Get Mystery Box with random crypto!

ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የሰርጥ አድራሻ: @zdfitsumkebe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.71K
የሰርጥ መግለጫ

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-12-02 14:27:24

459 views✞£iŧsûm✞, 11:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-01 10:20:59 +• ኤፍታህ •+

አያድርገውና ጆሮዎቻችን ቢደነቁሩ እና ምላሳችን ቢተሳሰር ሰዎች በሦስት መንገድ ምላሽ ሊሰጡን ይችላሉ:: አንዱ ወገን "እንኳን እንዲህ ሆነበት" ብሎ መዘባበቻ የሚያደርገን ነው፡፡ ሌላው ወገን ደግሞ ክፉ ባይናገርም ለመርዳት ግን አይቀርበንም:: እንዲያው ከሩቅ ሆኖ "አይይ... የእገሌ ነገር እንዲህ ሆነ በቃ?" ብሎ ከንፈር የሚመጥ ይሆናል:: ሦስተኛው ወገን ግን ከደዌያችን የምንፈወስበት ቦታ ፈጥኖ ሊወስደን ይሞክራል:: በሁሉ ነገር ሊረዳንም ዝግጁ ነው፡፡ በወንጌል እንደምናነበው፤ በሦስተኛው ወገን የሚመደቡ መልካም ሰዎች አንድ ደንቆሮ እና ዲዳ የሆነን ሰው ወደ ጌታ ይፈውሰው ዘንድ አመጡት::

እነዚህ ሰዎች ወደ ጌታችን ያመጡትን ሰው ”እኛ አምጥተነዋል፤ ሌላውን እርሱ ይወጣው” ብለው ከፊት አሰልፈው ብቻ አልተውትም:: እንዲፈወስ ጥልቅ ፍላጎት ስለነበራቸው ጌታችን "እጁንም ይጭንበት ዘንድ ለመኑት" (ማር 7:33) ተብሎ ተጽፏል፡፡ እርሱም ይህንን ተመልክቶ ከሰዎች መካከል ለይቶ ወሰደው:: በቃሉ ብቻ መፈወስ የሚችል ጌታ ቢሆንም፤ እርሱ ግን "ጣቶቹንም በጆሮቹ አገባ እንትፍም ብሎ መላሱን ዳሰሰ፤ ወደ ሰማይም አሻቅቦ አይቶ ቃተተና፦ ኤፍታህ፡ አለው፥ እርሱም ተከፈት፡ ማለት ነው። ወዲያውም ጆሮቹ ተከፈቱ የመላሱም እስራት ተፈታ አጥርቶም ተናገረ።" (ማር 7:33-35) ይህ ሰው በእውነት እድለኛ ሰው ነበር:: መታመሙን አይተው ወደ ባለ መድኃኒቱ የሚያመጡ፣ ከዚያም አልፎ ይፈወስ ዘንድ የሚለምኑለት ወዳጆች ነበሩት:: የእኛስ ነገር እንዴት ይሆን? ቅዱስ ቃሉን ለመስማት የተሳነፉ ጆሮዎቻችንን ዓይቶ፣ ለክፋት እንጂ መልካም ለመናገር አልፈታ ያለውን አንደበታችንን ተመልክቶስ ማን መታመማችንን ይወቅልን? ታማችኋል፤ ወደ ባለ መድኃኒቱ ሂዱ ብሎ ማን ወደ ፈዋሹ ዘንድስ ያምጣን?

