Get Mystery Box with random crypto!

ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የሰርጥ አድራሻ: @zdfitsumkebe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.71K
የሰርጥ መግለጫ

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-12-11 06:50:52 አዲስ መንፈሳዊ ትረካ ክፍል 2 "የጠፋው ልጅ" ጸሐፊ @binigirmachew ተራኪ ሜሮን እንዳሻው

ሁላችንም ልናዳምጠው የሚገባ ትረካ ነው የሁሉም ሰው ታሪክ ስለሆነ


ክፍል ሁለት

ጠፍተህ ልትሄድ እንደምትችል አውቃለሁ።ለጥፋትና በኃጢአት ሕይወት እንደምትኖርም አውቃለሁ።ነገረ ግን ጥበበኛ ሆነህ ወደ እኔ ወደ አባትህ ቤት ትመለስ ዘንድ እጠብቅሃለሁ።የጠፋው ልጅ ብዙ ስለቸገረወ ወደ አባቱ ቤት ለመመለስ አሰበ።(ሉቃ11፥13)ረጅም ጊዜ አልፈጀበትም።
እኛ ወደ ኃጢአት ለመሮጥ ምን ያህል እንፈጥናለን? ከእግዚአብሔር ለመራቅ ሕይወታችንን በችግር መካከል እንዲሁም በፈተና ውስጥ የምናልፍበት ጊዜ ምን ያህል ነው?


ብዙ ጊዜ አልፈጀበትም ማድረግ የሚገባውን ነገር ምን እንደሆነ አላሰበም።አንዳንድ ጊዜ በኃጢአት ጊዜያዊ ደስታ እንታውራለን...ሙሉ ትረካውን በድምፅ ለማግኘት












Subscribe like share ማድረግ እንዳትረሱ መንፈሳዊ ቻናሎችን እንደግፍ
34 viewsዲያቆን አቤንዔዘር ሙሉ, 03:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 19:39:31
ሰበር ዜና!

ታላቁ የዝቋላ ደብረ ከዋክብት ገዳም በታጠቁ ኃይሎች እየታመሰ ይገኛል ፡፡

የበርካታ መናንያን መኖሪያ ታላቁ የዝቋላ ደብረ ከዋክብት ገዳም በታጠቁ ኃይሎች እየታመሰ ይገኛል ፡፡ ማምሻው የታጠቁ ኃይሎች በሁሉም አቅጣጫ ወደ ገዳሙ ሰብረው በመግባ መነኮሳትን በማገት ገዳሙን እያመሱት ይገኛል ፡፡

ሚዲያችን የሚመለከታቸውን አካላት ቦታው ድረስ በመደወል እየደረሰባቸው የሚገኘውን እንግልት ተረድተናል "ከገዳሙ የጥበቃ ኃይሎች የሚገኙትን መሣሪያዎች በከበባ ነጥቀዋል ፡ ገዳሙን በሁሉም አቅጣጫ በመግባት እያስጨነቁ ይገኛሉ ሦስት አገልጋዮችን አግተዋቸዋል ድረሱል ድረሱልን" የሚል ድምፅን አሰምተዋል ሲል ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ ዘግቧል።

መረጃው የተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ነው።
968 views✞£iŧsûm✞, edited  16:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-10 10:26:58 † ታላቁ ነቢይ "#ቅዱስ_ኤልያስ †
ታህሳስ 1 በዓለ ልደቱ

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ ቀጥላ ቅዱስ ኤልያስን ታከብራለች:: "ርዕሰ ነቢያት - የነቢያት ራስም" ትለዋለች:: እርሱ ሰማይን የለጐመ: እሳትን ያዘነመ: ፍጥረትንም በቃሉ ያዘዘ አባት ነውና:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-

ቅዱሱ ትውልዱ ነገዱ ኢዮርብዓም ነጥሎ ከወሰዳቸው እሥራኤል ፲ሩ ነገድ ሲሆን
አባቱ "#ኢያስኑዩ" :
እናቱ ደግሞ "ቶና [ቶናህ]" ይባላሉ::

በጐ አምልኮ ነበራቸውና እግዚአብሔር ማሕጸነ ቶናህን ቀድሶ ይህንን ቅዱስ ፍሬ ፈጠረ::

