Get Mystery Box with random crypto!

ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የሰርጥ አድራሻ: @zdfitsumkebe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.71K
የሰርጥ መግለጫ

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-12-12 10:23:24 በርጠሜዎስ ነኝ

Bini Girmachew

ጌታዬ ሆይ ያለ ማየትን ዘመን በማየት ለውጬ ፥ የሚያዩኝን ለማየት በቅቼ ፥ ብርሃንን ከብርሃናት አምላክ ተመጽውቼ የምኖር በርጠሜዎስ እኔ ነኝ ። እኔ ነኝ ለማለት ድሮ የማልደፍር፥ ክፉውን ታሪኬን ወደ ኋላ የጣልኩኝ ፥ የማያዩ አይመሩኝም ፥ ዓይን የሌለው በትር ገደሉን እንጂ መድረሻውን አይጠቁመኝም ብዬ የጣልኩኝ ፥ ዓይን አውሱኝ እያልኩ ስጣራ የኖርኩኝ ፥ መቶዎችን ለምኜ አንዱን የማራራ እኔ ነኝ በርጠሜዎስ ከመቃብር በላይ የዋልኩኝ ።

የድሮ ዕውር የዛሬ ተመልካች ፥ የድሮ ተመሪ የዛሬ መንገድ አመልካች ፥ የድሮ ተመጽዋች የዛሬ ሠራተኛ በርጠሜዎስ እኔ ነኝ ሁለተኛ የተሠራሁኝ ። ጌታዬን አግኝቼ ከሰው መከጀልን ያቆምሁ...ሙሉውን ለማንበብ

                
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun

በYoutube ለመከታተል
              
https://www.youtube.com/channel/UCawJZOERphyparnxlMZwa6w
650 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 07:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 10:22:20 አዲስ መንፈሳዊ ትረካ የመጨረሻው ክፍል "የጠፋው ልጅ" ጸሐፊ @binigirmachew ተራኪ ሜሮን እንዳሻው

ሁላችንም ልናዳምጠው የሚገባ ትረካ ነው የሁሉም ሰው ታሪክ ስለሆነ

ክፍል አራት

ራሳችን መመልከታችን ብቻውን በቂ አይደለም።ይህ የመጀመሪያ ደረጃ ነው።ሁለተኛው እርምጃ መሄድ ነው።ምን ይህል ጊዜ ተቀምጠን አሰብን?ይህንን ነገር እጀምራለሁ ለማለት ምን ያህል ጊዜ ቀጠሮ ያዝን።አዲስ የአመጋገብ ዕቅድ፣የገንዘብ ዕቅድ፣አዲስ መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ዕቅድ ሁልጊዜም የምለው ነገ እጀመራለሁ ነው።ነገ የሚመቸን ቀን ነው ምክንያቱም ፈጥኖ እንደሚመጣ አናስበውምና።ነገን ነገ ይወልደዋል።ቀጠሮአችን በዚህ መልኩ ማረፊያ ማብቂያ የሌለው ቀጠሮ ይሆናል።ዛሬ ተስሥቼ ወደ አባቴ ቤት እሄዳሁ ልንል ይገባናል።


የጠፋው ልጅ የተማረው ይሄንን ነው።ሁላችንም ተመሳሳይ በሆነ መንገድ መማር አይጠበቅብንም።ከዚህም በበለጠ ፈጥነን ወደ አባታችን ቤት የምንመለስበት መንገድ መማር ይጠበቅብናል።እሣት እንደሚያቃጥል ለማወቅ የግድ እጃችንን ከእሳት ላይ ማስቀመጥ አይጠበቅብንም።የጠፋው ልጅ ትህትናን ከመከራው ተመሯል።መመለስ እንዳለበት አውቋል።ንስሐ ትልቁን ድርሻ ይይዛል።ወደ አባታችን የምንመለሰው እንዴት ነው?...ሙሉ ትረካውን በድምፅ ለማግኘት












