Get Mystery Box with random crypto!

ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የሰርጥ አድራሻ: @zdfitsumkebe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.71K
የሰርጥ መግለጫ

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-12-07 16:22:02 የዘማሪዋ ቤተ ክርስትያን መስራች ከሆኑት ውስጥ አንዱ ማርቲን ሉተር (Marthin Luther) እንኳ ቅድስት እናት ድንግል ማርያምን "የሰማያዊው ዓለም እመቤትና ንግሥት'' በማለት አክብሮቱን የሚገልፅ ነበር።
በዚህም ምክንያት ጆን ካልቪን እና ዝዊንግሊ በተባሉ ሌላ የዚሁ እምነት ፅንፈኛ አራማጆች ሉተርን አምልኮተ ሰብዕ (ፍጡር) አራማጅ ነው በማለት እንደ ሰሞነኛው ፓስተር ነኝ ባይ ይቃወሙት ነበር።
ብልህ ነኝ ባይ ከዚህም መማር ይችል ይመስለኛል።


~Ephraim soliana~
2.2K views✞£iŧsûm✞, 13:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 14:55:23
~ዜና ተዋሕዶ~

የኤርትራው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ሥርዓተ ቀብር ላይ ለመገኘት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች ወደ አስመራ ያቀናሉ !

ሕዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ቀዳማዊ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በቅዱስነታቸው ሥርዓተ ቀብር ላይ የሚገኙ ልዑካንን በዛሬው ዕለት ወደ አስመራ እንዲጓዙ ወስኗል።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የታላቋ ብሪታኒያ እና የሩቅ ምሥራቅ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ተመድቦው በአስመራ በሚካሄደው ሥርዓተ ቀብር ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ይወክላሉ።

ተ.ሚ.ማ እንደደረሰው መረጃ የቅዱስነታቸው አቡነ ቄርሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘሀገረ ኤርትራ ግብዓተ መሬት በነገው ዕለት በአስመራ ቅድስት ማርያም ካቴድራል ይከናወናል።


~ምንጭ~

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ
3.4K views✞£iŧsûm✞, edited  11:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-07 11:04:45 አንቲዮች (st Antioch) የተባለው ሊቅ ጠላታችን ተስፍ በማስቆረጥ ሲያጠቃን እጃችንን ልንሰጠው አይገባም ። ይልቁንም ጠንካሮችና በእምነት ብርሃን ውስጥ ራሳችንን ሰውረን የምንከላከል ልንኾን ይገባናል ይለናል ። አክሎም ክፍ መንፈስ ተስፍ ሊያስቆርጠን ሲሻ በጥብዓት ኾነን እንዲህ ልንለው ይገባል ፦ (ከእግዚአብሔር የተለየ ፥ ከገነት የተባረርክ ክፍ አገልጋይ አንተ ለእኛ ምንድ ነህ ? የአንተ ድፍረት ለእኛ ምንም አያደርግም ። የእግዚአብሔር ልጅ የኾነው ክርስቶስ በእኛም ላይ ስልጣን አለውና ።) በማለት ክርስቶ ከእኛ ጋር ከኾነ ተስፍ በመቁረጥ ለዲያብሎስ ከታዘዘው ከአስቆሮቱ ይሁዳ ጋር ምንም ዓይነት ኅብረት ሊኖረን እንደማይችል ነገረን ።

( ~ኦርቶዶክሳዊ አእምሮ~)
3.5K views✞£iŧsûm✞, 08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 15:03:38
አንድ በጣም ትልቅ ቆሻሻ የጫነ ጋሪ የሚገፋ ሰው ወደ ቤትህ መጥቶ "እባክህ በርህን ክፈትልኝና ይህን ቆሻሻ አንተ ቤት ላራግፈው?" ቢልህ፣ "ውይ የሚጥልበት ቢያጣ ነው። ባይቸገር ወደ እኔ አይመጣም ነበር" ብለህ ደጅህን ከፍተህ ታስገባዋለህ? በፍጹም፤ እንደውም "እንዴት ብታስበኝ ነው? ምነው ስታየው ቤት አልመሰለህም? እንዴት ሰው በሚኖርበት ቤት ቆሻሻ ካልደፋሁ ትላለህ? ስትል ለጠብ ትጋበዛለህ። መደፈርህ እያንገበገበህ "እምቢ!" ብለህ ትቆጣለህ። በእርግጥም ያስቆጣል።

ግን ሌላ የሚከፋ ሽታ ያለው ቆሻሻን ጭኖ ለመጣ ባላጋራ እኮ በፈቃድህ የከፈትከው ቤት አለ። የምን ቤት? ልብህ ነዋ፤ ማን ይኖርበታል አልኸኝ? እግዚአብሔር ነዋ። አንተ ለመኖሪያ ቤትህ ጽዳት የምትጠነቀቀውን ያህል የያዕቆብ አምላክ ለሚያርፍበት ኅሊናህ ተጠንቅቀህ ታውቃለህ? ሰይጣን ጭኖ የሚያመጣውን የኃጢአት ቆሻሻ ሁሉ እሺ ብለህ ወደ ልብህ በማስገባት የፈጣሪህን መቅደስ ለምን ታቆሽሻለህ? ንጹሑ እግዚአብሔር የሚያድርበትን ቤት ሊያቆሽሽ በመጣ ሰይጣን ላይ እንዴት አልተቆጣህም? ድፍረቱ ለምን አላብከነከነህም?