#ቅዱስ_ኤልያስ በተወለደ ቀን በቤታቸው ብርሃን ተሞልቶ ታይቷል:: ብርሃን የለበሱ ፬ ሰዎች [መላእክት] መጥተውም በእሳት ሰፋድል [መጐናጸፊያ] ሲጠቀልሉት ወላጆቹ በማየታቸው ደንግጠው ለነቢያትና ለካህናት ነገሯቸው::

ካህናቱ ግን ነገሩ ቢረቅባቸው "ምን ዓይነት ፍጥረት ይሆን? በእሥራኤል ይነግሥ ይሆን! ወይስ ነቢይ ይሆን?" ብለውም አድንቀዋል:: ቅዱስ ኤልያስ ከልጅነቱ ጀምሮ ኮስታራ: ቁም ነገረኛ: ንጽሕናንም የሚወድ እሥራኤላዊ ነው::

ወቅቱ [ከክርስቶስ ልደት ፱ መቶ ዓመት በፊት] ሕዝቡና ነገሥታቱ የከፉበት: እግዚአብሔር ተክዶ ጣዖት የሚመለክበት ነበር:: ድሮ በኢሎፍላውያን እጅ የነበሩት ጣዖታት [ዳጐንና ቤል] በዚያ ዘመን ወደ እሥራኤል ገብተው ነበር::

#ቅዱስ_ኤልያስ ግን በዚህ ክፉ ትውልድ መካከል ሆኖም ሥርዓተ ኦሪትን የጠነቀቀ: የንጽሕናና የአምልኮ ሰው ነበር::

በዚያ ወራትም እግዚአብሔር ለነቢይነት ጠራው:: እርሱም "እሺ" ብሎ ታዞ የእግዚአብሔርን የጸጋ ጥሪ ተቀበለ::

ቅዱሱ ብዙ ጊዜ ለጉዳይ ካልሆነ ከሰው ጋር መዋል: ማደርን አይወድምና መኖሪያውን በተራሮችና በዱር አደረገ::

በተለይ ደብረ ቀርሜሎስ ለእርሱ ቤቱ ነበር:: በዚህ ሕይወቱም ከመልከ ጼዴቅ ቀጥሎ :-

፩. ለድንግልና [ድንግል ነበርና]
፪. ለብሕትውና [ብቸኛ ነበርና]
፫. ለምንኩስና [ተሐራሚ ነበርና] በብሉይ ኪዳን መሠረትን የጣለ ነቢይ ይባላል::

መቼም በብሉይ ኪዳን የቅዱስ ኤልያስን: በዘመነ ክርስቶስ የመጥምቁ ዮሐንስን: በዘመነ ሊቃውንት ደግሞ የአፈ ወርቅ ዮሐንስን ያህል ደፋርና መገሥጽ አስተማሪ አልነበረም:: በጊዜው ደግሞ አክአብና ኤልዛቤል የሚባሉ ክፉ ባልና ሚስት በእሥራኤል ላይ ነግሠው ሕዝቡን ጣዖት አስመለኩት::

ይባስ ብለው ደግሞ በወይኑ እርሻ አማካኝነት ኢይዝራኤላዊው ናቡቴን በሃሰት ምስክር ደሙን አፈሰሱት:: ናቡቴም "የአባቶቼን ርስት አልሸጥም: አልለውጥም::" በማለቱ እንደ ሰማዕት ይቆጠራል::

#ኤልያስ ግን ይህንን ሲሰማ ወደ አክአብና ኤልዛቤል ቀርቦ "የናቡቴ ደም በእናንተ ላይ አይቀርም:: የአንቺንም ደም ውሻ ይልሰዋል" አላቸው:: በዚህ ምክንያትም ኤልዛቤል ልትገድለው ብትፈልገውም እርሱ የእግዚአብሔር ነውና አላገኘችውም::

በዚህ ብስጭትም ይመስላል አንድ ሺህ ነቢያትን ሰብስባ "ፍጇቸው" አለች:: ፱ መቶው ሲታረዱ አንድ መቶውን ግን ቅዱስ አብድዩ በዋሻ ውስጥ ደብቆ እየመገበ አተረፋቸው:: በእሥራኤል ውስጥ ግን ዓመጻና ኃጢአት እየተስፋፋ ሔደ:: የእግዚአብሔርን ስጦታ እየተመገበ ሕዝቡ ለቤል [ለበዓል] ሰገደ::