Subscribe like share ማድረግ እንዳትረሱ መንፈሳዊ ቻናሎችን እንደግፍ
624 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 07:27:54 የግእዝን ቋንቋ በአንድ ወር ውስጥ አቀላጥፎ ማውራት ይፈልገሉ

አዎን እፈልጋለሁ የምትሉ
አሪፍ የቴሌግራም ቻናል ልጋብዛችሁ
ያለ ምንም ጥርጥር ትወዱታለችሁ %

JOIN አድርጉና ግእዝን በአማረኛ ይማሩ @LESANGEEZ128
@LESANGEEZ128
@LESANGEEZ128
@LESANGEEZ128
@LESANGEEZ128

የግእዝ ትምህርት በYOUTUBE
https://youtube.com/channel/UCbuXpsXU7hDaFWELjzHlxdg


𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
@lesangeez128
@Orthodox_Addis_Mezmur
@orthodox_spiritual_poems
@Eotc_Books_By_Pdf
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆
352 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 04:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-12 07:25:06 የዶሮ ላባዎች ሲበተኑ

አንድ ወጣት ወደ አንድ ታላቅ አባት ዘንድ ይሄድና አባት እውነት ባልሆነ አሉባልታ የሰውን ስም በማጥፋት የጎዳሁ መሆኔ አሁን ታወቀኝ ።

እና ስለ ሀጢያቴ ምን ላድርግ ብሎ ጠየቃቸው!
እሳቸውም እንዲሁ ሲሉ መለሱለት...ሙሉውን ለማንበብ

                
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun

በYoutube ለመከታተል
              
https://www.youtube.com/channel/UCawJZOERphyparnxlMZwa6w
173 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 20:52:43 ~በዓታ_ለእግዝእትነ_ማርያም~

#ታኅሣሥ_3


ታኅሣሥ ሦስት በዚህች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ነው ። እርሷ ለእግዚአብሔር የስእለት ልጅ ነበረችና።

እናቷ ቅድስት ሐና ልጅ የሌላት ስለሆነች በቤተ እግዚአብሔር ውስጥ ከሴቶች ተለይታ ርቃ ትኖር ነበር ሽማግሌ ከሆነ ከኢያቄም ከባሏ ጋርም እጅግ የምታዝን ሆነች ። እግዚአብሔርም ኀዘናቸውን ሰማ ቅድስት ሐናም እንዲህ ብላ ለእግዚአብሔር ተሳለች የሰጠህኝን ፍሬ ለእግዚአብሔር አገልጋይ አደርገዋለሁ ።

ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምንም በወለደቻት ጊዜ ሦስት ዓመት በቤቷ ውስጥ አሳደገቻት ከዚህም በኋላ ከደናግል ጋር ትኖር ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ ወሰደቻት በቤተ መቅደስም ምግቧን ከመላእክት እጅ እየተቀበለች ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረች ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ዓለም መጥቶ ከእርሷ ሥጋን እስከ ነሣ ድረስ።

ከሴቶች ሁሉ የተመረጠች ይቺ ናት በቤተ መቅደስም በመኖር ዐሥራ ሁለት ዓመት ሲፈጸምላት እርሷ ለእግዚአብሔር የተሰጠች የስዕለት ልጅ ናትና ለሚጠብቃት ይሰጧት ዘንድ ካህናት እርስበርሳቸው ተማከሩ በሴቶች ላይ የሚደርስ በርሷ ላይም ይደርስባታል ብለው ስለፈሩ በቤተ መቅደስ ውስጥ ይተዋት ዘንድ ለእርሱ ትክክል መስሎ አልታያቸውም ስለዚህም ሊጠብቃት ለሚገባው በእርሷ ላይ እጮኛ ሊአኖሩ ወደዱ።