ጌታ ሆይ፤ እኛስ በብርቱ ታምመናል:: በጥበብህ መስማትን ይሰሙ ዘንድ ያበጀሃቸው ጆሮዎቻችን ክቡር ወንጌልህ ለመስማት ሲሆን ይደነቁራሉ፤ ለከንቱ ወሬ ሲሆን ግን ያለ እክል ይሠራሉ፡፡ ሐሜትን ለመቅዳት ወለል ብለው ይከፈታሉ፤ ተግሳጽህን ለመስማት ግን ይከረቸማሉ:: መልካምን ይናገሩ ዘንድ በጥበብ የፈጠርካቸው ምላሶቻችንም በከንቱ ልፍለፋ ሁሌም ይጠመዳሉ፤ ቅዱስ ቃልህን ለማካፈል ግን ይኮላተፋሉ:: ምላሶቻችን አንተን እንዲያመሰግኑ፣ ሰዎችንም በመልካም ቃላት እንዲያክሙ ብትፈጥርልንም፤ እኛ ግን ሰዎችን በሐሜት እያቆሰልንበት፤ በስድብም እያደማንበት እናሳዝንሃለን:: በንግግራችን አጥንት ማለምለም እንቢ ቢለን፤ ቅስም እየሰበርንበት አለን፡፡

ክቡር መድኃኔዓለም፤ ደንቆሮና ኮልታፋውን ሰው ወዳጆቹ አስበውለት ወደ አንተ አመጡት:: አንተም ጣቶችህን ወደ ጆሮዎቹ አስገባህ:: እንትፍ ብለህም ምላሱን ዳሰስክ:: በዚህም ቸርና ሰውን ወዳጅ መሆንህን አሳየኸን:: ከደጅህ የቆምነውን እኛን ከንቱዎቹን እንደ እርሱ ትፈውሰን ዘንድ ወደ አንተ መጥተናል:: እባክህ፤ ከዓለም ግርግር ለይተህ ውሰደን:: ጆሮዎቻችንን እና ምላሶቻችንንም ዳስስልንና ዝንት ዓለም አንተን እያወደስንህ የምንኖር እንሁን:: ፈዋሽ ቃላቶችህ ከንቱ የሆኑ ጆሮዎቻችንን ዘልቀው ወደ ልባችን እንዲገቡ አድርግልን፡፡ የደነደነ ልቤን አረሰረሰ፣ የተዘጉ ጆሮዎቼን ከፈተ፣ የተቆለፈ አንደበቴንም ፈታ ብለን እንዘምር::

ቸርና ሰውን ወዳጅ ሆይ፤ ለደንቆሮውና ለዲዳው ሰው "ኤፍታህ" ብለህ የተዘጉ ጆሮዎቹን ከፈትክለት፤ የምላሱንም እስራት ፈታህለት፡፡ለቃልህና ለተግሳጽህ ዝግ ሆኖ የቆየውን የእኛን ጆሮ "ኤፍታህ" ብለህ የምትከፍትልን መቼ ይሆን? ለወሬ እንጂ ለንስሃ አልፈታ ያለውን ምላሳችንን፤ ለሐሜት እንጂ ሥጋና ደምህን ለመቀበል አልከፈት ያለው አፋችንንስ "ኤፍታህ" ብለህ የምትከፍትልን መቼ ነው?

ጌታችን ሆይ፤ እኛ ልጆችህ ትፈውሰን ዘንድ አንተን ብለን መጥተናልና ተመልከተን:: እኛንም እዘንልን እና "ኤፍታህ" ብለህ መልካምን ሁሉ ለመስማት የሰነፉ ጆሮዎቻችንን ክፈትልን፤ ክፉን ሁሉ ለመናገር የፈጠነ አንደበታችንንም ለመልካም ፍታልን::

Fresenbet G.Y Adhanom


https://t.me/akanim1wasen2
2.3K viewsወሰንየለው ባህሩ, 07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 11:53:18
“ንጉሡ ዳዊት በታቦተ ጽዮን ፊት ዘለለ፤ ብላቴናው ዮሐንስ ግን ታቦተ ጽዮን ምሳሌ ነበረች ሲል በአማናዊቷ ታቦት በእመቤታችን ፊት ዘለለ፡፡ ዳዊት በታቦተ ጽዮን ፊት ሲዘል ለንጉሣውያን ሕግ አልታዘዘም ነበር፤ ብላቴናው ዮሐንስም በእመቤታችን ፊት ሲዘል የሕፃናትን ሕግ አልጠበቀም፡፡ ከዳዊት በቀር ንጉሥ መዝለሉ ታይቶ ተሰምቶም አይታወቅም፤ ሕፃን መዝለሉም እንዲሁ፡፡”

~ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ

~ እመ አምላክ ወላዲተ አምላክ በጭንቅ ውስጥ ያለውን ሕዝባችን ትታደግልን!

