Get Mystery Box with random crypto!

ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zdfitsumkebe — ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ
የሰርጥ አድራሻ: @zdfitsumkebe
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.71K
የሰርጥ መግለጫ

ዘማሪ ዲያቆን ፍፁም ከበደ

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2022-11-13 08:56:41
እግዚአብሔር ሁልጊዜ ወደ መከራ እንዳትገባ አያደርግም። አንዳንድ ጊዜ በወጀብ ውስጥ መንገድ ያዘጋጅልሃል። ግፊው በሚበዛበት ዐውሎ ነፋስ እያለፍህ ተፍገምግመህ እንዳትወድቅ ጉልበትህን ያጸናል፤ ኃይልን ያስታጥቅሃል። እንዲህ እያደረገ በመንፈስ ያጎለምስሃል።

እግዚአብሔር ዳንኤልን በአናባስት ጉድጓድ ከመጣል፣ ሠለስቱ ደቂቅን ወደ እቶን እሳት ከመግባት፣ ጳውሎስና ሲላስን ወደ ወኅኒ ከመውረድ ሊያድናቸው ይችል ነበር። ይሁን እንጂ እንዲህ አላደረገም። አምላካችን ፈተና ካለባቸው ቦታዎች ሁሉ ሊያወጣን ቃል አልገባምና። ነገር ግን በመከራ ጊዜያችን ሁሉ ከእኛ እንደማይለይና በእውነት ይዘነውም እንደ ሆነ በድል ነሺነት እናጠናቅቅ ዘንድ እንደሚረዳን ቃሉን ሰጥቶናል።

የጌታ እናት እመቤታችን የተወደደ ልጇን ይዛ በግብጽ በረሃ እንደ ወፍ ከተንከራተተች በኋላ ሕፃኑን የሚፈልገው ክፉ ሄሮድስ ሲሞት ተመልሳ ወደ ገሊላ ገብታለች። እንደ ድንግል ጌታን በመሐል እጅህ ብትታቀፍ እንኳን  ግብጽ መውረድ  አይቀርልህም። ይሁን እንጂ የመጣብህን መከራ ድል ነሥተህ ወደ ገሊላ መመለስህም እርግጥ ነው።

"ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል"
                              1ኛ ቆሮ 10፥13


ዲያቆን አቤል ካሳሁን
አዲስ አበባ
951 views✞£iŧsûm✞, edited  05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 22:34:57 ትክክለኛ ወቅታዊ ኦርቶዶክሳዊ መረጃ ማግኘት ይፈልጋሉ?
የተለያዩ የአውደምህረት ዝማሬ፣ ስብከት
ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃ
የቅዱሳን እና የገዳማት ታሪኮች
እነዚህን ለማግኘት ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን እና ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ እንሁን

subscribers subscribers
subscribers subscribers




306 viewsማኔ ቴቄል ፋሪስ, 19:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-12 22:06:26
እንደዚህ ውብ የሆኑ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስዕሎችንና ፎቶዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/+YkS5xznutqNjZTE0
https://t.me/+YkS5xznutqNjZTE0
230 views✞£iŧsûm✞, 19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 18:23:51 ++ አባቶቻችን እንዲህ አሉ ++

"መካሪ አያስፈልገኝም የማለትን ያህል ታላቅ ትዕቢት የለም"
ቅዱስ ባስልዮስ

"በኃጢአት በወደቅህ ጊዜ ተስፋ ቆርጠህ ጸሎትህን እንዳታቆም። ንስሓ እስከምገባ ድረስ ብለህ ጸሎት ካቆምክ መቼም ንስሓ አትገባም። ምክንያቱም ጸሎት ራሱ የእውነተኛ ንስሓ መግቢያ በር ነው" ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ

"ሰዎች አንድ ሰው ተነሥቶ ሌላውን ሲገድል ወንጀለኛ ነህ ይሉታል። አንድ ላይ ተሰባስበው ብዙ ሰዎችን ሲገድሉ ግን ውጊያ ይሉትና መግደላቸውን ጀግንነት ይሉታል" ቅዱስ ቆጵሮሳዊ

