Get Mystery Box with random crypto!

*~የትዕቢት ታማኝ ልጅ ማን ነው ?~* በወንድሞች ላይ መፍረድ የእግዚአብሔር የሆነውን የጌትነቱ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

*~የትዕቢት ታማኝ ልጅ ማን ነው ?~*

በወንድሞች ላይ መፍረድ የእግዚአብሔር የሆነውን የጌትነቱን ንብረት እንደ መስረቅ፣ በክርስቶስም የፍርድ ዙፋን ላይ ራስን እንደማስቀመጥ ይቆጠራል፡፡ ታዲያ ከዚህ በላይ ድፍረት፣ ከዚህ የሚበልጥ ኃጢአትስ ከየት ይገኛል? አበው ‹ሌሎች ላይ መፍረድ› የትዕቢት ታማኝ ልጅ ሲሆን፣ መጋቢና አሳዳጊውም እርሱው (ትዕቢት) እንደ ሆነ ይናገራሉ፡፡

***
የሥነ ልቡና ሳይንሱም እንደሚናገረው አንዳንድ ጊዜ በራስ ውስጥ ያለ የዕውቀት እና የልምድ ክምችት እያነሰ ሲመጣ፣ በሰው ፊት ዝቅ ብሎ ላለመታየት ሲባል በሁሉን ፈራጅና ነቃፊነት መጋረጃ ራሳችንን ልንከልል እንሞክራለን። ይህም አንዱ የሰብዕና መቃወስ (personality disorder) ምልክት ነው።

+++እግዚአብሔር በሰው ያልፈረዱ ቅዱሳን ካሉበት ገነት በቸርነቱ ያግባን!+++

+++‹‹አትፍረዱ አይፈረድባችሁምም›› ሉቃ 6፡37+++ በሚል እስተማሪ ፁሑፍ የተወሰደ ።

~ዲያቆን አቤል ካሳሁን~