እግዚአብሔር አንተ ልትኖርበት ከምትፈልገው ንጹሕ ቤት የበለጠ ጽዱ መቅደስ የማይፈልግ ይመስልሃል?

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
አዲስ አበባ
1.6K views✞£iŧsûm✞, edited  12:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 09:34:39
+++ እንዲህ ዐይነት ሕዝብ . . . +++

ጦርነት የሚወድ ሕዝብ፥ ግድያን በባህሉ ያስውባል፤ በሥነ ቃሉ ያጌያግጣል፤ በልሂቃኖቹ የፍትሐዊነት አክሊል ያቀዳጃል፤በእንደራሴዎቹ ያውጃል። ጭካኔን የጀግንነቱ ምስክር አድርጎ ይተርካል። የኅዘን ድንኳኑም ሰው በመሞቱ ሳይሆን፥ በአሟሟቱ በሚያዝኑ ስዎች ይሞላል።

በእንዲህ ዓይነት ሕዝብ ውስጥ ከሰው ሞት ይልቅ የአጋዘን ሞት ይከብራል። ከሚገደለው ሰው ይልቅ መግደያው ቦታ አለው። ለሰይፉ፣ ለጦሩ፣ ለሜንጫውና ለጋሻው የክብር ማስቀመጫ አለው። እርሱ የማይበላውን ቅባት፥ መግደያውን ይወለውልበታል። ለግዳይ የሚፈለገው ክቡሩ የሰው ልጅ ግን ራሱን ከሞት የሚያድንበት ጥግ የለውም። ለሞቱም ማንነቱ ይጠቀሳል።

በእንዲህ ዐይነት ሕዝብ ውስጥ የጅምላ ግድያ ወንጀል መሆኑ ቀርቶ ፥ የዚያ ሕዝብ ቋሚ እሴት ወደ መሆን ይለወጣል።

እንዲህ ዐይነቱን ማኅብረሰባዊ ሽንቁር ቅዱስ ቆጵርያኖስ ዘቅርጣግና ሲገልጠው "ስዎች ግድያን በብቸኝነት ሲፈጽሙት እንደ ወንጀል ይቆጠራል፤ በጅምላ ሲያደርጉት ግን ወደ እሴትነት ይለወጣል።” በማለት ነው።
እኛም እንደሕዝብ እንዲህ ሆነን ይሆን የጅምላ ግድያን የተከባከብነው?

(~ ዲያቆን ታደሰ ወርቁ ~)
165 views✞£iŧsûm✞, edited  06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-06 08:31:02
"አቤቱ ወደ ሞት የሚነዱትን ታደግ፤
ሊታረዱ የተወሰኑትን አድን" ምሳ.24:11

በዚህች ሰዓት በወለጋ ወገኖቻችን በፍርሃትና ጭንቀት ላይ ናቸው:: እነርሱን የከበበ ሞት ያልከበበን እነርሱ ባሉበት ሥፍራ ባለመገኘታችን ብቻ ነው:: አድራሻው ተቀየረ እንጂ አሁንም እንደ ቅጠል የሚረግፉት የገዛ ወንድሞቻችን ናቸው::

"አቤቱ እስከ መቼ ድረስ ነው?" መዝ. 6:3

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
360 views✞£iŧsûm✞, edited  05:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 22:51:08
እንኳን ደስ አላችሁ በዩቲዩብ የምናውቀው #ማኅቶት_ቲዩብ አሁን ደግሞ በቴሌግራም መጥታል ለመቀላቀል ከስር Join የሚለውን ንኩት።

https://t.me/+SLPMr-p0D_QzRyzI
127 views✞£iŧsûm✞, 19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-05 22:51:08
.

ለፕሮፋይል ፒክቸር የሚሆኑ መንፈሳዊ ፎቶዎችን ማግኘት ይፈልጋሉ መልሶት አዎ ከሆነ ከስር ያለውን ሊንክ በመጠቀም ማግኘት ይችላሉ


https://t.me/+YkS5xznutqNjZTE0
https://t.me/+YkS5xznutqNjZTE0
https://t.me/+YkS5xznutqNjZTE0
292 views✞£iŧsûm✞, 19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