"የክርስቲያኖች መሣሪያ በእጃቸው ሰይፍን መታጠቅ ሳይሆን እጃቸውን ወደላይ ለጸሎት መዘርጋት ነው"
ቅዱስ አትናቴዎስ ዘእስክንድርያ

"እግዚአብሔር ለአብርሃም "ከሀገርህ ውጣ ከወገኖችህ"ተለይ ብሎት ነበር። በዚህ ጥሪ እግዚአብሔር ሁላችንንም የተወለድንበት ዘር እንድንተው ይጠራናል። ሰማዕቱ ዮስጦስ (100 AD-165 AD)

"ክርስቶስ ጴጥሮስን "ሰይፍህን ወደ ሰገባው አስገባ" ሲለው ትጥቅ ያስፈታው ጴጥሮስን ብቻ ሳይሆን እንደ ጴጥሮስ በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ነበር" ሊቁ ጠርጡለስ (160 AD - 220 AD)

‹‹ይጸልያል ነገር ግን የሌሎችን ጸሎትም ይሰማል፡፡ ያለቅሳል የሌሎችን ዕንባ ግን ያብሳል፡፡ ሰው ነውና አልዓዛር ወዴት እንደተቀበረ ጠየቀ፡፡ አምላክ ነውና አልዓዛርን ከሞት አስነሣ፡፡ እርሱ በርካሽ ዋጋ ያውም በሠላሳ ብር ብቻ ተሸጠ፡፡ ነገር ግን ዓለምን በውድ ዋጋ በከበረ ደሙ ገዛ፡፡ እንደ በግ ለመታረድ ተነዳ እርሱ ግን የእስራኤል እረኛ የዓለምም ሁሉ ጠባቂ ነበረ፡፡ እንደ በግ ዝም አለ ነገር ግን እርሱ በምድረ በዳ በሚጮኽ ሰው ድምፅ የተሰበከ ቃል ነበር፡፡ እርሱ የተሰቃየና የቆሰለ ነበር ፤ ሁሉንም በሽታና ቁስል ግን ይፈውስ ነበር›› ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ

"ለቤተ መቅደስህ ተክል ያደረግኸኝ፡፡ አቤቱ ሆይ የውጭ ተክል አታድርገኝ፡፡ የጽድቅ ተክል አድርገኝ፡፡ የኃጢአት አይደለም፡፡ የዕውነት ተክል አድርገኝ የሐሰት አይደለም የፍቅር ተክል አድርገኝ የጽል አይደለም፡፡
የመጻሕፍት መጀመሪያ የምትሆን ኦሪት ደመና የምትጋርደኝ፡፡ ከቅዱስ ወንጌል ፈሳሽ የምጠጣ ከጎንህ ከፈሰሰው ደም የምረካ ልሁን፡፡ በናትህ በድንግል ጸሎት የሃይማኖት አበባ ላብብ፡፡ የጽድቅ ፍሬን ላፍራ ከቅዱሳንህ ሐዋርያትም ከቃላቸው ፍሬ የተነሣ እስከ ዘለዓለሙ ድረስ የተባረከ የወይን ቦታ ልባል የጽድቅን ፍሬ የሚያስቀረውንም የኃጢአት እሾህ ጠምዝዘው ከደጁም አሜከላውን አረሙንም ሙጃውንም ንቀለው፡፡ አቤቱ ከኔም አርቀው ሥርዓትህን የሚሠሩትን ያበባቸውን ፍጻሜ እንዳፈራ አድርገኝ" ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
2.8K views✞£iŧsûm✞, 15:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 13:01:41 ~ታናሽ መንፈሳዊ ጉባኤ~

