2022-11-15 07:09:25
~ ደብረ ቁስቋም~
ህዳር ስድስት
እመቤታችን ከልጇ ከወዷጇ ከጌታችን ጋር ከስደት ወደሀገሯ የተመለሰችበት ቀን ነው
ይህም ቀን ቁስቋም ተብሎ ተሰይሟል።
ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ተራራ ማለት እንደሆነ
ደብረ ታቦር ማለትም የታቦር ተራራ ማለት እንደሆነ
ደብረ ሲና ማለት የሲና ተራራ ማለት እንደሆነ።
ደብረ ሊባኖስ ማለትም የሊባኖስ ተራራ ማለት እንደሆነ።
ደብረ ቁስቋም ማለት የቁስቋም ተራራ ማለት ነው
ጌታችን ታምራት በሰራባቸው ተራራዎች በአሉ በተራራዎች ተሰይሞ ይከበራል።
ቁስቋምም እመቤታችን ከስደት ስትመለስ ከልጇ ከጌታችን ከፃድቁ ከዮሴፍ ከቅድስት ሰሎሜ ጋራ ያረፈችበት ተራራ ነው ።
ስለዚህ በአሉ ቁስቋም ተብሎ ይከበራል።
እመቤታችን ከልጇ ጋራ 42 ወር ተሰዳ በግብፅ ከኖረች በሇላ አሳዳጃው ሄሮድስ ሰለሞተ ወደሀገራ እንድትመለስ መልአኩ ለዮሴፍ ነግሮት ሲመለሱ በዚህ ተራራ ላይ አርፈዋል።
በዚም ተራራ ላይ ቅዱሳን መላእክት ክንፋቸውን ዘርግተው በእመቤታችን እና በጌታችን ላይ ረበዋል
ሊቁ ቅዱስ ያሬድም
~ዮም ፀለሉ መላእክት ላእለ ማርያም ወላእለ ወልዳ ክርስቶስ በደብረ ቁስቋም~
ብሎ እንደተናገራው በዚህ ተራራ መላእክት ረበው ዘምረውበታል አመስግነውበታል
እመቤታችን ተአምራት ባደረገችበት ዕለትና ተራራ ተሰይሞ በአለ ክብሯ ይከበራል።
ስለዚህ ቁስቋም ማለት ማርያም ማለት አይደለም እመቤታችን ያረፈችበት ተራራ ነው እንጂ
ልደታ በአታ ኪዳነ ምህረት ፍልሰታ ማለትም ማርያም ማለት ሳይሆን ልዩ ልዩ ታሪኳ የተከናወነበት ቀን ነው
ልደታ ብለን የምናከብረው የተወለደችበትን ቀን ነው
በአታ ብለን የምናከብረው ቤተ መቅደስ የገባችበት ቀን ነው
ኪዳነ ምህረት ብለን የምናከብረው የምህረት ቃል ኪዳን የተቀበለችበትን ቀን ነው
ፍልሰታ ብለን የምናከብረው ተነስታ ሥጋዋ ወደሰማይ
በእርገት የፈለሰበትን ቀን ነው
መናፍቃን እንደሚሉት ተራራ አናመልክም
ሰው የተወለደበትን ቀን እንደሚያከብር
እኛም እመቤታችን የተወለደችበትን ከስደት የመለሰችበትን ከሞት የተነሳችበትን ቀን እናከብራለን
በዘመናችን ያሉ ሰዎች
የአህያ ቀን
የውሻ ቀን
የበሽታ ቀን እያከበረ
የእመቤታችን የጌታችን የፃድቃንን ክብረ በአል ቀን ማክበር ያቅተዋል ።
ህዳር 5/2010
አዲስ አበባ
(~ መጋቤ ሐዲስ ሄኖክ ፈንቴ~)
እንኳን አደረሳቹሁ የቻናሌ ቤተሰቦች !!!
ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ
8.5K views✞£iŧsûm✞, edited 04:09