Get Mystery Box with random crypto!

ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የሰርጥ አድራሻ: @zdfitsumkebe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.71K
የሰርጥ መግለጫ

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-11-23 09:18:35 ቅዱስ ቄርሎስ እውነተኛ ጾም የነፍስ ተድላ ደስታ ማግኛ እንደሆነ ሲናገር''ከሥጋና ከወይን በመከልከልና እነዚህን በመተው የምንጾመው የረከሱ ነገሮች ናቸው ብለን በመጸየፍ አይደለም ነገር ግን እነዚህ የሚታዩት ቁሳዊ ነገሮችን በመናቅና በመተው መንፈሳዊና ሰማያዊ ተድላ ደስታን እናገኝ ዘንድ ተስፋ በማድረግ ነው እንጂ በጾማችን ጊዜ ሥጋንና ወይንን የምንተወው ሰማያዊ ዋጋን ከእግዚአብሔር ዘንድ እናገኝ ዘንድ ተስፋ ስለምናደርግ ነው፤በለቅሶ ዘርተን በደስታ እናጭድ ዘንድ ነው እንጂ ከእነዚህ ነገሮች ስትከለከሉና ስትታቀቡ የተጠሉና የረከሱ ነገሮች እንደሆኑ አድርጋችሁ ማሰብ የለባችሁም ነገር ግን ሥጋና ወይን በተፈጥሯቸው መልካም ነገሮች ቢሆኑም በፊትህ ስለተዘጋጁልህ መንፈሳዊ ነገሮች ስትል በጾም ጊዜ እነርሱን ተዋቸው።'' በማለት ተናግሯል።
ቅዱስ አትናቴዎስ ደግሞ
"ጾም ከመላእክት ጋር በአንድ ማዕድ መቀመጥ ነው" ይላል።

መልአከ ገነት እሸቴ የተባሉ ታዋቂ ባለቅኔ ስለጾም እንዲህ ሲሉ (የሚብዝኁ) ቅኔ ተቀኝተዋል።
ግዘፈ ሥጋ በእክል ወግዘፈ ነፍስ በጾም አምጣነ ሥጋ ጽኑስ።
ኢይቀውም ምንተ እንበለ መብልዕ ሐዲስ።
ወእንበለ ጾም ብዙኅ አልባቲ በቊዔት ለባሕታዊት ነፍስ።
''የሥጋ ውፍረት በእህል ሲሆን የነፍስ ውፍረት ደግሞ በጾም ነው፤ችጋረኛ ሥጋ ያለ አዲስ ምግብ ምንም አይቆምም ለብቸኛ ነፍስ ያለብዙ ጾም ጥቅም የላትም።

ቅዱስ ያሬድ'' እስመ በጾም ወበጸሎት ኤልያስ ዐርገ ውስተ ሰማያት።
በጾም ኤልያስ ወደ ሰማያት ዐረገባት።''

እንኳን ለጾመ ነብያት በሰላም አደረሳችሁ
@akanim1wasen2
@akanim1wasen2
@akanim1wasen2

ይቀላቀላሉ ያተርፉበታል
873 viewsወሰንየለው ባህሩ, 06:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-22 22:03:24 ስለ ምን ማወቅ ይፈልጋሉ
ስለ ስርአተ ቤተክርስቲያን:ስለ ምስጢረ ቁርባን፡ መንፈሰዊ ምክር፡ታሪክ የየእለቱ ስንክሳር ፡ የሚዘከርበት ፍፁም ኦርቶዶክሳዊ ቻናል። ናታኒም ቲዩብ
መቼ ነው ፍጹም ክርስቲያን የምትሆኑት ጊዜያችሁን አታባክኑ አሁኑኑ join ብላችሁ መንፈሳዊ ሰው ሁኑ ክርስቲያን መንፈሳዊ ሰው ነው



𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒
514 views✞£iŧsûm✞, 19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-22 22:02:36
እንኳን ደስ አላችሁ በዩቲዩብ የምናውቀው #ማኅቶት_ቲዩብ አሁን ደግሞ በቴሌግራም መጥታል ለመቀላቀል ከስር Join የሚለውን ንኩት።

https://t.me/+SLPMr-p0D_QzRyzI
262 views✞£iŧsûm✞, 19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-22 09:41:36 ~ፆመ_ነብያት~