ይህን ጊዜ ግን #ቅዱስ_ኤልያስ እንዲህ አለ :- "ሕያው እግዚአብሔር አምላከ ኃይል: ዘቆምኩ ቅድሜሁ: ከመ ኢይረድ ጠል በእላ መዋዕል ዘእንበለ በቃለ አፉየ::" ብሎ ዝናም ከሰማይ እንዳይወርድ ከለከለ::

ለ፫ ዓመታት ከ፮ ወራት ሰማይ ዝናም ለዘር ጠል ለመከር ከመስጠት ተከለከለ::

ሕዝቡ በኃጢአቱ ምክንያት ተጐዳ:: እርሱን ቁራ ይመግበው: ምንጭ ፈልቆለት ይጠጣ ነበር:: ይሔው ቢቀርበት ጸለየ:: እግዚአብሔርም ከፈለገ ኮራት ወደ ሰራፕታ እንዲወርድ አዘዘው:: በዚያም የነቢዩ ዮናስ እናት እንጐቻ ጋግራ ብታበላው ቤቷ በበረከት ተሞላ::

ልጇ ሕጻኑ ዮናስ ቢሞትም በጸሎቱ አስነሳላት:: ቀጥሎም ፯ ጊዜ በትጋት ጸልዮ ለ፫ ዓመታት ከ፮ ወራት የዘጋውን ሰማይ ከፍቶታል:: ሕዝቡም ዕለቱኑ ከበረከቱ ቀምሰዋል::

ከዚያ አስቀድሞ ግን ከኤልዛቤል ፰ መቶ ፶ ነቢያተ ሐሰትና ካህናተ ጣዖት ጋር ተወዳድሮ አሸንፏቸዋል:: መስዋዕት ሰውተው የእርሱን ብቻ እሳት ከሰማይ ወርዳ በልታለታለችና ሕዝቡ ፰ መቶ ፶ ውን ሐሰተኛ ነቢያት በወንዝ ዳር በሰይፍ መትተዋቸዋል::

ይሕንን የሰማች ኤልዛቤልም ትገድለው ዘንድ አሳደደችው:: "አቤቱ ከአባቶቼ አልበልጥምና ውሰደኝ! ብቻየን ቀርቻለሁና" ብሎ ቢጸልይ እግዚአብሔር ለጣዖት ያልሰገዱ ሰባት ሺህ ሰዎችን እንዳተረፈ: እርሱንም ወደ ብሔረ ሕያዋን እንደሚወስደው ብሥራትን ነገረው::

ደክሞት ተኝቶ ሳለም ቅዱስ መልአክ [ሚካኤል] ቀስቅሶ ታየው:: እንጐቻ ባገልግል: ውሃ በመንቀል አቅርቦ "ብላ! ጠጣ!" አለው:: በላ: ጠጣ: ተኛ:: እንደ ገና ቀስቅሶ አበላው:: በ፫ኛው ግን "ብላዕ እስከ ትጸግብ እስመ ርሑቅ ፍኖትከ - ጐዳናህ ሩቅ ነውና እስክትጠግብ ብላ" አለው::

ኤልያስም ለ፵ ቀናት ያለ ምግብ ተጉዟል:: ከዚያ በሁዋላም ምድራዊ ሕብስትን አልተመገበም:: እግዚአብሔር አክአብና ኤልዛቤልን ከተበቀላቸው በሁዋላም ቅዱስ ኤልያስ በክፋተኞች ላይ ፪ ጊዜ እሳትን አዝንሟል::

የሚያርግበት ጊዜ ሲደርስም ደቀ መዝሙሩን ኤልሳዕን "የምትሻውን ለምነኝ" ቢለው "እጥፍ መንፈስህን" አለው:: ፫ ጊዜ ሊያስመልሰው ሞከረ:: ቅዱስ ኤልሳዕ ግን በብርታት ተከተለው:: ዮርዳኖስን ከፍለው ከተሻገሩ በሁዋላ ግን ቅዱስ ኤልያስን ሠረገላ እሳት ወርዶ ነጠቀው:: ለኤልሳዕም እኩሉን ግምጃውን ጣለለት::

ዛሬ #ቅዱስ_ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን ያለ ሲሆን በዘመነ ሐሳዌ መሲሕ መጥቶ በሰማዕትነት ከቅዱስ ሔኖክ ጋር ያርፋል::

/ ሥንክሳር ዘታህሳስ 1 /
( ከ፩ነገ.፲፯ - ፪ነገ.፪, እና ዕርገተ ኤልያስን ያንብቡ )


