Get Mystery Box with random crypto!

'የብልጽግና ወንጌል' የሚለው አስተምህሮ እምነት በፕሮቴስታንቶች ውስጥ ባሉ በተለያዩ ግለሰቦችና አ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

"የብልጽግና ወንጌል" የሚለው አስተምህሮ እምነት በፕሮቴስታንቶች ውስጥ ባሉ በተለያዩ ግለሰቦችና አንጃዎች የሚታመን እምነት ሲኾን ፣ ዋናው አስተምህሮውም የእግዚአብሔር ዋናው ፍቃድ በእርሱ የሚያምኑ ሰዎች ኹሉ ሀብታሞች ጤናማዎች እንዲኾኑ ነው የሚል ነው ። የብልጽግና ወንጌል አማኞች አስተማሪዎች ሰዎች በእርሱ ካመኑ እግዚአብሔር ደግሞ ሀብትን ጤናን አብዝቶ ይሰጣቸዋል ፤ ቤተሰባዊ ሕይወታቸው ተድላ ደስታ የመላበት ፥ ስራቸው ሁሉ የተቃናና አልጋ በአልጋ ይኾናል ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ በእግዚአብሔርና በአማኙ መካከል ላለው ለዚህ ስምምነት የውል ማረጋገጫ ነው ይላሉ ። ይህ አስተምህሮ እንግዲህ ሰዎች እነርሱ ካሰቡት ሐሳብ ጋር ምድራዊ ፍላጎታቸውን የሚያሳካላቸው ሆኖ ስለሚያገኙት ይቀላቀሉት ዘንድ ይወዳሉ ።

ክርስትና ከዚህ ይለያል እኛስ ሐገራችን በሰማይ ነው ማለት በምድር እያለን ምድርን ሰማይ አድርገን መኖር መቻል ክርስቶስ ለእኛ እንዳሰበልን መኖር እንጂ እኛ እንዳሰብነው መኖር አለመሻት ማለት ነው ።

~ዲያቆን ፍፁም ከበደ~