# ፆመ_ነብያት_መቼ_ይገባል ?
ለምንስ_እንፆማለን?
ፆመ ነብያት ወይም የገና ፆም

#ሐሙስ ህዳር 15 ይጀምራል ታህሳስ 29 በዕለተ ይፈታል። ይህ ማለት የዘንድሮ የገና ፆም ቅበላ እስከ ማክሰኞነው ከረቡዕ ጀምሮ የፍስክ ምግቦች አይበሉም።

ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው ነብያት የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ የፆሙት ታላቅ ፆም ነው።

ዛሬም እኛ ክርስቲያኖች የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በፆምና በፀሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የምናስብበት ነው።

=> ይህ ፆም፣ ፆመ ድህነት፣ ፆመ ማርያም ፣ ፆመ አዳም ፆመ ፊሊጶስ ፆመ ስብከት በመባል ይጠራል።

# ፆመ_ድህነት የተባለበት ምክንያት መርገመ ስጋ መርገመ ነብስ የአዳም እዳ በደል ጠፍቶ ድህነት ስለተገኘበት ነው።

# ፆመ_ማርያም የተባለበት ምክንያት ንፅይተ ንፁሃን ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስ ድንግል ማርያም ጌታን በማህፀኔ ተሸክሞ ልፆም ልፀልይ ይገባል ብላ ለ40 ቀን እስከ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ድረስ የፆመችው ፆም ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል።

# ፆመ_አዳም የተባለበት ምክንያት ለአዳም የተነገረው ትንቢት፣ የሚጠበቀው ሱባኤ እንደደረሰ የሚያበስር በመሆኑ ጾመ አዳም ይባላል፡፡ አዳም ቢበድልም ንስሐ ገብቶ በማልቀሱ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ ብሎ የተነገረው ተስፋ መድረሱን፣ ምሥጢረ ሥጋዌ እውን ሊሆን መቃረቡን የሚያስረዳ ጾም ነው፡፡

# ፆመ_ፊሊጶስ የተባለበትም ምክንያት ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ ሲያስተምር በሰማዕትነት ሲሞት አስከሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስከሬን እንዲገልጽላቸው ከኅዳር አስራ ስድስት ጀምረው ሲጾሙ በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስከሬን ቢመልስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል ለዚህም ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

# ፆመ_ስብከት የተባለበትም ምክንያት የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት የሰውልጆች ተስፋ የተመሰከረበት የምሥራቹ የተነገረበት

ስለሆነም «ጾመ ስብከት» ይባላል፡፡
ፆሙን የሀጥያታችን መደምሰሻ መንግስተ ሰማያተን መውረሻ ያድርግልን። የቅዱሳን ነብያት አባቶቻችንንም በረከት በሁላችንም ላይ ያሳድርብን።
ወስበሐት_ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ_ድንግል
ወለመስቀሉ_ክቡር
አሜን ።
8.8K views✞£iŧsûm✞, edited  06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-21 07:06:30 ኅዳር ፲፪

~ ለውጦ ማክበር ~

ንግሥት ክሌዎፓትራ "ሳተርን" ለሚባል ጣዖት ያሠራችው ቤት በእስክንድርያ ነበር። ይህ ቤተ ጣዖት እስከ እለ እስክንድሮስ ፓትርያርክ ዘመን 212-326 ድረስ ነበር። እለእስክንድሮስም ሊያጠፋ ሲነሣ በሕዝቡ ልቡና ገና አምልኮ ጣዖት ስላልጠፋላቸው 18 ፓትርያሪኮች ያልነኩትን አንተ ለምን ታፈርስብናለህ ብለው ተቃወሙት። እለእስክንድሮስም ሕዝቡን መክሮና አስተምሮ የሳተርን በዓል ይውልበት የነበረበትን ዕለት ወደ ቅዱስ ሚካኤል የበዓል ዕለት አደረገው። (ስንክ ሳር ኅዳር 12፣ Coptic Encyclopedia, Vi S.p 1617)።

ከእምልኮ ጣዖት ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር የእስክንድርያ ሰዎች በእለ እስክንድሮስ በኩል እየበረሩ ገቡ። የጣዖት መክበሪያ የነበረው በእለ እስክንድሮስ ጸሎት የቅዱስ ሚካኤል መክበሪያ የእግዚአብሔር መመስገኛ ኾነ። ይህን ቤተ ጣዖት ሳስብ ምናልባት በኃጢአታችን ምክንያት የእኛን ሰውነት የሚወክል ይኾን እላለሁ። ብዙዎቻችን የእግዚአብሔር መቅደስ የኾነውን ሰውነታችንን የአጋንንት መርኪያ ቤተ ዘፈን አድርገነዋልና።