እንኳን አደረሳቹሁ


ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ኅዳር 21 2015 ደብረ ማርቆስ ኢትዮጵያ
3.1K views✞£iŧsûm✞, edited  08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-30 07:59:18 ~ቅድስት_ጽዮን_ድንግል_ማርያም~

ኅዳር ሃያ አንድ በዚች ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የበዓልዋ መታሰቢያ ነው።

~ "ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው። አንድም በምሥጢሩ "ማሕደረ አምላክ" ማለት ነው። ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል።


~ ኅዳር ሃያ አንድ ቀን ጽዮን ማርያምን የምናከብርባቸውን ምክንያቶች።~

#በዚህች_ቀን:-
~ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን።

~ ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ።

~በዘመነ ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በአሚናዳብ ሠረገላ ሁና ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ቅዱሱ ንጉሥ በታላቅ ሐሴት በፊቷ ዘመረ። አገለገለ። ምድራዊ ክብሩን እስኪረሳ ድረስ ለታቦተ አምላክ የተቀኘላት በማሰብ።

~ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ፤

~ የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ፤

~ ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ዕለት በማሰብ፤

~ በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች። በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታልና ይህንንም በማሰብ፤

~ በአብርሃ ወአፅብሃ ዘመነ መንግስት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ አዋጅ የታወጀበትን በማሠብ፤

~ አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ፤

~ በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ዕለት በመሆኑ፤

በእነዚህ ምክንያቶች በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን።


እንኳን አደረሳቹሁ የቻናሌ ቤተሰቦች
እማምላክ ወላዲተ አምላክ ሀገራችንን ከክፍ ሁሉ ትጠብቅልን ።


ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ኅዳር 21 2015 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ ኢትዮጵያ
941 views✞£iŧsûm✞, edited  04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 22:29:51
እንኳን ደስ አላችሁ በዩቲዩብ የምናውቀው #ማኅቶት_ቲዩብ አሁን ደግሞ በቴሌግራም መጥታል ለመቀላቀል ከስር Join የሚለውን ንኩት።

https://t.me/+SLPMr-p0D_QzRyzI
366 views✞£iŧsûm✞, 19:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 14:07:49 ~ኅዳር 21~

እንኳን ለታቦተ ጽዮን አመታዊ በአል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

**በዚች በኅዳር 21ቀን ነቢዮ ዘካርያስ በተቅዋመ ማኅቶት አምሳል ያየበት ፡፡

**እንዲሁም ቀዳሚ ምኒልክ ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የገባበት ፡፡

**እንዲሁም ታቦተ ጽዮን በዮዲት ጉዲት ገዜ በዝዋይ ደሴት ቆይታ ሰላም ሲኾን ተመልሳ
አክሱም የገባችበት ዕለት ነው ፡፡

**በተጨማሪም አብርሀና ወ አጽበሐ(ንጉስ ኢዛና እና ሳይዛነ) በአክሱም ከተማ የታቦተ ጽዮን
ቤተ መቅደሱን ሠርተው ቅዳሴ ቤቱን ያከበሩበት የበአሉ መታሰቢያ ኅዳር 21ቀን
ነው፡፡

በዚች በኅዳር 21 ያረገችው ታአምር ይህ ነው ፍልሰጥኤማውያን ጽዮንን
ማርከው ወደ አዛጦን ወስደው በደጎን ሥር አድርገው ኼዱ፡፡ በነጋው ቢገብ
በግንባሩ ተደፍተው፡፡ አገኙት፡፡ እንደ ነበረው አድርገው ኼዱ፡፡ በነጋው ቢመጡ
እጅ እግሩ ተቁራርጦ ደረቱ ቀርቶ አገኙት፡፡ ከዚያ ወደ ጌት ወደ ምትባል ቦታ
ሰደዷት፡፡ ከዚያም ወደ አስቀሎና ኢሎፋሊ እየተዘዋወረች ለ7ወር ተቀመጠች፡፡