አሁን አሁን የሚለቀቁ ማስታወቂያዎች መዳረሻቸው አደገኛ ይመስለኛል፡፡ የማስታወቂያው ግዝፈት ከፎቶው ጋራ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ እእንተና እነ እንተና የሚመጡበት ይላል፡፡
ከዚህ ማስታዎቂያ በኁዋላ በታናሽ ጉባኤ ማን ሊማር ይችላል?
የታናሽ እና የታላቅ መለኪያው ምንድን ነው?
መንፈስ ቅዱስ ትንሽ እና ትልቅ አለው?
ታላቅ ጉባኤ አንድ ቀን ገነት ያስገባል? ታናሹስ ጉባኤ ያዘገያል?
በታላቁ ደብር ምናምን ይላል ታናሽ ደብር አለ ማለት ነው?
በምናደርጋቸው ወለባዎች ትውልዱን መልከ ዘማ ያደረግነው ይመስለኛል፡፡
ታናሽነትን ማስታወቂያውም ጠላት፡፡ ታዋቂውም ጠላት፡፡

   ( ~ገብረ መድኅን እንየው~ )
2.3K views✞£iŧsûm✞, 10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 10:33:53
~ ወደ ቀድሞው ነገር እንመለስ ~

#መግብያ_ትኬቱ_ተልኮልናል
ጉባኤው አ አ በቤተ-ክህነት አዳራሽ (ጽርሐ ጽዮን አዳራሽ)

#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ዋናው_በር_ፊትለፊት_ሽዋ_ዳቦ_መነጽር_ቤቶቹ_ውስጥ_ወይም_በ0986025463_0966214181_ይደውሉ!!

https://t.me/BetMetsahfte
692 views✞£iŧsûm✞, edited  07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 19:08:39
እንደዚህ ውብ የሆኑ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስዕሎችንና ፎቶዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/+YkS5xznutqNjZTE0
https://t.me/+YkS5xznutqNjZTE0
195 views✞£iŧsûm✞, 16:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 19:07:38 ስለ ምን ማወቅ ይፈልጋሉ
ስለ ስርአተ ቤተክርስቲያን:ስለ ምስጢረ ቁርባን፡ መንፈሰዊ ምክር፡ታሪክ የየእለቱ ስንክሳር ፡ የሚዘከርበት ፍፁም ኦርቶዶክሳዊ ቻናል። ናታኒም ቲዩብ
መቼ ነው ፍጹም ክርስቲያን የምትሆኑት ጊዜያችሁን አታባክኑ አሁኑኑ join ብላችሁ መንፈሳዊ ሰው ሁኑ ክርስቲያን መንፈሳዊ ሰው ነው



𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒
293 views✞£iŧsûm✞, 16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 12:45:43
~የእግዚአብሔር ሀብት ነውና አንሱት~

ወንድሞቼ! ከእናንተ መካከል አንድ ዐይነ ሥውር ሰው ወደ ጉድጓድ ገብቶ ሊወድቅ ሲል እጁን ዘርግቶ የማይደግፈው ማን ነው ? ታዲያ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በልቡናቸው ታውረው ወደ ሲዖል ጉድጓድ ለዘላለም ሲወድቁ እንድምን እጃችን የበለጠ አይዘረጋም ? ወገኖቼ! በነፍስም በሥጋም የታመመ ሰው ስታዩ " የእኔ ሥራ አይደለም፣ የቀሳውስቱና የመነኮሳት ሥራ እንጂ። " አትበሉ። አንድ ትልቅ በወርቅ የተሞላ ሳጥን ወድቆ ብታዩ " ይህ እኔን አይመለከተኝም ሌሎች መጥተው ያንሡት እንጂ " ትላላችሁን ? ግራ ቀኛችሁን አይታችሁ በፍጥነት የምታነሱት አይደለምን ? ይህ ወደ ዘላለም ጉድጓድ እየወደቀ ያለው ወንድማችሁም ከዚያ ወርቅ በላይ ውድ የእግዚአብሔር ሀብት ነውና አንሡት እንጂ የበለጠ እንዲወድቅ አትደግፉት።

(~ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ~)

ሰማዕትነት አያምልጣችሁ
ተርጓሚ ገብረእግዚአብሔር ኪደ
1.2K views✞£iŧsûm✞, edited  09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 22:23:45
እንደዚህ ውብ የሆኑ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስዕሎችንና ፎቶዎችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ

https://t.me/+YkS5xznutqNjZTE0
https://t.me/+YkS5xznutqNjZTE0
199 views✞£iŧsûm✞, 19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