱ ያግባን!+++

ዲያቆን አቤል ካሳሁን


https://t.me/akanim1wasen2
469 viewsወሰንየለው ባህሩ, 13:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-14 08:46:17
እነሆ አዲስ ቻናል ይዘንሎት መጣን
በማርያም ይህን ቻናል ሳይቀላቀሉ እንዳያልፉ ይደሰቱበታል መርጠን ለናንተ አቀረብንሎ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲   █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
142 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-14 07:35:28 አዲስ መንፈሳዊ ትረካ ሕማማት ክፍል 1 "የመጀመሪያው ቁስል"

ስለ ያስቆሮቱ ይሁዳ መጻፍ የሚማርክ ርዕሰ ጉዳይ አለመሆኑን የምናውቀው አራቱ ወንጌላውያን አስገዳጅ ከሆኑባቸው ጥቂት ቦታዎች በስተቀር ስለ ይሁዳ ብዙ ባለመጻፋቸው ነው
እኛም ስለ ይሁዳ ሳናነሳ ጌታችን ስለተቀበለው ሕማምና መከራ ብናነሳ ምነኛ በወደድን
ነገር ይሁዳ ራሱ ጌታችን ስለእኛ ድኅነት ከታገሳቸው መከራዎች አንዱ ነው።
ምክንያቱም የጌታችን ህማምና ስቃይ የሚጀምረው ከ12ቱ አንዱ አድርጎ የቆጠረው ይሁዳ አሳልፎ ሲሰጠው ነው።
በዕለተ አርብ በጠላቶቹ እጅ ከተሰቃየው ስቃይ በወዳጁ ይሁዳ ምክንያት የተሰቃየው የይሁዳ ስቃይ የከፋ ነበረ
"የታመንኩበት የሰላሜ ሰው ያልኩት እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሳ" ተብሎ እንደተነገረው ከሐዋርያቱ ጋር አንድ አድርጎ የሾመው የከረጢጡን ገንዘብ እንዲይዝ የታመነበት ደቀመዝሙሩ ሲከዳው ማየቱ የጌታችን መጀመሪያ ስቃዩ ነበር
ጌታችን ስለይሁዳ በመንፈሱ ታወከ ተብሎ ተጽፏል ከዚህ በፊት ጌታችን በመንፈሱ የታወከው...ሙሉ ትረካውን በድምፅ ለማግኘት












Subscribe like share ማድረግ እንዳትረሱ መንፈሳዊ ቻናሎችን እንደግፍ
174 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 04:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-13 22:35:32 *~የትዕቢት ታማኝ ልጅ ማን ነው ?~*

በወንድሞች ላይ መፍረድ የእግዚአብሔር የሆነውን የጌትነቱን ንብረት እንደ መስረቅ፣ በክርስቶስም የፍርድ ዙፋን ላይ ራስን እንደማስቀመጥ ይቆጠራል፡፡ ታዲያ ከዚህ በላይ ድፍረት፣ ከዚህ የሚበልጥ ኃጢአትስ ከየት ይገኛል? አበው ‹ሌሎች ላይ መፍረድ› የትዕቢት ታማኝ ልጅ ሲሆን፣ መጋቢና አሳዳጊውም እርሱው (ትዕቢት) እንደ ሆነ ይናገራሉ፡፡

***
የሥነ ልቡና ሳይንሱም እንደሚናገረው አንዳንድ ጊዜ በራስ ውስጥ ያለ የዕውቀት እና የልምድ ክምችት እያነሰ ሲመጣ፣ በሰው ፊት ዝቅ ብሎ ላለመታየት ሲባል በሁሉን ፈራጅና ነቃፊነት መጋረጃ ራሳችንን ልንከልል እንሞክራለን። ይህም አንዱ የሰብዕና መቃወስ (personality disorder) ምልክት ነው።

+++እግዚአብሔር በሰው ያልፈረዱ ቅዱሳን ካሉበት ገነት በቸርነቱ ያግባን!+++

+++‹‹አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም›› ሉቃ 6፡37+++ በሚል እስተማሪ ፁሑፍ የተወሰደ ።

~ዲያቆን አቤል ካሳሁን~
722 views✞£iŧsûm✞, 19:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-13 13:39:31 የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ አሜን።

በዝህ ቻናል የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙሮች የሚያገኙበት ቻናል ነው።

ይ ላ ሉ
የተለያዩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር

የቴዎድሮስ ዮሴፍ መዝሙር
የዳግማዊ ደርቤ መዝሙር
የቀዳሜጸጋ መዝሙር
የዘማሪት ለምለም ከበደ መዝሙር
የኪነጥበብ መዝሙር
የይልማ ኃይሉ መዝሙር
የዘማሪ አቤል መክብብ መዝሙር
የዘማሪት ትንቢት ቦጋለ

እነዚህንና የተለያዩ መዝሙር ያገኙበታል ይቀላቀሉን


█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN▒▓█
█▓▒░►OPEN◄░► OPEN▒▓█
█▓▒░ ►OPEN◄░►OPEN▒▓█
█▓▒░►OPEN◄░►OPEN ▒▓█
193 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 10:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-13 13:28:53




  Click Here 




147 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 22:51:57 #ድህነቷን እናፍቀዋለሁ