በኃላ ባደረገችው የኀይልና የመቅሰፍት ተአምር ቀንበር ያልተጫነባቸው
ጊደሮች ጠምደው በዐዲስ ሠረገላ ጭነው ካሳ በአይጥ ምስል ወርቅ ሠረተው
ላኳት፡፡
ጊደሮችም ያለ ነጅ ወደ አስራአል ሀገር አምጥተው በቤትሳሚስ ከኢያሱ ዕርሻ
አጠገብ ደርሰው ቆሙ፡፡ የቤተሳሚስም ሰዎች ሠረገላውን ፈልጠው ላሞቹን
ዐርደው መሥዋዕት አቅርበዋል፡፡ ከዚያ ወደ አሚናዳ ቤት መጥታ አልዓዛር
እያገለገት ዳዊት አስኪያመጣት ድረስ 7አመት ድረስ ተቀምጣለች፡፡

(~መድበለ ታሪክ~)


እንኳን አደረሳቹሁ የቻናሌ ቤተሰቦች

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ኅዳር 20 2015 ዓ.ም
2.6K views✞£iŧsûm✞, 11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-29 11:26:25 "አንድ በሩሲያ የሚተረት ተረት አለ " አንድ ሽማግሌ ሰው ዛፍ ሲተክል ያዩት ወጣቶች "ይህ ዛፍ የሚያፈራው ከብዙ ዓመታት በኋላ ነው።  አንተ እስከዚያ ልትቆይ አትችልም ለምን በከንቱ ትደክማለህ ?" አሉት። እርግጥ ነው እኔ አርጅቻለሁ። ነገር ግን ሰው የተከለውን በልቻለሁና እኔም ተክዬ ማለፍ ፣ ብድሬን መክፈል አለብኝ" ብሎ መለሰላቸው ይባላል ... አሉ " ፊታውራሪ ተክለሐዋርያት  ኦቶባዮግራፊ  መግቢያ ግርጌ ማስታዎሻ ላይ ።
   ------------
በተለይ ደግሞ የእኛ  ዘመን ኢትዮጵያውያን  የራሱን ምቾት መስዋእት አድርጎ  የሚቀጥለውን ትውልድ አስቦ ካልሰራ  ምናልባትም የምናስረክባቸው ነገር ላይኖር ሁሉ ይችላል ። ቢያንስ የእኛ አባቶች ሉዓላዊት ሀገር ከነ ሙሉ ክብሯ አስረክበውን ነበር ፤ በቀደሙት አባቶች ደምና አጥንት በተገነባች  ሀገር ላይ ስንኖር እዳ እንዳለብን ተገንዝበን እኛም የተሻለች ሀገር ሰርተን ለሚቀጥለው ትውልድ ለማስረከብ ዛሬ በትብብር  የማንበላው ኬክ ጋግረን ለሚቀጥለው ትውልድ ማቅረብ አለብን !
ከሠለጠኑት ሀገራትም የምንማረው ይኸንን ነው ።

         (~Tesgaw mamo~)
3.3K views✞£iŧsûm✞, 08:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-28 15:11:21
ጉባኤ ቴኦቶኮስ!

ቴኦቶኮስ ማለት የአምላክ እናት ማለት ነው።

በአዶላ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የዓመቱ ሶስተኛ ዙር ወርኃዊ ጉባኤ ከህዳር 21 እስከ 24 ቀን ድረስ ለተከታታይ አራት ቀናት በድምቀት ይካሄዳል።

እርሶም ከተዘጋጀው መንፈሳዊ ማዕድ ይሳተፉ ዘንድ በወላዲተ አምላክ ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!

በጉባኤ መገኘት ኦርቶዶክሳዊ ግዴታዬ ነው! በማለት ቃለ እግዚአብሔር ለመስማት እንፋጠን!