የሰው ልቡና የእግዚአብሔር ቤተ መንግሥት ነው። ኾኖም ሰዎች ሰውነታቸውን እያረከሱና ከእግዚአብሔር ፍቅር እየራቁ ሲሄዱ የአጋንንት መኖሪያ ሊያደርጉት ይችላሉ። በመኾኑም የሕይወታችን ዋና ጉዳይ መኾን ያለበት መቅደስ ሰውነታችንን መጠበቅ ነው። በእለእስክንድሮስ አምሳል በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለአገልግሎት የሚፋጠኑ ካህናትን በቅዱስ መስቀል ባርከው እንዲያነጹን መቅረብ ነው። ዝሙት የተባለ ጣዖት በልቡናችን ውስጥ የያዘውን ቦታ በካህናት ፊት ተናዘን እንድንነጻ የሚያደርገውን የንስሐን ቀኖና መቀበል ነው። ሕይወታችንን እያዛጉ ያሉትን ማናቸውንም ባዕድ የኾኑ ነገሮች በልቡናችን ውስጥ ሥር እንዳይዙ መጠንቀቅ ነው።

በእርጥም እኛ ፈቃዳችንን ለእለእስክንድሮሳዊ ፈቃድ ካስገዛን ሰውነታችን የቅዱሳን መላእክት በዓል መክበሪያ ወደ መኾን ይታደሳል። ቅዳሴ፣ ማኅሌትና ልዩ አገልግሎት ያለማቋረጥ የሚቀርብበት ንጹሕ መቅደስ ይኾናል። እንግዲያውስ ኹላችንም በሰውነታችን ውስጥ ቅዱስ ሚካኤልን እንፈልገው፤ በበዓልነት በእኛ ውስጥ እንዲከብር እንፍቀድ። ሰዎች የቅዱስ ሚካኤልን ያማረ የምልጃ ሽታ በእኛ ሰውነት ውስጥ እንዲያሸቱት እናድርግ! ወደ ቅዱስ ሚካኤላዊ የአገልግሎት ሕይወት ለመግባት እንመኝ፤ ደጋግመንም እንሻ!

( "ዲ/ን ዮሐንስ ጌታቸው" fb የተወሰደ ።)

እንኳን አደረሳችሁ የቻናሌ ቤተሰቦች

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ
ኅዳር 12 2015 ዓ.ም
226 views✞£iŧsûm✞, 04:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 21:59:24
ህዳር ፲፪ እንኳን አደረሳችሁ

እንደዚህ አይነት ምርጥ ምርጥ ፕሮፋይል ፒክቸሮችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ።

https://t.me/Ortho_pictures
https://t.me/Ortho_pictures
https://t.me/Ortho_pictures
52 views✞£iŧsûm✞, 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 21:59:15 ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል ሊቀላቀሉት የሚገባ ቻናል ነው።
በቻናሉ ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል
ቻናሉን ለመቀላቀል)

ቤተ ክርስቲያን ከሕግ በላይ ናት
ኢየሱስ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነው ማለት ምን ማለት ነው
ሕግ መቼ ተመሠረተ
ለምንስ ተመሠረተ

@EOTC_-OPEN_channel
@EOTC_-OPEN_channel
@EOTC_-OPEN_channel
20 views✞£iŧsûm✞, 18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 09:07:13 ~በዝምታ የተፈጸመ ተአምር~

