Get Mystery Box with random crypto!

~ዜና ተዋሕዶ~ የኤርትራው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ሥርዓተ ቀብር ላይ ለመገኘት | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

~ዜና ተዋሕዶ~

የኤርትራው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ሥርዓተ ቀብር ላይ ለመገኘት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች ወደ አስመራ ያቀናሉ !

ሕዳር 28 ቀን 2015 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ቀዳማዊ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በቅዱስነታቸው ሥርዓተ ቀብር ላይ የሚገኙ ልዑካንን በዛሬው ዕለት ወደ አስመራ እንዲጓዙ ወስኗል።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የታላቋ ብሪታኒያ እና የሩቅ ምሥራቅ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ተመድቦው በአስመራ በሚካሄደው ሥርዓተ ቀብር ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ይወክላሉ።

ተ.ሚ.ማ እንደደረሰው መረጃ የቅዱስነታቸው አቡነ ቄርሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ዘሀገረ ኤርትራ ግብዓተ መሬት በነገው ዕለት በአስመራ ቅድስት ማርያም ካቴድራል ይከናወናል።


~ምንጭ~

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