መቅረት ያስቆጫል!

ለዕለቱ ያድርሰን!
678 viewsወሰንየለው ባህሩ, 12:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-28 15:09:36 +++ ልሸፈንላችሁ? +++

ሙሴ ከሲና ተራራ ወርዶ ከሕዝቡ ጋር ሲገናኝ የፊቱን ማንጸባረቅ አይተው "ተሸፈንልን" ያሉት ሕዝቡ ናቸው። እርሱ "ከእግዚአብሔር ጋር ስነጋገር ቆይቼ እኮ አሁን መውረዴ ነው? ምነው የፊቴ ብርሃን አስቸገራችሁ? ልሸፈንላችሁ እንዴ?" አላለም። እንዲያውም ቅዱስ መጽሐፍ "ሙሴም ከተራራው በወረደ ጊዜ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ተነጋገረ የፊቱ ቁርበት እንዳንጸባረቀ አላወቀም ነበር" ነው የሚለው።(ዘጸ 34፥29) ለቅዱሳን እግዚአብሔር በፊታቸው የሚሥለው የክብር ብርሃን እነርሱን ለሚመለከታቸው እንጂ ለራሳቸው አይታወቃቸውም። እውነተኞቹ ቅዱሳን  "ተሸፈኑልን" የሚባሉ እንጂ "ልሸፈንላችሁ" የሚሉ አይደሉም።

ጥቂት በጎ ሥራ ሠርተህ ጻድቅነትህን በግድ ለማሳየት አትሞክር። ሌሎች ተሸፈንልን ይበሉህ እንጂ፣ አንተ ራስህ "ልሸፈንላችሁ" እያልህ የዋሐንን አታስጨንቅ።

በአገራችን የሚታወቅ ተረት አለ። አንድ ጊዜ ትንኝ በሬ ቀንድ ላይ ቆመችና "ከብጄህ እንደ ሆነ ንገረኝና ልነሣልህ" አለችው። በሬውም "እንኳን ልትከብጅኝ መኖርሽንም አላወቅሁም" አላት።

"ጻድቃን እንደ ሆኑ በራሳቸው ለሚታመኑና ሌሎቹን ሁሉ በጣም ለሚንቁ ይህን ምሳሌ ነገራቸው"   ሉቃስ 18፥9

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
አዲስ አበባ

          ( ቃለ ሕይወት ያሰማልን:: የሚደንቅ ነው:: "ማብራቱ አይታወቀውም ነበር" የሚያሳዝነው እነሱ ቅድስናቸው እንደማይታወቃቸው እኛም ኃጢአታችን አይታወቀንም:: ልብስ ሲቆሽሽ አይታወቀውም አይደል?    "ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ" )
671 views✞£iŧsûm✞, edited  12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-28 09:35:50 ክፍል -3

~ ወንጌል  ኦሪት እና ቁርኣን ~
                      ምን ዓይነት ሕግጋት ናቸው ~?

አቡ-ፈረጅ ባር ሄበሪዮስ(ወልደ ዕብራዊ) በበኩሉ የእስልምና ሕግ ከአይሁድ(ከብሉይ ኪዳን) እና ከክርስቲያኖች(ወንጌል) ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ሃይማኖቶች የተቀየጠ እንሆነ ይጠቁማል የትኛው ሕግ ከየትኛው ሃይማኖት እንደተወሰደም ይዘረዝራል።

"ባር ሄባርዮስ" እንደሚለው ከክርስትና ክርስቶስን የእግዚአብሔር ቃል ማለት ከአይሁድ ግዝረት ከአሕዛብ(ግመልን ጨምሮ) የእንስሳት መሥዋዕት ከከለዳውያን በእጣ ፈንታ ማመንን (ቀድሞ መወሰን) ከግብጻውያን ጥንቆላን ከሰዱቃውያን ከትንሳኤ በኋላ የመጋበትን አስተምህሮ ከሰባልዮሳውያን እግዚአብሔር በአካል በገጽ አንድ ነው የሚል አስተምህሮ ከአርዮሳውያን የእግዚአብሔር ቃል ፍጡር ማለትን ከምትሓተኛው ዑልያኖስ ክርስቶስ አልተሰቀለም ማለትን ወስዷል።