በቃና ዘገሊላ ጌታችን የሠራው ተአምር አምላካዊ ኃይሉን የሚያስረዳ ድንቅ ሥራ ነው እንጂ ምትሐት አይደለም።ብዙ ምትሐት የሚሰሩ ሰዎች በዓለም ላይ አሉ። እነዚህ ምትሐተኞች አስማታቸውን ሲሠሩ ብዙ ድግምት እየደገሙ በዕቃ ወይም በሰው ላይ እጃቸውን እያዞሩ እነሱም ብዙ ፍዳ እያዩ ከተለመደው ነገር ውጪ ሰዎችን እንዲህ አድርጉ እንዲህ አታድርጉ ብለው መከራ እያሳዩ ነው።ካሉት ቃል ወይም አካሔድ አንዳች ነገር ዝንፍ ቢል አስማቱ ሊከሽፍ ጨዋታው ሊፈርስ ይችላል። እንዲህ አድርገው የሚሰሩትን ምትሐት''የአባቶች አብነት ነው ጥበብ ነው አርት ነው ሳይንስ ነው በሰለጠኑት ዓለማት የተለመደ ነው'' እያሉ ሊያሳምኑን ይሞክራሉ።መቼም ዲያብሎስ ለኃጢአት የማያወጣው 'የክርስትና ስም' የለም።
ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን የቃናውን ተአምር ሲሠራ እንኳን ውኃውን ጋኖቹን በእጁ አልነካቸውም ጨርሶም አልተጠጋም።ለአገልጋዮቹ ''እስከ አፋቸው ውኃ ሙሉአቸው'' ከማለት በቀር ''በዚህ መንገድ ሒዱ ከዚህኛው ወንዝ ቅዱ ሰው እንዳታናግሩ በዚህ ጋር እንዳትዞሩ'' የሚል ዝርዝር አልተናገረም አገልጋዮቹም ውኃውን የቀዱት በማንኛውም ጊዜ እንደሚቀዱት ነው።ውኃው የተለየ ነገር እንዳልተጨመረበት በሚያረጋግጥና ሁሉም በግልጥ ሊያዩት በሚችሉበት ሁኔታ እስከ አፉ ድረስ እንዲሞላ ነው ያደረገው ።በአንደበቱ ''አንተ ውኃ የወይን ጠጅ ኹን'' ብሎም አልተናገረም ዓለማትን በዝምታ(በአርምሞና በኃልዮ) የፈጠረ አምላክ መሆኑን ሊያስረዳ ውኃውን ወይን ያደረገው በዝምታ ብቻ ነው። አይሁድ ወይን ጠጅ ሲጠምቁ የማስከር ኃይሉን ለመቀነስና ለብዙ ሰው ለማዳረስ አንድ እጁን ወይን በሦስት እጅ ውኃ ይበርዙት ነበር ። አምላካችን ወይን የሚበረዝበትንና ጣዕም የሚጠፋበትን ውኃ ወይን አደረገው።

ቃና ዘገሊላ ገፅ 101-102
ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ

መልካም ዕለተ ሰንበት ይሁንላችሁ
1.0K viewsሞቱማ ቸርነት, edited  06:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 07:21:15 የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ስረዓቱን እና ደምቡን ጠብቀው የተዘጋጁ ዝማሬዎች እንዲሁም የተለያዩ ትምህርቶችን መንፈሳዊ የቅዱሳን ታሪኮችን የሚያገኙበት የዩቱብ ቻናል እንጠቁሞ
በዚህ ቻናል
የተለያዩ የአውደምህረት ስብከት ዝማሬ
አዳዲስ ዝማሬ የሚያገኙበት
የቅዱሳን አባቶች ታሪክ
ጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት ታሪክ
ኢአማንያን በተዋህዶ ዙርያ ለሚጠይቁት ጥያቄ በሊቃውንት መልስ ያገኙበታል

በዚህ ቻናል ብዙ ስለሚያተርፉ ይግቡና ሰብስክራይብ ያድርጉ አገልግሎቱን ያበረታቱን

ይህ መንፈሳዊ እንጂ አለማዊ ቻናል አይደለም ማንም የተዋህዶ ልጅ የሆነ ሰብስራይብ ያድርግ

█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░ ► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵 ▒▓█
█▓▒░► 𝑶𝑷𝑬𝑵 ░ 𝑶𝑷𝑬𝑵
𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 ‌‌
571 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 04:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-19 22:48:48 ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል ሊቀላቀሉት የሚገባ ቻናል ነው።
በቻናሉ ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል
ቻናሉን ለመቀላቀል)

ቤተ ክርስቲያን ከሕግ በላይ ናት
ኢየሱስ ክርስቶስ የሕግ ፍጻሜ ነው ማለት ምን ማለት ነው
ሕግ መቼ ተመሠረተ
ለምንስ ተመሠረተ

@EOTC_-OPEN_channel
@EOTC_-OPEN_channel
@EOTC_-OPEN_channel
360 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