Get Mystery Box with random crypto!

ክፍል -3 ~ ወንጌል  ኦሪት እና ቁርኣን ~                       ምን ዓይነት ሕግ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

ክፍል -3

~ ወንጌል  ኦሪት እና ቁርኣን ~
                      ምን ዓይነት ሕግጋት ናቸው ~?

አቡ-ፈረጅ ባር ሄበሪዮስ(ወልደ ዕብራዊ) በበኩሉ የእስልምና ሕግ ከአይሁድ(ከብሉይ ኪዳን) እና ከክርስቲያኖች(ወንጌል) ብቻ ሳይሆን ከሌሎች ሃይማኖቶች የተቀየጠ እንሆነ ይጠቁማል የትኛው ሕግ ከየትኛው ሃይማኖት እንደተወሰደም ይዘረዝራል።

"ባር ሄባርዮስ" እንደሚለው ከክርስትና ክርስቶስን የእግዚአብሔር ቃል ማለት ከአይሁድ ግዝረት ከአሕዛብ(ግመልን ጨምሮ) የእንስሳት መሥዋዕት ከከለዳውያን በእጣ ፈንታ ማመንን (ቀድሞ መወሰን) ከግብጻውያን ጥንቆላን ከሰዱቃውያን ከትንሳኤ በኋላ የመጋበትን አስተምህሮ ከሰባልዮሳውያን እግዚአብሔር በአካል በገጽ አንድ ነው የሚል አስተምህሮ ከአርዮሳውያን የእግዚአብሔር ቃል ፍጡር ማለትን ከምትሓተኛው ዑልያኖስ ክርስቶስ አልተሰቀለም ማለትን ወስዷል።


ወደ "ጴጥሮስ አልፎንሲ" ሐተታ እንመለስ። ጴጥሮስ የእስልምና ሕግ የብሉይ ኪዳን(ተውራት) እና የወንጌል ቅይጥ የሆኑ ሕግጋት እንደያዘ ለማሳየት እንደ ምሳሌ የሚያነሣው በቀን አምስት ጊዜ መጸለይን ነው። እርሱ ራሱ ከአይሁድ እምነት ወደ ክርስትና የተመለሰው ጴጥሮስ አይሁድ በቀን ሦስት ጊዜ እንደሚጸልዩ እና በክርስትና ደግሞ ሰባት የጸሎት ጊዜያት እንዳሉ ያስረዳል። የእስልምናው ነብይ ሙሐመድ አምስት የጸሎት ጊዜያት ያዘዘው በአይሁድ (3) እና በክርትና(7) መካከል ያለውን ቁጥር ወስዶ ነው ይላል ጴጥሮስ ።ዮሐንስ ዘሰጎቪያም ተመሳሳይ ነጥብ አንሥቷል ። ለፍጹም የወንጌል ሕግ ማድረሻ የነበረው የሙሴ ሕግ ፍጻሜ በሆነው በወንጌል ሕግ ከተተካ በኋላ ወደኋላ ተመልሶ ሁለቱን መቀላቀል ሁለቱንም ማጥፋት ነው! ይላል ዮሐንስ።

በቁርኣን የተጻፈው የእስልምና ሕግም በሙሴ እና በወንጌል ሕግጋት መካከል ያለውን ግኑኝነት ስለሚያበላሽ እና ድንበራቸውን ስለሚያጠፋ በእጅጉ ይነቅፈዋል።
ከእነዚህ ምዕራባውያን ሊቃውንት በዘመን ወደ ሚቀድመው ወደ ክርስቲያኑ አል-ኪንዲ ተመሳሳይ ሐተታ እንመለስ እነዚህ ሁለቱ ሕግጋት(ኦሪትና ወንጌል) ቀድመው በሁለቱ ኪዳናት የተረጡ መሆናቸው ጠቁሞ ሁለቱን ቀላቅሎ ሌላ ሦስተኛ ሕግ መፍጠር እንደማይቻል ያስረዳል 'ጠላትህን ውደድ' የሚል ሕግና 'የሰው ዓይን ያጠፋ አይኑ ይጥፋ' የሚል ሕግ በአንድነት ሊተገበሩ አይችሉምና! ሦስተኛ ሕግ አስፈላጊ ከሆነ በሁለቱም ሕግጋት ያልተሰጡ ሌላ ከፍ ያሉ ሕግጋትን ለመጨመር ነው ይህ ደግሞ ከወንጌልም አልጎደለም በቁርአን ውስጥም አልጨመረም -ይላል አል-ኪንዲ ።

የወንጌል ሕግ ሰዎች በአስተሳሰባቸው እና በምግባራቸው አምላካቸውን እግዚአብሔርን እንዲመስሉት የሚያስችሉ ትዕዛዛትን የያዘ እና ይህን ለመፈጸም ኃይል የሚያገኙበትን መንገድም የሚያሳይ በመሆኑ ከወንጌል የበለጠ ከፍ የሚያደርግ ሕግ ሊኖር አይችልም በምግባር እግዚአብሔርን ከመምሰል በላይ መሔድ አይቻልምና። ወንጌል ስለራሱ የሚናገረውም እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የማይስተካከል እና የማይታደስ የጸና ፍጹም ሕግ እንደሆነ ነው።

ይቀጥላል .......

(የልቦና ችሎት)