ከዚህም አስቀድሞ ሊቀ ካህናት ዘካርያስ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ልጄ ማርያም ሆይ አንቺ እንዳደግሽና ለአካለ መጠን እንደደረስሽ ዕወቂ ልትታጪ ትወጃለሽን እግዚአብሔርን የሚፈራ መልካም የሆነ የተባረከ ጐልማሳ እንፈልግልሽን ወይም በሕይወትሽ ዘመን ሁሉ በቤተ መቅደስ ተቀምጠሽ እግዚአብሔርን ልታገለግዪው የምትሺ ከሆነ በሴቶች ላይ የሚደርሰው በሚደርስብሽ ወራት ወደ ቤተ መቅደስ ደጅ ከመግባት ትጠበቂ ዘንድ በኦሪቱ የተጸፈውን የርግማን ሥርዓት በአንቺ ላይ እንሠራለን አላት ።

ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያምም እነሆ እኔ የእግዚአብሔር አገልጋዩ በፊታችሁ ነኝ አባትና እናት የሉኝም ስሙ ቡሩክ ምስጉን ከሆነ ከእግዚአብሔር በታች በእናትና አባት ፈንታ እናንት ናችሁና የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እንደምታውቁ አድርጉ ብላ መለሰች።

ካህናቱና ማኅበሩም ሁሉ ዘካርያስን ወደ ቤተ መቅደስ ገብተህ ስለዚች ብላቴና ማርያም ወደ እግዚአብሔር ጸልይ አሉት ዘካርያስም ገብቶ ሲጸልይ በዚያን ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ተገለጠለትና እንዲህ አለው። ዘካርያስ ሆይ ወጥተህ ከዳዊት ወገን ሚስቶቻቸው የሞቱባቸውን ሁሉ ወንዶች ሰብስብ የየአንዳንዱንም በትር ከስሙ ጋር ውሰድ ወደ ቤተ መቅደስም በምሽት አግብተህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይበት በነጋ ጊዜም በትሮቻቸውን አውጣ እግዚአብሔርም በበትሩ ላይ ምልክት ለገለጠልህ ለዚያ ሰው ማርያምን ተቀብሎ ሊጠብቃት ይገባዋል።

ካህኑ ዘካርያስም ወጥቶ አንድነት ለተሰበሰቡት ሕዝብ የእግዚአብሔር መልአክ የነገረውን ነገራቸው በዚያንም ጊዜ ከዳዊት ወገን ጐልማሳም ቢሆን ሽማግሌም ቢሆን ሚስቱ የሞተችበት ሁሉ በኢየሩሳሌም ወደአለ ቤተ መቅደስ ይሒድ እያሉ ዓዋጅን ዙረው የሚናገሩ በእስራኤል አገር ሁሉ ላከ ።

ከዳዊት ወገን የሆነ ጠራቢው ዮሴፍም በሰማ ጊዜ በትሩን ይዞ ከናዝሬት ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ ካህኑ ዘካርያስም የሁሉንም በትሮች ተቀብሎ ስማቸውን በላያቸው ጻፈ ቁጥራቸውም አንድ ሽህ ዘጠኝ መቶ ሰማንያ አምስት ሆነ ዘካርያስም በትሮችን ወደ ቤተ መቅደስ አስገብቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እንዲሁም ሰዎች ሁሉ ከቤተ መቅደስ ውጭ ቁመው ይጸልዩ ነበር ዘካርያስም ጸሎቱን በፈፀመ ጊዜ ለየአንዳንዱ በትራቸውን አውጥቶ ሰጠ ጠራቢው ዮሴፍም በትሩን ሊቀበል በቀረበ ጊዜ ከእርሷ ነጭ ርግብ የመሰለች ተገለጠች እየበረረችም ሒዳ በጠራቢው ዮሴፍ ራስ ላይ ተቀመጠች ካህናቱና ሕዝቡ ሁሉ አይተው እጅግ አደነቁ ምስጉን የሆነ እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ።