ወደ "ጴጥሮስ አልፎንሲ" ሐተታ እንመለስ። ጴጥሮስ የእስልምና ሕግ የብሉይ ኪዳን(ተውራት) እና የወንጌል ቅይጥ የሆኑ ሕግጋት እንደያዘ ለማሳየት እንደ ምሳሌ የሚያነሣው በቀን አምስት ጊዜ መጸለይን ነው። እርሱ ራሱ ከአይሁድ እምነት ወደ ክርስትና የተመለሰው ጴጥሮስ አይሁድ በቀን ሦስት ጊዜ እንደሚጸልዩ እና በክርስትና ደግሞ ሰባት የጸሎት ጊዜያት እንዳሉ ያስረዳል። የእስልምናው ነብይ ሙሐመድ አምስት የጸሎት ጊዜያት ያዘዘው በአይሁድ (3) እና በክርትና(7) መካከል ያለውን ቁጥር ወስዶ ነው ይላል ጴጥሮስ ።ዮሐንስ ዘሰጎቪያም ተመሳሳይ ነጥብ አንሥቷል ። ለፍጹም የወንጌል ሕግ ማድረሻ የነበረው የሙሴ ሕግ ፍጻሜ በሆነው በወንጌል ሕግ ከተተካ በኋላ ወደኋላ ተመልሶ ሁለቱን መቀላቀል ሁለቱንም ማጥፋት ነው! ይላል ዮሐንስ።

በቁርኣን የተጻፈው የእስልምና ሕግም በሙሴ እና በወንጌል ሕግጋት መካከል ያለውን ግኑኝነት ስለሚያበላሽ እና ድንበራቸውን ስለሚያጠፋ በእጅጉ ይነቅፈዋል።
ከእነዚህ ምዕራባውያን ሊቃውንት በዘመን ወደ ሚቀድመው ወደ ክርስቲያኑ አል-ኪንዲ ተመሳሳይ ሐተታ እንመለስ እነዚህ ሁለቱ ሕግጋት(ኦሪትና ወንጌል) ቀድመው በሁለቱ ኪዳናት የተረጡ መሆናቸው ጠቁሞ ሁለቱን ቀላቅሎ ሌላ ሦስተኛ ሕግ መፍጠር እንደማይቻል ያስረዳል 'ጠላትህን ውደድ' የሚል ሕግና 'የሰው ዓይን ያጠፋ አይኑ ይጥፋ' የሚል ሕግ በአንድነት ሊተገበሩ አይችሉምና! ሦስተኛ ሕግ አስፈላጊ ከሆነ በሁለቱም ሕግጋት ያልተሰጡ ሌላ ከፍ ያሉ ሕግጋትን ለመጨመር ነው ይህ ደግሞ ከወንጌልም አልጎደለም በቁርአን ውስጥም አልጨመረም -ይላል አል-ኪንዲ ።

የወንጌል ሕግ ሰዎች በአስተሳሰባቸው እና በምግባራቸው አምላካቸውን እግዚአብሔርን እንዲመስሉት የሚያስችሉ ትዕዛዛትን የያዘ እና ይህን ለመፈጸም ኃይል የሚያገኙበትን መንገድም የሚያሳይ በመሆኑ ከወንጌል የበለጠ ከፍ የሚያደርግ ሕግ ሊኖር አይችልም በምግባር እግዚአብሔርን ከመምሰል በላይ መሔድ አይቻልምና። ወንጌል ስለራሱ የሚናገረውም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የማይስተካከል እና የማይታደስ የጸና ፍጹም ሕግ እንደሆነ ነው።

ይቀጥላል .......

(የልቦና ችሎት)
133 views✞£iŧsûm✞, edited  06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