የታላቁ ነቢይ የቅዱስ ኤልያስ
ረድኤት በረከት አይለየን
429 views✞£iŧsûm✞, 07:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-09 11:35:43 ሊያርስ እንደወጣ..
ተይዟል በአፈር ፤
ይዟል ሞፎር ፡
ተከልቷል ተብሎ ዘር ።
ያልቅሳል ሰሚ የታል
ጩህት ሞትን ፤
ጠርቶበታል ።
ህፃን ነው አበባ ፡
አይደግ ሰለምን እንባባ ።
ክፍት ያጎፈረው
ከጥልቅ የሚኖረው ፤
ስለተዋረሰው ።
ሳያስብ ሲያሳስብ ህይወትን
ልጅ እናት የሚያጎርስ እሳትን
እግዚኦ ስማ ከላይ
ሙት ስንቆጥር ስታይ ።


~ ዲያቆን ፍፁም ከበደ~
938 views✞£iŧsûm✞, edited  08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 22:19:23
እንኳን ደስ አላችሁ በዩቲዩብ የምናውቀው #ማኅቶት_ቲዩብ አሁን ደግሞ በቴሌግራም መጥታል ለመቀላቀል ከስር Join የሚለውን ንኩት።

https://t.me/+SLPMr-p0D_QzRyzI
275 views✞£iŧsûm✞, 19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 22:19:23
.

ለፕሮፋይል ፒክቸር የሚሆኑ መንፈሳዊ ፎቶዎችን ማግኘት ይፈልጋሉ መልሶት አዎ ከሆነ ከስር ያለውን ሊንክ በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ


https://t.me/+YkS5xznutqNjZTE0
https://t.me/+YkS5xznutqNjZTE0
https://t.me/+YkS5xznutqNjZTE0
282 views✞£iŧsûm✞, 19:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 21:36:03
እንኳን ደስ አላችሁ በዩቲዩብ የምናውቀው #ማኅቶት_ቲዩብ አሁን ደግሞ በቴሌግራም መጥታል ለመቀላቀል ከስር Join የሚለውን ንኩት።

https://t.me/+SLPMr-p0D_QzRyzI
80 views✞£iŧsûm✞, 18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 21:36:03
.

ለፕሮፋይል ፒክቸር የሚሆኑ መንፈሳዊ ፎቶዎችን ማግኘት ይፈልጋሉ መልሶት አዎ ከሆነ ከስር ያለውን ሊንክ በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ


https://t.me/+YkS5xznutqNjZTE0
https://t.me/+YkS5xznutqNjZTE0
https://t.me/+YkS5xznutqNjZTE0
72 views✞£iŧsûm✞, 18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-08 13:49:51 "የብልጽግና ወንጌል" የሚለው አስተምህሮ እምነት በፕሮቴስታንቶች ውስጥ ባሉ በተለያዩ ግለሰቦችና አንጃዎች የሚታመን እምነት ሲኾን ፣ ዋናው አስተምህሮውም የእግዚአብሔር ዋናው ፍቃድ በእርሱ የሚያምኑ ሰዎች ኹሉ ሀብታሞች ጤናማዎች እንዲኾኑ ነው የሚል ነው ። የብልጽግና ወንጌል አማኞች አስተማሪዎች ሰዎች በእርሱ ካመኑ እግዚአብሔር ደግሞ ሀብትን ጤናን አብዝቶ ይሰጣቸዋል ፤ ቤተሰባዊ ሕይወታቸው ተድላ ደስታ የመላበት ፥ ስራቸው ሁሉ የተቃናና አልጋ በአልጋ ይኾናል ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ በእግዚአብሔርና በአማኙ መካከል ላለው ለዚህ ስምምነት የውል ማረጋገጫ ነው ይላሉ ። ይህ አስተምህሮ እንግዲህ ሰዎች እነርሱ ካሰቡት ሐሳብ ጋር ምድራዊ ፍላጎታቸውን የሚያሳካላቸው ሆኖ ስለሚያገኙት ይቀላቀሉት ዘንድ ይወዳሉ ።

ክርስትና ከዚህ ይለያል እኛስ ሐገራችን በሰማይ ነው ማለት በምድር እያለን ምድርን ሰማይ አድርገን መኖር መቻል ክርስቶስ ለእኛ እንዳሰበልን መኖር እንጂ እኛ እንዳሰብነው መኖር አለመሻት ማለት ነው ።

~ዲያቆን ፍፁም ከበደ~
2.5K views✞£iŧsûm✞, 10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