ዘካርያስም ዮሴፍን ዮሴፍ ሆይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ እንደ ተናገረ ድንግል ማርያምን ወደ ቤትህ ወስደህ ጠብቃት አለው ዮሴፍም ቅድስት ድንግል ማርያምን ከካህናት እጅ ተቀበላት በእርሱም ዘንድ ኖረች ። ከዚህም በኋላ የመላእክት አለቃ ገብርኤል ስለ እግዚአብሔር ልጅ ከእርሷ ሰው ሁኖ ስለመወለዱ በዮሴፍ ቤት አበሠራት።


እንኳን አደረሳቹሁ አቻናሌ ቤተሰቦች
1.1K views✞£iŧsûm✞, edited  17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 19:15:55 +++ የተሰጠ እንባ +++

የሰው ልጅ ደካማ ነው። በውስጡ የሚፈራረቁበትን ስሜቶች ተሸክሞ ለማቆየት ይቸገራል። በጣም ሲደሰት ወይም በጣም ሲያዝን እነዚህን ስሜቶች የሚያስተነፍስበት ሳቅ ወይም ልቅሶ ይፈልጋል። ይህ ካልሆነ ግን ሰውነት ይጨነቃል። አዲስ የወይን ጠጅ እንደ ገባበት አሮጌ አቁማዳ እቀደድ እቀደድ ይላል። ከባዱን የስሜት ሰደድ እሳት የሚያበርድበት ትኩስ እንባ ከዓይን ካላዘነመ ዕረፍት የሚባል ነገር አያገኝም። ዓይን አላነባ ሲል የውስጥ ሕዋሳት የሕመም እንባ ማንባት ይጀምራሉ።

የሕክምና ሰዎች እንደሚናገሩት ሦስት ዓይነት እንባዎች አሉ። የመጀመሪያው ዓይን ውስጥ ባዕድ (ቆሻሻ) ነገር ሲገባ የምናነባው ቅጽበታዊ እንባ (Reflex tear) ሲሆን፣ ሁለተኛው ዓይናችን እንዳይደርቅና ራሱን ከinfection ለመከላከል ሲል የሚያመነጨው የማይቋረጥ እንባ (Continuous tear) ነው። ይህም እንባ 98% ውኃ ነው። ሦስተኛውና በጣም ጠቃሚው እንባ ደግሞ የውስጥ ስሜት ፈንቅሎ የሚያወጣው እንባ (Emotional tear) ነው። ተጨማሪ ጥናቶች ቢፈልግም የዘርፉ ሊቃውንት እንደሚሉት  በተለይ በኃዘን ጊዜ የሚፈስሰው እንባ ከሌሎቹ እንባዎች በተለየ በሰውነት ውስጥ የተለቀቀውን stress hormone ይዞ በማስወጣት ውጥረትን ለመቀነስ ትልቅ ፋይዳ አለው። ከዚህ እንባ ጋር ተያይዘው በሰውነት ውስጥ የሚለቀቁት እንደ oxytocin እና endorphins ያሉት ሆርሞኖች ደግሞ መረጋጋትና ዕረፍትን እንድናገኝ ያግዙናል።

ይህን የእንባ ጸጋ ለእኛ የሰጠ የሰውን ድካም የሚያውቅ እግዚአብሔር ነው። ልቅሶውንም ለውስጥ ውጥረት ማስተንፈሻ ብቻ ሳይሆን፣ የነፍሳችንን ጉድፍ የምናጠራበትና ወደ እርሱ ይዘን የምንቀርበው የተወደደ መባ አደረገልን። የፈጣሪን የምሕረት ልቡን የምናውክበትና ፈጥኖ እንዲታረቀን ደጅ የምንጠናበትን የእንባ ምንጭ እርሱ ባለቤቱ ከዓይናችን ሥር አኖረ።(መኃል 6፥5) ሊቁ ዮሐንስ ዘሰዋስው እንደ ተናገረው ይህንንም እንባ ወደ ሰማይ ለምንወጣበት የብርሃን መሰላል አንደኛው እርከን አድርጎ ሰጠን።

