Get Mystery Box with random crypto!

+++ እንዲህ ዐይነት ሕዝብ . . . +++ ጦርነት የሚወድ ሕዝብ፥ ግድያን በባህሉ ያስውባል፤ በ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

+++ እንዲህ ዐይነት ሕዝብ . . . +++

ጦርነት የሚወድ ሕዝብ፥ ግድያን በባህሉ ያስውባል፤ በሥነ ቃሉ ያጌያግጣል፤ በልሂቃኖቹ የፍትሐዊነት አክሊል ያቀዳጃል፤በእንደራሴዎቹ ያውጃል። ጭካኔን የጀግንነቱ ምስክር አድርጎ ይተርካል። የኅዘን ድንኳኑም ሰው በመሞቱ ሳይሆን፥ በአሟሟቱ በሚያዝኑ ስዎች ይሞላል።

በእንዲህ ዓይነት ሕዝብ ውስጥ ከሰው ሞት ይልቅ የአጋዘን ሞት ይከብራል። ከሚገደለው ሰው ይልቅ መግደያው ቦታ አለው። ለሰይፉ፣ ለጦሩ፣ ለሜንጫውና ለጋሻው የክብር ማስቀመጫ አለው። እርሱ የማይበላውን ቅባት፥ መግደያውን ይወለውልበታል። ለግዳይ የሚፈለገው ክቡሩ የሰው ልጅ ግን ራሱን ከሞት የሚያድንበት ጥግ የለውም። ለሞቱም ማንነቱ ይጠቀሳል።

በእንዲህ ዐይነት ሕዝብ ውስጥ የጅምላ ግድያ ወንጀል መሆኑ ቀርቶ ፥ የዚያ ሕዝብ ቋሚ እሴት ወደ መሆን ይለወጣል።

እንዲህ ዐይነቱን ማኅብረሰባዊ ሽንቁር ቅዱስ ቆጵርያኖስ ዘቅርጣግና ሲገልጠው "ስዎች ግድያን በብቸኝነት ሲፈጽሙት እንደ ወንጀል ይቆጠራል፤ በጅምላ ሲያደርጉት ግን ወደ እሴትነት ይለወጣል።” በማለት ነው።
እኛም እንደሕዝብ እንዲህ ሆነን ይሆን የጅምላ ግድያን የተከባከብነው?

(~ ዲያቆን ታደሰ ወርቁ ~)