ኢትዮጵያ ድሀ የነበረች ጊዜ - ያኔ ያለው ለሌለው ያካፍል ነበር፤የሌለው ጎዳና ወጥቶ፣ ደብር ተጠግቶ ለምኖ በልቶ ያድር ነበር፡፡የድሀ ልጅ በባዶ እግሩ ትምህርት ቤት እየተመላለሰ ፊደል ይቆጥር ነበር፡፡ በኩራዝ ጭለማ ይረታ ነበር፡፡. . . ያኔ ነብስ ካወቅን ጀምሮ የሀገራችን ከድህነት መውጣት ያሳስበን ነበር፡፡ወጣት ሆነን ሀገራችንን ከድህነት ለማውጣት እድገት በህብረት ዘመትን፣መሰረተ ትምህርት ዘመትን፤ሰላም እንድትሆን በብሄራዊ ውትድርና አገልግሎት ዘመትን፡፡

በወጣትነቴ ጠመንጃ ይዤ ዘብ የቆምኩላት ሀገር ዛሬ በጎልማሳነቴም ሰላም አለማግኘቷ ልቤ ድረስ ይጠዘጥዘኛል፡፡ድህነቷንም እናፍቀዋለሁ፤ድሃ ለምኖ የሚበላበትን፣ አባወራ ጥጥ ለቀማ ቆላ የሚወርድበትን፣ ‹‹ግፋ ቢል አዶላ!›› ብሎ ወርቅ ቁፋሮ በቀን ሰራተኝነት የሚሰደድበትን . . . ድህነቷን እናፍቀዋለሁ፤ሊያሳስበኝ ግን ልቦናዬ ጊዜ የለውም፡፡

ህይወት ረከሰ፤ሞት ነገሰ፡፡ከእንቅልፌ የሚቀሰቅሰኝ የወፎች ዜማ ሳይሆን የሞት ዜና ነው፡፡በድህነት ያለፉት እናትና አባቴ ሰው ተሰቅሎ ሲሞት አይተው ለሳምንታት እንቅልፍ አይተኙም ነበር፡፡የእኔ ዘመን አገዳደል ያኔ አልነበሩም፤የሀገሬ ልጆች ከዚያ ወዲህ ተጠበው የደረሱባቸው የጭካኔ ፍሬዎች ናቸው፡፡ከእንቅልፌ ስነቃ ስለምሰማው ሞት ሳስብ ውዬ ስለእሱው ሳስብ ያሸልበኛል፡፡

በየት በኩል ስለሌላ ነገር ማሰብ ይቻላል! የሀገሬ መልክ ሆኖ የሚያሳስበኝ ሞት እንጂ ድህነት አይደለም፡፡ስለሞት ባሰብኩ ቁጥርም በልጅነቴ የኖርኩት ሰላማዊ ድህነቷ ይናፍቀኛል፡፡ሞት በሚዘመርባት ሀገሬ ውስጥ እየኖሩ፣ከድህነት ሊፈውሷት የሚጥሩ ዜጎቿን ልረዳቸው አቅቶኛል፡፡እኔ ግን እላለሁ! ኢትዮጵያ ከድህነቷ የምትወጣው ማለቂያ በሌለው የዜጎች ሞት ከሆነ፣ለዘለአለም ድሀ ሆና ትኑርልን፤እንኑርባት፡፡

(ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ)
1.5K views✞£iŧsûm✞, 19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 17:32:49 የግእዝን ቋንቋ በአንድ ወር ውስጥ አቀላጥፎ ማውራት ይፈልገሉ

አዎን እፈልጋለሁ የምትሉ
አሪፍ የቴሌግራም ቻናል ልጋብዛችሁ
ያለ ምንም ጥርጥር ትወዱታለችሁ %

JOIN አድርጉና ግእዝን በአማረኛ ይማሩ @LESANGEEZ128
@LESANGEEZ128
@LESANGEEZ128
@LESANGEEZ128
@LESANGEEZ128

የግእዝ ትምህርት በYOUTUBE
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg


𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
@lesangeez128
@Orthodox_Addis_Mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
317 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 17:27:37
1, እመጓ
2, ዝጎራ
3, መርበብት
4, ዴርቶጋዳ
5, ዮራቶራድ
6, ዣንቶዣራ
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ
26, መጽሐፈ አክሲማሮስ
27, 14ቱ ፍሬ ቅዳሴያት ከነ አንድምታው
28, መልክዓ መለኮት
29, መጽሐፈ አሚን ወ ሥርዓት
30, ሰባቱ ምስጢራተ ቤተከርስቲያን
31, ሐይማኖተ አበው
32, ራዕየ ማርያም
34, የመናኝ ጉዞ
35, መልክዓ እግዚአብሔር
36, ታብተ ጽዮንን ፍለጋ
37, ፍካሬ ኢየሱስ ወትንቢተ ሳቤላ
38, መጽሐፍ ቅዱስ እና የህክምና ሳይንስ
39, መርበብተ ሰሎሞን
40, የ ቶ መስቀል ትርጉም
41, መጽሐፈ ፈውስ
42, ባሕረ ሐሳብ
43, ሞታ የተነሳችው ኦርቶዶክሳዊት ካትሪን
44, ቅዱስ ማርቆስ ኢትዮጵያዊ
45, ትንሳኤ ዘኢትዮጵያ
46, የ 666 ሳይንሳዊ ምስጢር
47, ቅኔ
48, ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ
49, ህይወተ ቅዱሳን
50, ነገረ ቅዱሳን

የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ

     __________
                       ይቀላቀሉን                      
     __________
214 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