የምትወደውን ሰው አጥተህ የምታነባ አንተ ሰው "እንዲህ ሳዝን ወዴት አለህ?" ብለህ ፈጣሪህን አትክሰስ። እግዚአብሔርን እንባህ ውስጥ ፈልገው ታገኘዋለህ። የውስጥህን ኃዘን ከሚያበርድበትና ስብራትህን ከሚጠግንበት መንገዶቹ አንዱ  "በሰጠህ እንባ" ነው።

"በደሌንና ነውሬን የሚያጥብ ዕንባ ስጠኝ። አቤቱ አንተን የሚያገለግል ዕንባን ስጠኝ። አቤቱ ልዩ ዕንባን ስጠኝ"
(ውዳሴ አምላክ)

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
አዲስ አበባ
1.3K views✞£iŧsûm✞, edited  16:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 15:17:18 የዶሮ ላባዎች ሲበተኑ

አንድ ወጣት ወደ አንድ ታላቅ አባት ዘንድ ይሄድና አባት እውነት ባልሆነ አሉባልታ የሰውን ስም በማጥፋት የጎዳሁ መሆኔ አሁን ታወቀኝ ።

እና ስለ ሀጢያቴ ምን ላድርግ ብሎ ጠየቃቸው!
እሳቸውም እንዲሁ ሲሉ መለሱለት...ሙሉውን ለማንበብ

                
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun
t.me/sew_hun_ke_sewm_sew_hun

በYoutube ለመከታተል
              
https://www.youtube.com/channel/UCawJZOERphyparnxlMZwa6w
155 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 12:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 15:10:59 አዲስ መንፈሳዊ ትረካ ክፍል 3 "የጠፋው ልጅ" ጸሐፊ @binigirmachew ተራኪ ሜሮን እንዳሻው

ሁላችንም ልናዳምጠው የሚገባ ትረካ ነው የሁሉም ሰው ታሪክ ስለሆነ

ክፍል ሦስት

ይህ ደግሞ አስጨናቂ ነገር ነው።ከአባቴ ቤት ጋር ያለኝ ግንኙነት ተቋርጦ እውነተኛ የሆነ ኪሣራ ላይ ነኝ።


የጠፋው ልጅ አሁን ይጨነቅ ጀመረ(ሉቃ 15፥14)።

ነጻ የምንሆንበትን ጊዜ ብዙ ነገሮችን ማውጣትና ማውረድ ቀላል በሆነ መንገድ እንደምናገኛቸውም ማሰብ የተለመደ ነው።

በአባቱ ቤት ረሐብ፣ጥም ቅዝቃዜ ተሰምቶት አያውቅም።ምክንያቱም ሁሉም ነገር የተትረፈረፈ ነውና።

ፍልስፍና ሁልጊዜ በሞላ ነገር ውስጥ ሆነው የሚያሰላስሉት ነው።ይህ ማለት ምንም የጎደለህ ነገር እስከሌለ ድረስ ስለብዙ ነገሮች ለማሰላሰል ጊዜ ይኖርሀል።

ነገር ግን ስትራብ፣ስትጠማ፣ልጆችህን መመገብ ሳይቻልህ ሲቀር ሌላ ነገር ውስጥ ካለህ ለፍልስፍና ጊዜ የለም።

ያለህበት ሁኔታ እውነታ የሚያሳየው ይህንን ነው።


ከአባትህ ቤት ሳለሁ የሞላልህ፣ደኅነትህ የተጠበቀ ነህ።

እንዲህ ብለህ ታስባለህ...ሙሉ ትረካውን በድምፅ ለማግኘት









75 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 06:51:17
እነሆ አዲስ ቻናል ይዘንሎት መጣን
በማርያም ይህን ቻናል ሳይቀላቀሉ እንዳያልፉ ይደሰቱበታል መርጠን ለናንተ አቀረብንሎ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥
█ 𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒 ➲   █
◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
71 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-11 06:51:04




  Click Here 




44 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